የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 102:1-5

መጽሐፈ መዝሙር 102:1-5 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! የአንተን ርዳታ በመፈለግ ስጮኽም አድምጠኝ! መከራ በሚደርስብኝ ጊዜ ከእኔ አትለይ! አድምጠኝ፤ በምጣራበትም ጊዜ ፈጥነህ ስማኝ! የሕይወት ዘመኔ እንደ ጢስ እየበነነ በማለቅ ላይ ነው፤ ሰውነቴም እንደ እሳት እየነደደ ነው። እንደ ደረቀ ሣር ተሰባብሬ ደቀቅሁ፤ የምግብ ፍላጎቴም ጠፋ። ድምፄን ከፍ አድርጌ በመቃተቴ ከቈዳና ከአጥንት በቀር ሰውነት የለኝም።