ሉቃስ 9:28-56

ሉቃስ 9:28-56 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ሊጸልይ ወደ አንድ ተራራ ወጣ። በመጸለይ ላይ እንዳለም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም እጅግ የሚያንጸባርቅ ሆነ። እነሆም፤ ሁለት ሰዎች፣ እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከኢየሱስ ጋራ ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ይፈጸም ዘንድ ስላለው ከዚህ ዓለም ስለ መለየቱ ይናገሩ ነበር። ጴጥሮስና ዐብረውት የነበሩት ግን እንቅልፍ ተጭኗቸው ነበር፤ ሲነቁ ግን ክብሩንና ከርሱ ጋራ የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ። ሰዎቹም ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ እዚህ ብንሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤ አንዱ ለአንተ፣ አንዱ ለሙሴ፣ አንዱም ለኤልያስ ይሆናል” አለው፤ የሚናገረውንም አያውቅም ነበር። ይህንም እየተናገረ ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ፈሩ። ከደመናውም ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ። ድምፁም በተሰማ ጊዜ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ፤ ደቀ መዛሙርቱም ነገሩን በልባቸው ያዙ እንጂ ስላዩት ነገር በዚያ ወቅት ለማንም አልተናገሩም። በማግስቱም ከተራራው ከወረዱ በኋላ፣ ብዙ ሕዝብ መጥቶ ኢየሱስን አገኘው። በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “መምህር ሆይ፤ ያለኝ ልጅ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ። መንፈስ ሲይዘው በድንገት ይጮኻል፤ ዐረፋ እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ ጕዳትም ካደረሰበት በኋላ በስንት መከራ ይተወዋል፤ ደቀ መዛሙርትህ እንዲያወጡለት ለመንኋቸው፤ ነገር ግን አልቻሉም።” ኢየሱስም “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው!” አለ። ልጁ በመምጣት ላይ ሳለም ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ልጁን ፈወሰው፤ ለአባቱም መልሶ ሰጠው። ሰዎቹም ሁሉ በእግዚአብሔር ታላቅነት ተገረሙ። እርሱ ባደረገው ሁሉ ሰዎች ሁሉ እየተገረሙ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ይህን የምነግራችሁን ነገር ልብ በሉ፤ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ዐልፎ ይሰጣልና” አለ። እነርሱ ግን ይህን አባባል አልተረዱም፤ እንዳያስተውሉ ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ነገር መልሰው እንዳይጠይቁትም ፈሩ። ከእነርሱ ማን እንደሚበልጥ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ክርክር ተነሣ። ኢየሱስም የልባቸውን ሐሳብ ተረድቶ፣ አንድ ሕፃን ይዞ በአጠገቡ አቆመ፤ እንዲህም አላቸው፤ “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ማንም ቢኖር እኔን ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ደግሞ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ከሁሉ ይበልጣልና።” ዮሐንስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፤ ከእኛ ጋራ ሆኖ ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው። ኢየሱስም፣ “አትከልክሉት፤ የማይቃወማችሁ ሁሉ እርሱ ከእናንተ ጋራ ነውና” አለው። ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሚያርግበት ጊዜ በመቃረቡ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ፤ አስቀድሞም መልእክተኞችን ወደዚያ ላከ። እነርሱም ሁኔታዎችን አስቀድመው ሊያመቻቹለት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ። ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም እያመራ መሆኑን ስላወቁ አልተቀበሉትም። ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ሲያዩ፣ “ጌታ ሆይ፤ ኤልያስ እንዳደረገው ሁሉ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት። ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፣ እርሱና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

