ዘሌዋውያን 26:27-46

ዘሌዋውያን 26:27-46 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ ‘በዚህ ሁሉ ግን ባትታዘዙኝ፣ በእኔም ላይ ማመፃችሁን ብትቀጥሉ፣ እኔም በቍጣዬ እመጣባችኋለሁ፤ ስለ ኀጢአታችሁም እኔው ራሴ ሰባት ዕጥፍ እቀጣችኋለሁ። የወንዶች ልጆቻችሁን ሥጋና የሴቶች ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ። የኰረብታ መስገጃዎቻችሁን እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በድኖቻችሁን በድን በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። ከተሞቻችሁን አፈራርሳለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም ወና አደርጋለሁ፤ ጣፋጭ ሽታ ያለውን መሥዋዕታችሁንም አልቀበልም። በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ እስኪደነቁ ድረስ፣ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ። በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ሰይፌን መዝዤም አሳድዳችኋለሁ። ምድራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ። ምድሪቱ ባድማ በሆነችበት ጊዜ ሁሉና እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር በምትኖሩበት ወቅት ምድሪቱ በሰንበት ዓመቷ ትደሰታለች፤ ምድሪቱም በሰንበቷ ታርፋለች፤ ትደሰታለችም። ምድሪቱ እናንተ በነበራችሁባት ጊዜ በሰንበት ያላገኘችውን ዕረፍት፣ ባድማ በምትሆንበት ጊዜ ሁሉ ታገኛለች። “ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም። የሚያሳድዳቸው ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት መቆም አትችሉም። በአሕዛብ መካከል ታልቃላችሁ፤ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች። ከእናንተ የተረፉት በጠላቶቻቸው ምድር በራሳቸው ኀጢአትና በአባቶቻቸው ኀጢአት ምክንያት መንምነው ያልቃሉ። “ ‘ነገር ግን ለእኔ ያልታመኑበትንና በእኔም ላይ ያመፁበትን የራሳቸውን ኀጢአትና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣ በዚያ ጊዜ ከያዕቆብ ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ከይሥሐቅም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ደግሞም ከአብርሃም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን ዐስባለሁ፤ ምድሪቱንም ዐስባታለሁ። ምድሪቱ እነርሱ ለቅቀዋት ስለ ሄዱ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱ በሌሉበት ጊዜም ባድማ ሆና በሰንበቷ ትደሰታለች፤ ሕጌን በማቃለላቸውና ሥርዐቴን በመናቃቸው፣ የኀጢአታቸውን ቅጣት ይቀበላሉ። በዚህ ሁሉ ግን ከእነርሱ ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን በማፍረስ፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ፈጽሜ እስካጠፋቸው ድረስ አልተዋቸውም፤ አልጸየፋቸውምም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ። ስለ እነርሱም ስል፣ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው አባቶቻቸው ጋራ የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” እግዚአብሔር በራሱና በእስራኤላውያን መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ በኩል ያቆማቸው ሥርዐቶች፣ ሕጎችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።

ዘሌዋውያን 26:27-46 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ፥ እኔ ደግሞ በቍጣ እሄድባችኋለሁ፤ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፥ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ መልካሙንም መዓዛችሁን አላሸትትም። ምድሪቱንም የተፈታች አደርጋለሁ፤ የሚቀመጡባት ጠላቶቻችሁም በእርስዋ የተነሣ ይደነቃሉ። እናንተም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ። በዚያም በተፈታችበት ዘመን ሁሉ እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር ሳላችሁ፥ ምድሪቱ ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች፤ በዚያም ጊዜ ምድሪቱ ታርፋለች፥ ሰንበትንም በማድረግዋ ትደሰታለች። እናንተ ተቀምጣችሁባት በነበረ ጊዜ በሰንበቶቻችሁ አላረፈችም ነበርና በተፈታችበት ዘመን ሁሉ ታርፋለች። በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ። ማንም ሳያሳድዳቸው ከሰይፍ እንዲሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ እናንተም በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም። በአሕዛብም መካከል ታልቃላችሁ፥ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች። ከእናንተም ተለይተው የቀሩት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይከሳሉ፤ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይከሳሉ። በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም ኃጢአት ይናዘዛሉ። እኔም ደግሞ በእንቢተኝነት ሄድሁባቸው፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አገባኋቸው፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ እኔ ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ደግሞ ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ። ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የኃጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ። ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም። እኔ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸውን የአባቶቻቸውን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። እግዚአብሔርም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ ያደረጋቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።

