መዝሙረ ዳዊት 102
102
የዳዊት መዝሙር።
1ነፍሴ፥ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች።
አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን።
2ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፥
ምስጋናውንም ሁሉ አትረሳም።
3ኀጢአትህን ሁሉ ይቅር የሚልልህ፤
ደዌህንም ሁሉ የሚፈውስህ፥
4ሕይወትህን ከጥፋት የሚያድናት፥
በይቅርታውና በምሕረቱ የሚከልልህ፥
5ምኞትህን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥
ጐልማስነትህን እንደ ንስር የሚያድሳት፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. መዝ. 102 ከቍ. 1 እስከ 5 በቅርብ በነጠላ ቍጥር አንስታይ ነው።
6እግዝአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤
ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
7ለሙሴ መንገዱን አሳየ፥
ለእስራኤል ልጆችም ፈቃዱን።
8እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥
ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ ጻድቅ#“ጻድቅ” የሚለው በግእዝ ብቻ። ነው።
9ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥
ለዘለዓለምም አይቈጣም።
10እንደ ኀጢአታችን አላደረገብንም፥
እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
11ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥
እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጸና።
12ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥
እንዲሁ ኀጢአታችንን ከእኛ አራቀ።
13አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፥
እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራላቸዋል፤
14ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤
አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።
15ሰውስ በዘመኑ እንደ ሣር ነው፤
እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤
16ነፍሱ ከእርሱ ይወጣልና፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና” ይላል።
ከእንግዲህም ወዲህ አይኖርምና
ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና።
17የእግዚአብሔር ይቅርታው ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥
ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤
18ሕጉን በሚጠብቁ፥
ትእዛዙንም ያደርጉ ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው።
19እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥
በመንግሥቱም ሁሉን ይገዛል።
20ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኀያላን፥
የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥
እግዚአብሔርን አመስግኑት፤
21ሠራዊቱ ሁሉ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. በቅርብ ነው።
ፈቃዱን የሚያደርጉ አገልጋዮቹ፥
እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል።
22ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ስፍራ ሁሉ፥
እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል።
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 102: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