እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥናሙና
የሁለት እህትማማቾች ታሪክ
ማርታ በጣም ትጉና በባህሪዋ ብዙ ነገር ባንድ ጊዜ መስራት ከሚወዱ ሰዎች ውስጥ ትመደባለች፡፡ ነገሮችን ማከናወን ትወዳለች። ይህ ብቻ አይደለም፣ በአዕምሮዋ እንደሳለችው እንዲሆንላት ትፈልጋለች፡፡ ይህ እንዲፈፀም ጠንክራ እየሰራች ነበር። ግን ነገሮች እየተገጣጠሙ አልነበረም፡፡ የሳለችው አልመጣላትም። እናም ጥፋተኛ የምታደርገውን ሰው መፈለግ ጀመረች፤ የዕለቱ ዕጩዎች - ማርያምና ራሱ ኢየሱስ ነበሩ።
እንደዚህ ተሰምቷቹ ያውቃል? “ሕይወቴ እንዲህ ይመስላል ብዬ አልጠበቅሁም” ወይም “______ ን በዚህ መልክ አልሳልኩትም” (ዳሹን ሙሉት) ብላችሁ ታውቃላችሁ? ግን ካልተጠነቀቅን እንደ ማርታ በጣም እንጨነቃለን፣ እንዋከባለን እናም ሕይወታችን እየሄደ በሚመስልበት ቦታ ላይ ትኩረታችን ይያዝና በዚያች ሰዓት ፊታችን ያለው ውበት ያመልጠናል፡፡
“ጭንቀት” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የመጣው ከ16ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን ቃል ሲሆን ይህም ቃል ትርጉሙ “ማነቅ” ነው፡፡ እና “መዋከብ” (የ15ኛ ክፍለ ዘመን ጀርመን ቃል) ደግሞ “እንደ ጀልባ መገልበጥ” ማለት ነው፡፡ ጀልባዋ (ሕይወታችን) እንዳይገለበጥ የምንፈልግ ከሆነ ሸክሙን ለማቃለል ወደ ባህር የሚጣሉትን መምረጥ አለብን፡፡
ኢየሱስ ስለ ምርጫ ይናገራል፡፡ ቁጭ ብሎ ማዳመጥ እንደ አንድ ምርጫ። ቁጭ ብለን ማዳመጥን መምረጥ እንችላለን፡፡ ወይም መሮጥና መዋከብን መምረጥ እንችላለን፡፡ ኢየሱስ ማርታን የቀድሞ ምኞቶቿን ባዶ ማድረግ እንድትመርጥ ኢየሱስ እየጠየቃት ነው። ቁጭ ብሎ ማዳመጥ “ራስን” ባዶ ማድረግ ይጠይቃል። ግን “ጊዜ የለኝም!” ትላላችሁ፡፡ ምናልባትም ይህን የምንለው በሕይወጣችን በጣም አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች ይሆናል፡፡ ግን ጊዜ አለን። ነገር ግን የሚጠበቅብን ከጀልባው ላይ የምንጥለውን ነገር መምረጥ ብቻ ነው! ራሳችንን ባዶ ስናደርግ ቁጭ ብለን ለማዳመጥ ጊዜ ይኖረናል፡፡
ማርታ በጣም ከመዋከቧ የተነሳ እርሷ ያጋጠማትን ትልቅ ስኬት እሱም የኢየሱስ በቤቷ መገኘትን ማየት አልቻለችም፡፡ እጅ መስጠት ምን ይጠይቃል? ምርጫ! ማርያም የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፡፡ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ዳግም ለማስጀመርና ለመምረጥ ጊዜው አሁን ነው!
የሕይወት ተዛምዶ
የምታመሰግኑባቸውን ርዕሶች፣ ከጀልባው ላይ የምትጥሉትን ነገሮችና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ዝርዝር መዝግቡ፡፡
ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ እንደ ማርያም ውበትህን ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ተራ እስኪሆንብኝ ድረስ ባንተ የፍቅር እይታ ውስጥ መማረክ እፈልጋለሁ።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በዚህ የ6 ቀን ጥናት ውስጥ ፍርሃት፣ ግራ መጋባትና ጭንቀትን ለማስወገድ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር መኖር ምን ያህል ማድረግ እንደሚችል እናያለን። ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በማሳለፍና ከቃሉ በመማር እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል፣ ትኩረታችንን እንዴት እንደምናስተካክልና አስተሳሰባችንን እንደምንለውጥ እናያለን።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://www.bezachurch.org |