ዘሌዋውያን 26:27-46 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ አግ​ድ​ማ​ች​ሁም ብት​ሄ​ዱ​ብኝ፥ እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ። የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ። የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በእጅ የተ​ሠሩ የዕ​ን​ጨት ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሬሳ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ሬሳ​ዎች ላይ እጥ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም ትጸ​የ​ፋ​ች​ኋ​ለች። ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም መዓዛ አላ​ሸ​ት​ትም። ምድ​ሪ​ቱ​ንም የተ​ፈ​ታች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ር​ስዋ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ቃሉ። እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ። “በዚ​ያም በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ሁሉ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ምድር ሳላ​ችሁ፥ ምድ​ሪቱ ሰን​በት በማ​ድ​ረ​ግዋ ደስ ይላ​ታል፤ በዚ​ያም ጊዜ ምድ​ሪቱ ታር​ፋ​ለች፤ ስን​በ​ት​ንም በማ​ድ​ረ​ግዋ ደስ ይላ​ታል። እና​ንተ ተቀ​ም​ጣ​ች​ሁ​ባት በነ​በረ ጊዜ በሰ​ን​በ​ቶ​ቻ​ችሁ አላ​ረ​ፈ​ችም ነበ​ርና በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ሁሉ ታር​ፋ​ለች። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤ ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው ከሰ​ይፍ እን​ዲ​ሸሹ እርስ በር​ሳ​ቸው ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላሉ፤ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም። በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ምድር ትው​ጣ​ች​ኋ​ለች። ከእ​ና​ን​ተም ተለ​ይ​ተው የቀ​ሩት ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይጠ​ፋሉ፤ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀጢ​አት ደግሞ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ይቀ​ል​ጣሉ። “እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እን​ዳ​ሉኝ፥ በፊ​ቴም አግ​ድ​መው እንደ ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛሉ። እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤ ያን ጊዜ እኔ ከያ​ዕ​ቆብ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ደግ​ሞም ከይ​ስ​ሐቅ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን፥ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አስ​ባ​ለሁ። ምድ​ርም ከእ​ነ​ርሱ መጥ​ፋት የተ​ነሣ ባዶ ትቀ​ራ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ሳይ​ኖሩ በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ዕረ​ፍት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ፍር​ዴ​ንም ስለ ናቁ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም ሥር​ዐ​ቴን ስለ ተጸ​የ​ፈች የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ቅጣት ይሸ​ከ​ማሉ። ነገር ግን እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ነኝና እነ​ርሱ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ሳሉ፥ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያለ​ኝን ቃል ኪዳን እስ​ካ​ፈ​ርስ ድረስ አል​ጥ​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ጸ​የ​ፋ​ቸ​ው​ምም። እኔ አም​ላ​ካ​ቸው እሆን ዘንድ አሕ​ዛብ እያዩ ከግ​ብፅ ምድር ከግ​ዞት ቤት እን​ዳ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው የቀ​ድሞ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውን ስለ እነ​ርሱ አስ​ባ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ር​ሱና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰ​ጣ​ቸው ሥር​ዐ​ቶ​ችና ፍር​ዶች፥ ሕግ​ጋ​ትም እነ​ዚህ ናቸው።

