YouVersion Logo
Search Icon

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

DAY 24 OF 28

የእግዚአብሔር ህዝብ አምላክንና ሌሎችን ውደድ የሚለውን ታላቅ ትዕዛዝ በተደጋጋሚ ችላ ማለታቸውን ብሉይ ኪዳን ይዘግባል። ከእነሱ የተሻለ ነገር ለማድረግ እንዴት ተስፋ እናደርጋለን? ኢየሱስ ከታላቁ ትእዛዝ ጋር የሚሄድ አዲስ ትእዛዝ በመጨመር መታዘዝ እንድንችል ይረዳናል። የኢየሱስ አዲሱ ትዕዛዝ የእርሱ የመሥዋዕትነት ፍቅር ለተከታዮቹ ሌሎችን የመውደድ ኃይል እንዴት እንደሚሰጥ ያሳያል።

ያንብቡ፦

ዮሐንስ 13÷34 ፣ ማርቆስ 12÷29-31ን ይከልሱ።
1ኛ ዮሐንስ 4÷9-11

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

ዮሐንስ 13÷34ን ከማርቆስ 12÷29-31 ጋር አነጻጽሩ። በእነዚህ ሁለት ትዕዛዛት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? የኢየሱስ ተምሳሌትነት ራሱ ታላቁን ትዕዛዝ በምን መልኩ ያሟላል?

1ኛ ዮሐንስ 4÷9-11ን በጥንቃቄ ይከልሱ። የትኛዎቹ ቃላት ወይም ሐረጎች ለእርስዎ ጎልተው ይታያሉ? በዚህ ክፍል መሰረት፣ ኢየሱስ ህይወቱን የሰጠው ለምን ነበር? ለሌሎች ያለንንስ ፍቅር ሊያነሳሳው የሚገባው ነገር ምንድን ነው?

ዛሬ ለተማሩት ነገር ምላሽ የሚሆን ጸሎት ለመጸለይ ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ።

Day 23Day 25

About this Plan

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More