BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample
የእውነተኛ ፍቅር የመጨረሻ መመዘኛ አይኑን እንኳን ማያት ለማይፈልጉት ሰው የሚሰጡት ምላሽ እንደሆነ ኢየሱስ የተናገረ ሲሆን፤ ቃል በቃል ያለው “ጠላቶቻችሁን ውደዱ በምላሹም ምንም ሳትጠብቁ መልካም አድርጉላቸው” ነው። ለኢየሱስ ይህ አይነቱ ፍቅር የእግዚአብሔርን ባህርይ ያንጸባርቃል።
ያንብቡ፦
ሉቃስ 6÷27-36
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
ምን ያስተውላሉ? በሚያነቡበት ጊዜ ምን አይነት ጥያቄዎች፣ ሀሳቦችና ስሜቶች ተፈጠረብዎት?
እርስዎ ወይም እርስዎ የሚያውቁት ሰው ምንም ምላሽ ሳይጠብቅ ለጠላቱ ፍቅር የሰጡበትን ታሪክ ወይም ገጠመኝ ያስታውሱ ወይም ይናገሩ።
ኢየሱስ በዚህ አይነት መልኩ ሌሎችን ለሚወዱ ሰዎች ምን ቃል ገብቷል (ቁጥር 35ን ይመልከቱ)?
ራሱ እግዚአብሔር ለክፉዎችና ለምስጋና ቢሶች ምን ያህል ደግ እንደሆነ ያስተውሉ። ይህ ስለ እግዚአብሔር ባህርይ ምን ይናገራል? እግዚአብሔር ምስጋና ቢስ እና ክፉ በሆኑ ሰዎች ላይ ክፉ የሚሆንበትን አለም አንድ አፍታ አስቡ። በህይወት የሚተርፍ ሰው ይኖራል?
በቁጥር 36 እግዚአብሔር እንዴት እንደተገለጸ ያስተውሉ። በፍቅርና በምህረት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
የኢየሱስ ቃላት ዛሬ እርስዎን የሚሞግትዎ ወይም የሚያበረታታዎ እንዴት ነው? ዛሬ በተግባር ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉበት አንዱ መንገድ ምንድን ነው?
ንባብዎና ምልከታዎ ወደ ጸሎት እንዲያመራዎ ያድርጉ። ለእግዚአብሔር የምህረት ፍቅር ያለዎትን ምስጋና ይግለጹ። ይህን ፍቅር ከሌሎች የነፈጉበትን መንገድ ለእግዚአብሔር በታማኝነት ይንገሩት። ለበደልዎት ሰዎች ይጸልዩ እንዲሁም እርሱ በሚወድበት አይነት ፍቅር ሌሎችን እንዲወዱ እግዚአብሔር ዘወትር እንዲረዳዎ ይጠይቁ።
Scripture
About this Plan
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More