እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥናሙና
አስተርጓሚው
በመጀመሪያ ልናስተውል የሚገባው ነገር እግዚአብሔር ይህንን ትእዛዝ ለኢያሱ የሰጠበት ቦታ የት እንደሆነ ነው፡፡ ኢያሱ በምድረ በዳ መሃል አይደለም፣ ነገር ግን ኢያሱ (ከእስራኤል ጋር) ያለው በተስፋይቱ ምድር ደጃፍ ላይ ነው፡፡ ትኩረቴን የሳበው ነገር ቢኖር የተስፋውና የፍርሃቱ ቅርበት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የገባላቸው ቃል ወሰን መልከዓ-ምድራዊ ብቻ ሳይሆን ሥነ-ልቦናዊም ነበር፡፡
“እነዚህም ስለ ሰለሏት ምድር በእስራኤላውያን መካከል እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አሠራጩ፤ ‘ያየናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ግዙፎች ናቸው፤’” ዘኁልቍ 13:32
ሰላዮቹ ምድሪቱን በተመለከተ ከአርባ ዓመት ቀደም ብለው ለእስራኤላውያኑ የሰጧቸው ዘገባ ይህ ነው፡፡ እነርሱ ግን የተፋጠጡት ከግዙፍ ሰዎቹ ጋር ሳይሆን ከፍርሃት ጋር ነበር! ፍርሃት በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች ላይ ተመሥርቶ የራሱን ትርጓሜዎች የሚመግብህ መንፈስ ነው፤ የምን “ሊሆን” ይችላልና ምን “ሊመጣ” ይችላል ትርጓሜዎች። መረጃው እውነት ቢሆንም (ግዙፍ ሰዎች ነበሩ) ትርጓሜው ውሸት ነበር!
ፍርሃት በዓይናችን (እና በስሜታችን) ምስክርነት ላይ የተመሠረተ ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል በመንፈሳችን ውስጥ በእግዚአብሔር ቃል ምስክርነት ላይ የተመሠረተ ነው! በዙሪያቹ ያሉትን ክስተቶች የምትተረጉሙት ከየትኛው የመመልከቻ መነፅር አንፃር ነው? የትኛው እንዲያንቀሳቅሳችሁ ትመርጣላችሁ?
እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳይፈራ ወይም ልቡ እንዳይዝል አዞታል፡፡ እግዚአብሔር ልቤ እንዳይዝል ወይም እንዳልፈራ የሚያዘኝ ከሆነ ፍርሃት ምርጫ ነው ማለት ነው! የፍርሃት መሰማት ሁልጊዜ የታሰበ ውሳኔ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ለፍርሃት መልስ መስጠት ግን በእርግጠኝነት ምርጫ ነው!
በመጨረሻም፣ እግዚአብሔር ለኢያሱ የሰጠው አማራጭ ምስክርነት ይህ ነበር - እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፡፡ ትልቁ ስጦታ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ነገሮች ላይ ሳይሆን ግን ይልቁን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የመሆኑ መገለጥ ነው! ከፊታችሁ ያለው ምንም ይሁን፣ ከእናንተ ጋር ባለው በእርሱ ተማምናችሁ ተራመዱ!
የሕይወት ተዛምዶ
አሁን እያጋጠማችሁ ባሉ ሁኔታዎች ላይ የእግዚአብሔር ቃል ምስክርነትን ይፈልጉ! ቃሉ ትክክለኛውን ትርጓሜ ይስጣችሁ፡፡
ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ አሁን በልቤ ተስፋዎችህን ትከል! ልቤን በአንተ አብሮነት ድፍረት ሙላው!
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በዚህ የ6 ቀን ጥናት ውስጥ ፍርሃት፣ ግራ መጋባትና ጭንቀትን ለማስወገድ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር መኖር ምን ያህል ማድረግ እንደሚችል እናያለን። ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በማሳለፍና ከቃሉ በመማር እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል፣ ትኩረታችንን እንዴት እንደምናስተካክልና አስተሳሰባችንን እንደምንለውጥ እናያለን።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://www.bezachurch.org |