መዝሙር 102:1-5
መዝሙር 102:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤ ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል። ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤ እህል መብላትም ዘንግቻለሁ። ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣ ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋራ ተጣበቀ።
Share
መዝሙር 102 ያንብቡመዝሙር 102:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴ፥ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች። አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን። ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትረሳም። ኀጢአትህን ሁሉ ይቅር የሚልልህ፤ ደዌህንም ሁሉ የሚፈውስህ፥ ሕይወትህን ከጥፋት የሚያድናት፥ በይቅርታውና በምሕረቱ የሚከልልህ፥ ምኞትህን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጐልማስነትህን እንደ ንስር የሚያድሳት፥
Share
መዝሙር 102 ያንብቡ