የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 102:1-5

መዝሙረ ዳዊት 102:1-5 መቅካእኤ

አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ተቃጥለዋልና። ልቤም እንደ ተመታ ሣር ደረቀ፤ እህል መብላትም ተረሳኝ።