YouVersion Logo
Search Icon

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

DAY 25 OF 28

የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ፍቅርን የሚገልጥ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ራሱ ፍቅር ነው። እንደ ሥሉስ አምላክነቱ፣ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜም ሆነ ወደፊት ሌሎችን ያማከለ፣ ራሱን የሚሰጥ እና ህብረትን የሚወድ ነው። ፍቅር ከባህሪዎቹ አንዱ ብቻ አይደለም። ፍቅር ማንነቱ ነው። ኢየሱስ (እግዚአብሔር ወልድ) የእግዚአብሔርን ፍቅር በሙላት ገልጧል፤ ይህንንም በሰው ልጆች ፈንታ ህይወቱን በመስጠት በግልጽ አሳይቷል። ሰዎች ኢየሱስ እንደሚወዳቸው ሲያምኑ፣ የእግዚአብሔርን የፍቅር ህብረት ይቀላቀላሉ፤ ከእርሱ ጋር ሌሎችን ለመውደድ በሚያስችል መልኩ መሰረታዊ ባህርያቸውም ይቀየራል።

ያንብቡ፦

1ኛ ዮሐንስ 4÷8፣ 1ኛ ዮሐንስ 4÷16፣ 1ኛ ዮሐንስ 3÷16፣ ዮሐንስ 15÷9-13

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

1ኛ ዮሐንስ 4÷16ን ይከልሱ። እግዚአብሔር በእውነት እንደሚወድዎ ማመንን ተምረዋል?

ከሆነ፣ ፍቅሩን የመቀበል ተሞክሮትን ይግለጹ። እግዚአብሔር እንደሚወድዎ ሙሉ በሙሉ ማመን ከጀመሩ በኋላ በህይወትዎ የተለወጠ ነገር ምንድን ነው? የእርሱን ፍቅር ለሌላ ሰው ዛሬ እንዴት ማካፈል ይችላሉ?

ካልሆነ፣ እግዚአብሔር ለእርስዎ ያለውን ፍቅር ለመቀበል እንዴት እንደተቸገሩ ይግለጹ። እግዚአብሔር እንደሚወድዎ ሙሉ በሙሉ ቢያምኑ በህይወትዎ ምን የሚቀየር ነገር የሚኖር ይመስልዎታል?


ዮሐንስ 15÷9ን ይከልሱ። እግዚአብሔር አብ ኢየሱስን ምን ያህል የሚወደው ይመስልዎታል? ኢየሱስም እርስዎን በዚያ ልክ ይወድዎታል የሚለውን ሀሳብ አስቡበት። ይህን ሲያስቡ ምን አይነት ጥያቄዎች፣ ሀሳቦች ወይም ስሜቶች ተፈጠረብዎ?


ኢየሱስ ፍቅሩን ሰው ሊኖር ወይም ሊውል ከሚችልበት ስፍራ ጋር አነጻጽሮታል። በአንድ ስፍራ በትክክል ለመኖር፣ መጀመሪያ ወደዚያ ቤት ሊገቡ፣ የሸከፉትንም እቃ ቦታ ሊያሲዙ፣ የቤቱን አቀማመጥ ሊያውቁና በዚያ ስፍራ በምቾት እንዴት ሊመላለሱ እንደሚችሉ መማር ይኖርብዎታል። የሆነ ቦታ መኖር ሲጀምሩ ሌላ ምን ያደርጋሉ? ይህ ኢየሱስ ለእርስዎ ያለውን ፍቅር ከማመን ጋር እንዴት ይነጻጸራል?

ንባብዎና ምልከታዎ ወደ ጸሎት እንዲያመራ ያድርጉ። ፍቅሩ እንዴት እንደሚያስደንቅዎ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ፣ እንዴት ፍቅሩን መቀበል እንደሚቸገሩ በግልጽ ይንገሩት። ለእርስዎ ያለውን ፍቅር ለማመን የሚያስፈልግዎትንም ነገር ይንገሩት።

Day 24Day 26

About this Plan

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More