ሉቃስ 9:28-56 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር። ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ። ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር። ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ። ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም። በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት። እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ መምህር ሆይ፥ ለእኔ አንድ ልጅ ነውና ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ። እነሆም፥ ጋኔን ይይዘዋል፥ ድንገትም ይጮኻል አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፥ እየቀጠቀጠም በጭንቅ ይለቀዋል፤ ደቀ መዛሙርትህንም እንዲያወጡት ለመንሁ፥ አልቻሉምም። ኢየሱስም መልሶ፦ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው አለ። ሲቀርብም ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኵሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው ለአባቱም መለሰው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ፥ ለደቀ መዛሙርቱ፦ የሰው ልጅ በሰው እጅ ይሰጥ ዘንድ አለውና እናንተ ይህን ቃል በጆሮአችሁ አኑሩ አለ። እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፥ እንዳይገባቸውም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ነገርም እንዳይጠይቁት ፈሩ። ከእነርሱም ማን እንዲበልጥ ክርክር ተነሣባቸው። ኢየሱስም የልባቸውን አሳብ አውቆ ሕፃንን ያዘ፤ በአጠገቡም አቁሞ፦ ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና አላቸው። ዮሐንስም መልሶ፦ አቤቱ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ ከእኛ ጋርም ስለማይከተል ከለከልነው አለው። ኢየሱስ ግን፦ የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነውና አትከልክሉት አለው። የሚወጣበትም ወራት በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና፥ በፊቱም መልክተኞችን ሰደደ። ሄደውም ሊያሰናዱለት ወደ አንድ ወደ ሳምራውያን መንደር ገቡ፤ ፊቱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ስለ ነበረ አልተቀበሉትም። ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? አሉት። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፦ ምን ዓይነት መንፈስ እንደ ሆነላችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ። ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

ሉቃስ 9:28-56 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከዚ​ህም ነገር በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ጴጥ​ሮ​ስን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዮሐ​ን​ስን ይዞ​አ​ቸው ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ። ሲጸ​ል​ይም የፊቱ መልክ ተለ​ወጠ፤ ልብ​ሱም ነጭ ሆነ፤ እንደ መብ​ረ​ቅም አብ​ለ​ጨ​ለጨ። እነ​ሆም፥ ሁለት ሰዎች መጥ​ተው ከእ​ርሱ ጋር ይነ​ጋ​ገሩ ነበር። እነ​ር​ሱም ሙሴና ኤል​ያስ ነበሩ። በክ​ብ​ርም ተገ​ል​ጠው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይደ​ረግ ዘንድ ያለ​ውን ክብ​ሩ​ንና መው​ጣ​ቱን ተና​ገሩ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ት​ንም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው በእ​ን​ቅ​ልፍ ፈዝ​ዘው አገኘ፤ በነ​ቁም ጊዜ ክብ​ሩ​ንና ከእ​ርሱ ጋር ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት ሰዎች አዩ። ከዚ​ህም በኋላ ከእ​ርሱ ሲለዩ ጴጥ​ሮስ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “መም​ህር፥ ሆይ፥ እዚህ ብን​ኖር ለእኛ መል​ካም ነው፤ ሦስት ሰቀ​ላ​ዎ​ች​ንም እን​ሥራ፤ አን​ዱን ለአ​ንተ፥ አን​ዱ​ንም ለሙሴ፥ አን​ዱ​ንም ለኤ​ል​ያስ” አለው፤ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቅም ነበር። ይህ​ንም ሲና​ገር ደመና መጣና ጋረ​ዳ​ቸው፤ ወደ ደመ​ና​ውም በገቡ ጊዜ ፈሩ። ከደ​መ​ና​ውም ውስጥ፥ “የመ​ረ​ጥ​ሁት ልጄ ይህ ነው፤ እር​ሱን ስሙት” የሚል ቃል መጣ። ቃሉም ከመጣ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ብቻ​ውን ተገኘ፤ እነ​ርሱ ግን ዝም አሉ፤ ያዩ​ት​ንና የሰ​ሙ​ት​ንም በዚያ ጊዜ ለማ​ንም አል​ተ​ና​ገ​ሩም። በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ራ​ራው ወረዱ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ተቀ​በ​ሉት። አንድ ሰውም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጮኾ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ እርሱ ለእኔ አንድ ነውና ልጄን ታይ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ። እነሆ፥ ጋኔን ሊነ​ጥ​ቀኝ ነው፤ ድን​ገ​ትም ያስ​ጮ​ኸ​ዋል፤ ጥሎም ያፈ​ራ​ግ​ጠ​ዋል፤ አረ​ፋም ያስ​ደ​ፍ​ቀ​ዋል፤ ቀጥ​ቅጦ በጭ​ንቅ ይተ​ወ​ዋል። እን​ዲ​ያ​ወ​ጡ​ትም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ለመ​ን​ሁ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ማው​ጣት ተሳ​ና​ቸው።