የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥናሙና

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ

ቀን {{ቀን}} ከ6

ሁሉም ነገር…በሕብረት

በሉቃስ 24፡13 ከኢየሱስ መቀብር በኋላ ሁለቱ የእርሱ ደቀመዛሙርት ኤማሁስ ወደሚባል ከተማ እየሄዱ የሆነውንና እየሆነ ያለውን ለመረዳት ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ግራ የተጋቡ ይመስላሉ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ኢየሱስ ራሱ ተቀላቅሏቸው ስለምን እንደሚያወሩ ጠየቃቸው፡፡ በዚያን ጊዜ በሁሉም ነገር የተዳከሙ ይመስላል፣ ‹‹እነርሱም በሀዘን ክው ብለው ቆሙ›› ይላል:: የሆነውንና እየሆነ ያለውን ነገር ለእርሱ ከመናገራቸው በፊት ጊዜ መውሰድና አቅም ማሰባሰብ ያለባቸው ይመስላል፡፡ በሰዓቱ አብሯቸው የነበረው ኢየሱስ መሆኑን ለማወቅ ዓይናቸው ተይዞ ነበር፡፡ ይሰማቸው የነበረው ድካም እና ግራ መጋባት ይሁን አብሯቸው የነበረው ኢየሱስ መሆኑን ከማወቅ/ከማስተዋል የከለከላቸው?

ነገር ግን ከኢየሱስ ጋር አብረው ተቀመጡና እንጀራ ሲቆርሱ በድንገት ዓይናቸው ተከፈተና ኢየሱስን አወቁት፡፡ የተፈጠረውንና የሚፈጠረውን ነገር ለመሸከምና ለመረዳት በሚሞክሩበት ጊዜ አብሯቸው ኢየሱስ እንደነበር አስተዋሉ፡፡ ሕብረት ወደ መገለጥ መራቸው፡፡ ዛሬ እያለፍንበት ባለንበት መንገድና እየተፈጠረ ባለው ነገር ሁሉ ኢየሱስ አብሮን አለ፡፡ እየሆነ ባለው ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ በእርግጥ ወደ ድካም፣ ግራ መጋባት፣ ቁጣና ሀዘን ይመራናል፡፡ ነገር ግን ሕብረት ማድረግ የሁሉም ነገር መልስ ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ይመራናል፡፡

ዳዊት በዙሪያው ያለውን ክፋት ካስተዋለ በኋላ በመዝሙረ ዳዊት  73፡16-17 ‹ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣ አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ።  ይኸውም ወደ አምላክ መቅደስ እስክገባ፣ መጨረሻቸውንም እስካይ ድረስ ነበር።

የሕይወት ተዛምዶ
እንደ ዳዊት ሁሉንም ነገር በራሳችን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ህብረት ውስጥ እንረዳ፡፡

ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ ህብረትን እንድመርጥ እና ዛሬ እየሆነ ያለውን ነገር ሁሉ እንድረዳ ያንተን መረዳት ስጠኝ፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ

በዚህ የ6 ቀን ጥናት ውስጥ ፍርሃት፣ ግራ መጋባትና ጭንቀትን ለማስወገድ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር መኖር ምን ያህል ማድረግ እንደሚችል እናያለን። ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በማሳለፍና ከቃሉ በመማር እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል፣ ትኩረታችንን እንዴት እንደምናስተካክልና አስተሳሰባችንን እንደምንለውጥ እናያለን።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://www.bezachurch.org