ዘሌዋውያን 26:27-46 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ ‘በዚህ ሁሉ ግን ባትታዘዙኝ፣ በእኔም ላይ ማመፃችሁን ብትቀጥሉ፣ እኔም በቍጣዬ እመጣባችኋለሁ፤ ስለ ኀጢአታችሁም እኔው ራሴ ሰባት ዕጥፍ እቀጣችኋለሁ። የወንዶች ልጆቻችሁን ሥጋና የሴቶች ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ። የኰረብታ መስገጃዎቻችሁን እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በድኖቻችሁን በድን በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። ከተሞቻችሁን አፈራርሳለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም ወና አደርጋለሁ፤ ጣፋጭ ሽታ ያለውን መሥዋዕታችሁንም አልቀበልም። በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ እስኪደነቁ ድረስ፣ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ። በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ሰይፌን መዝዤም አሳድዳችኋለሁ። ምድራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ። ምድሪቱ ባድማ በሆነችበት ጊዜ ሁሉና እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር በምትኖሩበት ወቅት ምድሪቱ በሰንበት ዓመቷ ትደሰታለች፤ ምድሪቱም በሰንበቷ ታርፋለች፤ ትደሰታለችም። ምድሪቱ እናንተ በነበራችሁባት ጊዜ በሰንበት ያላገኘችውን ዕረፍት፣ ባድማ በምትሆንበት ጊዜ ሁሉ ታገኛለች። “ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም። የሚያሳድዳቸው ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት መቆም አትችሉም። በአሕዛብ መካከል ታልቃላችሁ፤ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች። ከእናንተ የተረፉት በጠላቶቻቸው ምድር በራሳቸው ኀጢአትና በአባቶቻቸው ኀጢአት ምክንያት መንምነው ያልቃሉ። “ ‘ነገር ግን ለእኔ ያልታመኑበትንና በእኔም ላይ ያመፁበትን የራሳቸውን ኀጢአትና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣ በዚያ ጊዜ ከያዕቆብ ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ከይሥሐቅም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ደግሞም ከአብርሃም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን ዐስባለሁ፤ ምድሪቱንም ዐስባታለሁ። ምድሪቱ እነርሱ ለቅቀዋት ስለ ሄዱ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱ በሌሉበት ጊዜም ባድማ ሆና በሰንበቷ ትደሰታለች፤ ሕጌን በማቃለላቸውና ሥርዐቴን በመናቃቸው፣ የኀጢአታቸውን ቅጣት ይቀበላሉ። በዚህ ሁሉ ግን ከእነርሱ ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን በማፍረስ፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ፈጽሜ እስካጠፋቸው ድረስ አልተዋቸውም፤ አልጸየፋቸውምም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ። ስለ እነርሱም ስል፣ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው አባቶቻቸው ጋራ የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” እግዚአብሔር በራሱና በእስራኤላውያን መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ በኩል ያቆማቸው ሥርዐቶች፣ ሕጎችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።

ዘሌዋውያን 26:27-46 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ፥ እኔ ደግሞ በቍጣ እሄድባችኋለሁ፤ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፥ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ መልካሙንም መዓዛችሁን አላሸትትም። ምድሪቱንም የተፈታች አደርጋለሁ፤ የሚቀመጡባት ጠላቶቻችሁም በእርስዋ የተነሣ ይደነቃሉ። እናንተም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ። በዚያም በተፈታችበት ዘመን ሁሉ እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር ሳላችሁ፥ ምድሪቱ ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች፤ በዚያም ጊዜ ምድሪቱ ታርፋለች፥ ሰንበትንም በማድረግዋ ትደሰታለች። እናንተ ተቀምጣችሁባት በነበረ ጊዜ በሰንበቶቻችሁ አላረፈችም ነበርና በተፈታችበት ዘመን ሁሉ ታርፋለች። በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ። ማንም ሳያሳድዳቸው ከሰይፍ እንዲሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ እናንተም በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም። በአሕዛብም መካከል ታልቃላችሁ፥ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች። ከእናንተም ተለይተው የቀሩት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይከሳሉ፤ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይከሳሉ። በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም ኃጢአት ይናዘዛሉ። እኔም ደግሞ በእንቢተኝነት ሄድሁባቸው፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አገባኋቸው፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ እኔ ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ደግሞ ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ። ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የኃጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ። ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም። እኔ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸውን የአባቶቻቸውን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። እግዚአብሔርም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ ያደረጋቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።

