YouVersion Logo
Search Icon

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

DAY 26 OF 28

አጋፔ ፍቅር በተቀዳሚነት ሰዎች ላይ የሚከሰት ስሜት አይደለም። ፍቅር ተግባር ነው። የሌሎችን ደህንነት ለመፈለግ ሰዎች የሚያደርጉት ምርጫ ነው። ሐዋሪያው ጳውሎስ፣ ከደብዳቤዎቹ በአንዱ፣ ፍቅር ከመንፈሳዊ እውቀት ወይም ከልዩ ችሎታዎች እንደሚበልጥና ምንም ነገር ያለፍቅር ትርጉም አልባ እንደሆነ ተናግሯል። በመቀጠልም ፍቅር በትክክል ምን እንደሚያስብና እንዴት እንደሚያደርግ በትክክል ይገልጻል።

ያንብቡ፦

1ኛ ቆሮንቶስ 13÷1-7

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

1ኛ ቆሮንቶስ 13÷4-7ን በወረቀት ላይ ጻፉ። ይህን ቃል በራስዎ እጅ ጽሑፍ በሚጽፉበት ጊዜ የትኞቹ ቃላት ወይም ሐረጎች ናቸው ለእርስዎ ጎልተው የሚታዩ?

በየትኛው የፍቅር ገጽታ ነው ይበልጥ ሊያድጉ የሚያስፈልግዎ? እግዚአብሔርን ይንገሩትና እንዲረዳዎ ይጠይቁት።

የጳውሎስን የፍቅር ፍቺ በመጠቀም ኢየሱስ እንዴት እንደወደድዎ ከግምት ውስጥ ያስገቡ። ለምሳሌ፣ ኢየሱስ ታጋሽ፣ ደግ፣ ትሁት እና የራሱን የማይፈልግ የሆነልዎ እንዴት ነው?

ዛሬ እግዚአብሔር እንደሚወዳቸው አስታዋሽ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ማን ናቸው? በዚህ ሳምንት ኢየሱስ ፍቅሩን በእርስዎ በኩል ማጋራት የሚፈልገው በምን መልኩ ነው? ስለዚህ ጉዳይ ለመጸለይ ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ። በሚጸልዩ ጊዜ ወደ አእምሮዎ የሚመጡ የትኛዎቹንም ሀሳቦች በጽሑፍ አስፍሯቸውና በዚህ ሳምንት የኢየሱስን ፍቅር ለማጋራት እቅድ አውጡ።

Day 25Day 27

About this Plan

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More