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “የማ​ታ​ምን ከዳ​ተኛ ትው​ልድ፥ እስከ መቼ ከእ​ና​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼስ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ? ልጅ​ህን ወደ​ዚህ አም​ጣው” አለው። ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ። እነ​ር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ባደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ሁሉ ሲደ​ነቁ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው። “እና​ን​ተስ ይህን ነገር በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት፤ የሰው ልጅ በሰ​ዎች እጅ ተላ​ልፎ ይሰጥ ዘንድ አለ​ውና።” እነ​ርሱ ግን ይህን ነገር አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ እን​ዳ​ይ​መ​ረ​ም​ሩት ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነውና፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም እን​ዳ​ይ​ጠ​ይ​ቁት ይፈ​ሩት ነበ​ርና። እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ማን እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ ዐሰቡ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በል​ቡ​ና​ቸው የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና አንድ ሕፃን ወስዶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አቆ​መው። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በስሜ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሕፃን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፥ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል፤ ራሱን ከሁሉ ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ርግ እርሱ ታላቅ ይሆ​ናል።” ዮሐ​ን​ስም መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ በስ​ምህ ጋኔን ሲያ​ወጣ ያየ​ነው አንድ ሰው አለ፤ ከእ​ኛም ጋር አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ህ​ምና ከለ​ከ​ል​ነው፤” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ከ​ል​ክ​ሉት፤ ባለ​ጋ​ራ​ችሁ ካል​ሆነ ባል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ነውና” አላ​ቸው። የመ​ው​ጣቱ ወራ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሄድ ፊቱን አቀና። በፊ​ቱም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ሄደ​ውም ያዘ​ጋ​ጁ​ለት ዘንድ ወደ ሰማ​ርያ ከተማ ገቡ። ነገር ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም፤ ፊቱን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅ​ንቶ ነበ​ርና። ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ን​ስም ይህን ባዩ ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ኤል​ያስ እንደ አደ​ረገ እሳት ከሰ​ማይ ወርዶ ያጥ​ፋ​ቸው እን​ድ​ንል ትፈ​ቅ​ዳ​ለ​ህን?” አሉት። እርሱ ግን ዘወር ብሎ፥ “ከምን መን​ፈስ እንደ ሆና​ችሁ አታ​ው​ቁም” ብሎ ገሠ​ጻ​ቸው። የሰው ልጅ የሰ​ውን ነፍስ ሊያ​ድን እንጂ ሊያ​ጠፋ አል​መ​ጣም። ወደ ሌላም መን​ደር ሄዱ።

ሉቃስ 9:28-56 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ሊጸልይ ወደ አንድ ተራራ ወጣ። በመጸለይ ላይ እንዳለም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም እጅግ የሚያንጸባርቅ ሆነ። እነሆም፤ ሁለት ሰዎች፣ እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከኢየሱስ ጋራ ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ይፈጸም ዘንድ ስላለው ከዚህ ዓለም ስለ መለየቱ ይናገሩ ነበር። ጴጥሮስና ዐብረውት የነበሩት ግን እንቅልፍ ተጭኗቸው ነበር፤ ሲነቁ ግን ክብሩንና ከርሱ ጋራ የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ። ሰዎቹም ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ እዚህ ብንሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤ አንዱ ለአንተ፣ አንዱ ለሙሴ፣ አንዱም ለኤልያስ ይሆናል” አለው፤ የሚናገረውንም አያውቅም ነበር። ይህንም እየተናገረ ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ፈሩ። ከደመናውም ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ። ድምፁም በተሰማ ጊዜ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ፤ ደቀ መዛሙርቱም ነገሩን በልባቸው ያዙ እንጂ ስላዩት ነገር በዚያ ወቅት ለማንም አልተናገሩም። በማግስቱም ከተራራው ከወረዱ በኋላ፣ ብዙ ሕዝብ መጥቶ ኢየሱስን አገኘው። በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “መምህር ሆይ፤ ያለኝ ልጅ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ። መንፈስ ሲይዘው በድንገት ይጮኻል፤ ዐረፋ እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ ጕዳትም ካደረሰበት በኋላ በስንት መከራ ይተወዋል፤ ደቀ መዛሙርትህ እንዲያወጡለት ለመንኋቸው፤ ነገር ግን አልቻሉም።” ኢየሱስም “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው!” አለ። ልጁ በመምጣት ላይ ሳለም ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ልጁን ፈወሰው፤ ለአባቱም መልሶ ሰጠው። ሰዎቹም ሁሉ በእግዚአብሔር ታላቅነት ተገረሙ። እርሱ ባደረገው ሁሉ ሰዎች ሁሉ እየተገረሙ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ይህን የምነግራችሁን ነገር ልብ በሉ፤ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ዐልፎ ይሰጣልና” አለ። እነርሱ ግን ይህን አባባል አልተረዱም፤ እንዳያስተውሉ ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ነገር መልሰው እንዳይጠይቁትም ፈሩ። ከእነርሱ ማን እንደሚበልጥ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ክርክር ተነሣ። ኢየሱስም የልባቸውን ሐሳብ ተረድቶ፣ አንድ ሕፃን ይዞ በአጠገቡ አቆመ፤ እንዲህም አላቸው፤ “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ማንም ቢኖር እኔን ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ደግሞ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ከሁሉ ይበልጣልና።” ዮሐንስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፤ ከእኛ ጋራ ሆኖ ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው። ኢየሱስም፣ “አትከልክሉት፤ የማይቃወማችሁ ሁሉ እርሱ ከእናንተ ጋራ ነውና” አለው። ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሚያርግበት ጊዜ በመቃረቡ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ፤ አስቀድሞም መልእክተኞችን ወደዚያ ላከ። እነርሱም ሁኔታዎችን አስቀድመው ሊያመቻቹለት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ። ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም እያመራ መሆኑን ስላወቁ አልተቀበሉትም። ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ሲያዩ፣ “ጌታ ሆይ፤ ኤልያስ እንዳደረገው ሁሉ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት። ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፣ እርሱና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

ሉቃስ 9:28-56 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር። ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ። ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር። ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ። ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም። በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት። እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ መምህር ሆይ፥ ለእኔ አንድ ልጅ ነውና ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ። እነሆም፥ ጋኔን ይይዘዋል፥ ድንገትም ይጮኻል አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፥ እየቀጠቀጠም በጭንቅ ይለቀዋል፤ ደቀ መዛሙርትህንም እንዲያወጡት ለመንሁ፥ አልቻሉምም። ኢየሱስም መልሶ፦ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው አለ። ሲቀርብም ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኵሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው ለአባቱም መለሰው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ፥ ለደቀ መዛሙርቱ፦ የሰው ልጅ በሰው እጅ ይሰጥ ዘንድ አለውና እናንተ ይህን ቃል በጆሮአችሁ አኑሩ አለ። እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፥ እንዳይገባቸውም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ነገርም እንዳይጠይቁት ፈሩ። ከእነርሱም ማን እንዲበልጥ ክርክር ተነሣባቸው። ኢየሱስም የልባቸውን አሳብ አውቆ ሕፃንን ያዘ፤ በአጠገቡም አቁሞ፦ ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና አላቸው። ዮሐንስም መልሶ፦ አቤቱ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ ከእኛ ጋርም ስለማይከተል ከለከልነው አለው። ኢየሱስ ግን፦ የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነውና አትከልክሉት አለው። የሚወጣበትም ወራት በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና፥ በፊቱም መልክተኞችን ሰደደ። ሄደውም ሊያሰናዱለት ወደ አንድ ወደ ሳምራውያን መንደር ገቡ፤ ፊቱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ስለ ነበረ አልተቀበሉትም። ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? አሉት። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፦ ምን ዓይነት መንፈስ እንደ ሆነላችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ። ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

ሉቃስ 9:28-56 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን በኋላ ጴጥሮስን፥ ዮሐንስንና ያዕቆብን አስከትሎ ለመጸለይ ወደ አንድ ተራራ ላይ ወጣ። በሚጸልይበትም ጊዜ መልኩ ተለወጠ፤ ልብሱም ነጭ ሆኖ አንጸባረቀ፤ እነሆ፥ በድንገት ሁለት ሰዎች መጥተው ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ነበሩ። በክብር ተገልጠው ይነጋገሩ የነበሩትም፥ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም መከራ እንደሚቀበልና እንደሚሞት ነበር። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ጓደኞቹ በእንቅልፍ ተሸንፈው ተኝተው ነበር፤ በነቁ ጊዜ ግን የኢየሱስን ክብርና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች አዩ። ሁለቱ ሰዎች ከኢየሱስ ተለይተው በሄዱ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ አንድ ለአንተ፥ አንድ ለሙሴ፥ አንድ ለኤልያስ የሚሆኑ ሦስት ዳሶች እንሥራ!” አለው፤ ጴጥሮስ ይህን ሲናገር የሚለውን አያውቅም ነበር። ጴጥሮስ ይህን ሲናገር ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ደመናውም በጋረዳቸው ጊዜ ፈሩ። ከደመናውም ውስጥ፥ “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ። ድምፁም ከተሰማ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያዩትን ሁሉ በዚያን ጊዜ ለማንም ሳይናገሩ ዝም አሉ። በማግስቱ ኢየሱስና ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ከተራራው በወረዱ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን ተገናኙት። ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጮኸ! “መምህር ሆይ፥ ይህ ለኔ አንድ ልጅ ነውና እንድታድንልኝ እለምንሃለሁ፤ እነሆ! ርኩስ መንፈስ በድንገት ይዞ ያስጮኸዋል፤ በመሬት ላይ ጥሎ ዐረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ሰውነቱንም እያቈሰለ በአሳር ይለቀዋል። ርኩሱን መንፈስ እንዲያስወጡለት ደቀ መዛሙርትህን ጠይቄአቸው ነበር፤ ነገር ግን አልቻሉም።” ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተ እምነት የሌላችሁ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጅህን ወዲህ አምጣው።” ልጁም ወደ ኢየሱስ በቀረበ ጊዜ ጋኔኑ በመሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሠጸው፤ ልጁንም ፈውሶ ለአባቱ ሰጠው። ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ታላቅ ኀይል በማየታቸው ተገረሙ፤ ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ነገር በመደነቅ ላይ ሳሉ እርሱ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ይህን የምነግራችሁን ቃል ልብ ብላችሁ አስተውሉ! እነሆ፥ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል።” እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፤ የንግግሩም ምሥጢር ተሰውሮባቸው ነበር፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። ደቀ መዛሙርቱ “ከእኛ ከሁላችን የሚበልጥ ማን ነው?” በማለት ክርክር አንሥተው ነበር። ኢየሱስ ግን የልባቸውን ሐሳብ ዐውቆ አንድ ሕፃን ልጅ አመጣና በአጠገቡ አቆመው፤ እርሱም “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝን ይቀበላል። ከእናንተ መካከል ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ይሆናል፤” አላቸው። ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፤ ነገር ግን ከእኛ ጋር ስላልሆነ ከለከልነው፤” አለ። ኢየሱስም “የማይቃወማችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነ ተዉ፤ አትከልክሉት!” አለ። ኢየሱስ የሚያርግበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ። ከእርሱ በፊት ቀድመው የሚሄዱትንም መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ሁሉን ነገር ለማዘጋጀት በሰማርያ ወደምትገኘው ወደ አንዲት መንደር ሄዱ። ነገር ግን እርሱ በዚያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድ መሆኑን ዐውቀው ስለ ነበር የዚያች መንደር ሰዎች ሊቀበሉት አልፈለጉም። ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፥ “ጌታ ሆይ! ከሰማይ እሳት ወርዶ እነዚህን ሰዎች ያቃጥላቸው ዘንድ እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት። ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ መለስ ብሎ ገሠጻቸው። [እናንተ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደ ሆናችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ፥ ለማጥፋት አይደለም።] ከዚያም ተነሥተው ወደ ሌላ መንደር ሄዱ።

ሉቃስ 9:28-56 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢየሱስም እነዚህን ቃላት ከተናገረ በኋላ፥ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ መብረቅ ፀዳል አብረቅርቆ ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሁለት ሰዎች ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ነበሩ፤ በክብርም ተገልጠው በኢየሩሳሌም ሊፈጽመው ስላለ ሞቱ ይናገሩ ነበር። ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ተጫጭኖአቸው ነበር፤ ነቅተውም ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ። ከእርሱም ሁለቱ ሰዎች በተለዩ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ “አቤቱ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ፥ አንድም ለሙሴ፥ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤” አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር። ይህንም ሲናገር ሳለ ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም በገቡ ጊዜ ፈሩ። ከደመናውም፦ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ። ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ቀረ። እነርሱም ዝም አሉ፥ ያዩትንም ምንም ዓይነት ነገር በነዚያ ቀናት ለማንም አላወሩም። በማግስቱም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኘው። እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ “መምህር ሆይ! ለእኔ ብቸኛ ልጄ ነውና፥ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ። እነሆም፥ ርኩስ መንፈስ ይይዘዋል፤ ድንገትም ይጮኻል፤ አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ አድቅቆ በጭንቅ ይለቀዋል፤ ደቀ መዛሙርትህንም እንዲያወጡት ለመንሁ፤ እነርሱ ግን አልቻሉም።” ኢየሱስም መልሶ፦ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው፤” አለ። ልጁም በመምጣት ላይ ሳለ ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው፤ ልጁንም ለአባቱ መልሶ ሰጠው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ ሳሉ፥ እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ፦ “የሰው ልጅ በሰው እጅ ተላልፎ የሚሰጥ ስለሆነ እናንተ እነዚህን ቃላት በጆሮዎቻችሁ አኑሩ፤” አለ። እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፤ እንዳይገባቸውም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህም ነገር እርሱን ለመጠየቅ ፈሩ። ከእነርሱም መካከል ማን እንደሚበልጥ በእነርሱ ዘንድ ክርክር ተነሣ። ኢየሱስም የልባቸውን አሳብ አውቆ አንድ ሕፃን ወሰደና፥ በአጠገቡም አቁሞት፦ “ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን ይቀበላል፤ በእናንተ መካከል ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና፤” አላቸው። ዮሐንስም መልሶ፦ “አቤቱ! አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፤ ከእኛ ጋርም ስለማይከተል ከለከልነው” አለው። ኢየሱስ ግን፦ “የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነውና አትከልክሉት፤” አለው። ኢየሱስ የሚያርግበት ወራት በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና፤ እርሱም አስቀድሞ መልክተኞችን ላከ። ሄደውም ሊያሰናዱለት ወደ አንዲት የሳምራውያን መንደር ገቡ፤ ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ ፊቱን አቅንቶ ስለ ነበረ የመንደሩ ሰዎች አልተቀበሉትም። ደቀመዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ “ጌታ ሆይ! ከሰማይ እሳት ወርዶ እንዲበላቸው እንድናዝዝ ትወዳለህን?” አሉት። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸው። ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።