የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥናሙና

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ

ቀን {{ቀን}} ከ6

በአንዳች አትጨነቁ

ጭንቀት ለሰው ልጅ ባዕድ አይደለም።  አማኝ መሆን ከጭንቀት ጋር ከመፋለም ነፃ አያደርገንም። ከላይ የተጠቀሰው ምንባብ ለማያምኑ ሰዎች የተጻፈ አይደለም፣ ይልቁንም ጳውሎስ የጻፈው ለፊልጵስዩስ ቤተክርስቲያን ነው። በሌላ አገላለጽ፣ እኛ በዚህ ውጊያ ብቻችንን አይደለንም እንዲሁም ጭንቀትን ብቻችንን አናሸንፍም።

በመጀመሪያ ጭንቀትን ለማሸነፍ የጦርነቱን ሜዳ ማወቅ አለባችሁ። በራሳችሁ አዕምሮ ጭንቀትን ማሸነፍ አይችሉም። በሌላ አገላለጽ ከጭንቀታችሁ በማሰብ መውጣት አይችሉም። በአዕምሮአቹ ውስጥ ብዙ ጊዜ በሰጣችሁት መጠን እንዲያውም የበለጠ የመጨነቃችሁ ዕድል እየሰፋ ይመጣል። በሚያስጨንቃችሁ ጉዳይ ላይ ባሰላሰላችሁት መጠን ጭንቀታችሁ ስር እየሰደደ ይመጣል።

ስለዚህ በመጀመሪያ የጭንቀታችሁ ምክኒያት የሆነውን ነገር ከአዕምሮአችሁ አውጡና በፀሎት ወደ እግዚአብሔር ውሰዱት! ስለሁኔታው ከራሳችሁ ጋር ማውራት አቁሙና ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጀምሩ! እናም ከእግዚአብሔር ጋር ስትነጋገሩ ስለጉዳዩ በመናገር አትጀምሩ። ከእግዚአብሔር ጋር በአምልኮ መገናኘት ጀምሩ። አምልኮአችሁ ለእግዚአብሔር መገባቱ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ማድረግ ሁኔታን ያሳንሳል፣ እናም የእግዚአብሔርን ፍቅርና ታማኝነት በልባችሁ ያገዝፋል።

በሁለተኛ ደረጃ “ምስጋና”! ምስጋና ስሜት አይደለም፣ ነገር ግን የታሰበበት የእምነት አቋም ነው። ምስጋና ለእግዚአብሔርና ለገዛ ልባችሁ “እግዚአብሔር ሆይ በአንተ እታመናለሁ” ይላል! ወደ እግዚአብሔር ማምጣት ብቻ አይደለም፣ ግን ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር መተው ትችላላችሁ ማለት ነው። ይህ ቁልፍ ነው! ምክንያቱም ብዙዎቻችን ጭንቀታችንን ወደ እግዚአብሔር “ማምጣት” ብንችልም እግዚአብሔርን ጋር “ትተነው” መሄድ ግን ይከብደናል። ስለሆነም ጳውሎስ እንድንጸልይ ብቻ ሳይሆን “በምስጋና” እንድንጸልይ ያዘዘው ለዚህ ነው! ምስጋና ልባችንን ወደ ምናምንበት አቅጣጫ ያቀናዋል። እግዚአብሔር በእጁ እንደያዘው እንድናምን። ድሉ ሊገኝና ሊፈጸም የሚችልበት ብቸኛ ቦታ በእግዚአብሔር እጅ ነው።

የሕይወት ተዛምዶ
1.    በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማምለክ ጊዜ መመደባችሁን አረጋግጡ።
2.    ልመናችሁን በእምነት ወደ እግዚአብሔር አምጡ። ኢየሱስ ሸክማችሁን እንደጠየቀ አስታውሱ። ወደ እርሱ ለመምጣት በሚያስችል ልክ  እንድታምኑት ይፈልጋል።
3.    ሸክማችሁን በእምነት አምጥታችሁ ሸክማችሁን በምስጋና ትታችሁ ሂዱ።

ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ እጆችህ ከሃሳቦቼ ስለሚበልጡ አመሰግንሃለሁ። አሁን አምንሃለሁ እናም ጭንቀቴን (ቶቼን) በእጅህ እተዋቸዋለሁ።

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 3ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ

በዚህ የ6 ቀን ጥናት ውስጥ ፍርሃት፣ ግራ መጋባትና ጭንቀትን ለማስወገድ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር መኖር ምን ያህል ማድረግ እንደሚችል እናያለን። ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በማሳለፍና ከቃሉ በመማር እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል፣ ትኩረታችንን እንዴት እንደምናስተካክልና አስተሳሰባችንን እንደምንለውጥ እናያለን።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://www.bezachurch.org