ዘሌዋውያን 26:27-46 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“ይህም ሁሉ ተፈጽሞባችሁ እኔን መቃወም ብትቀጥሉና ለእኔም ባትታዘዙ፥ በእናንተ ላይ በቊጣ እነሣለሁ፤ በእናንተ ላይ የማመጣውንም ቅጣት ካለፈው ሰባት ጊዜ የበለጠ እንዲሆን አደርጋለሁ። ስለዚህም ከመራባችሁ ጽናት የተነሣ የገዛ ልጆቻችሁን ለመብላት ትገደዳላችሁ። በየኰረብታው ላይ ያሉአችሁን መስገጃዎች እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈራርሳለሁ፤ ሬሳዎቻችሁንም በወደቁት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ፈጽሞ እጸየፋችኋለሁ፤ ከተሞቻችሁንም ውድማ አደርጋለሁ የማምለኪያ ስፍራዎቻችሁንም አፈራርሳለሁ መሥዋዕታችሁንም አልቀበልም። ምድራችሁን ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ በወረራ የያዛትም ጠላት ጥፋትዋን አይቶ በፍርሃት ይንቀጠቀጣል። በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤ እናንተ በጠላቶቻችሁ አገር በምትኖሩባቸው ዓመቶች ሁሉ ምድራችሁ ባዶ ስለምትሆን ሰንበቶችን ታከብራለች፤ ከዚያ በኋላ ምድሪቱ ዕረፍት አድርጋ በሰንበቶች ትደሰታለች። እናንተ በነበራችሁባት ጊዜ በሰንበቶቻችሁ ያላገኘችውን ዕረፍት አሁን ሰው አልባ በሆነችበት ጊዜ ዐረፈች። “ከስደት የቀሩት ሁሉ ነፋስ የሚነካውን የቅጠል ኮሽታ በሰሙ ቊጥር በድንጋጤ በርግገው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ በጦርነት ላይ ልክ ጠላት እንደሚያሳድዳቸው ያኽል ሆነው ይሸሻሉ፤ ምንም ዐይነት ጠላት በአጠገባቸው ሳይኖር ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ከጠላት እንደሚሸሹ ሆነው አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ተሰነካክለው ይወድቃሉ፤ ማንኛውንም ጠላት ተቋቊማችሁ ለመዋጋት አትችሉም። በአሕዛብ መካከል ትጠፋላችሁ፤ በጠላቶቻችሁም ምድር ተውጣችሁ ትቀራላችሁ። በጠላቶቻችሁ ምድር ከሞት ተርፋችሁ የምትቀሩት ጥቂቶቻችሁ፥ በራሳችሁና በቀድሞ አባቶቻችሁ ኃጢአት ምክንያት መንምናችሁ ትቀራላችሁ። “ነገር ግን የእናንተ ዘሮች የራሳቸውን ኃጢአት፥ እንዲሁም በእኔ ላይ ያመፁትንና የተቃወሙኝን የቀድሞ አባቶቻቸውን ኃጢአት ይናዘዛሉ፤ እነርሱን ተቃውሜ ወደ ጠላቶቻቸው አገር እንዲሰደዱ አደረግሁ፤ ሆኖም እልኸኛ ልባቸው በትሕትና ተሰብሮ ከኃጢአታቸው ቢታረሙ፥ ከያዕቆብ፥ ከይስሐቅና ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም ለሕዝቤ ለመስጠት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል አድሳለሁ። ከሕዝብዋ ባዶ የሆነችው ምድር ውድማ ሆና ሰንበቶችን ታከብራለች፤ እነርሱም ሥርዓቴን ስላልተቀበሉና ሕጌን ስላላከበሩ፥ በኃጢአታቸው ምክንያት ቅጣቱን በሙሉ ይቀበላሉ። ይሁን እንጂ በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ እንኳ እስከ መጨረሻ አልተዋቸውም ወይም አልደመስሳቸውም፤ ይህማ ቢሆን ኖሮ ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን እስከ መጨረሻ ባልጠበቅሁም ነበር፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ። ነገር ግን አምላካቸው እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” እግዚአብሔር በእርሱና በእስራኤል ሕዝብ መካከል በሙሴ አማካይነት በሲና ተራራ ላይ የሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።

ዘሌዋውያን 26:27-46 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ይህም ተደርጎባችሁ እንኳ ባትሰሙኝ፥ እኔንም በመቃወም ብትሄዱ፥ እኔ ደግሞ በቁጣ እናንተን በመቃወም እሄዳለሁ፤ እኔም ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። ከተሞቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ መቅደሶቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፥ መልካሙንም መዓዛችሁን አላሸትም። ምድሪቱንም የተራቈተች አደርጋለሁ፤ የሚቀመጡባትም ጠላቶቻችሁ በእርሷ ላይ ይሣቀቃሉ። እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም ባድማ ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ይፈርሳሉ። “በዚያም በጠላቶቻችሁ ምድር ሳላችሁ፥ ምድሪቱ ባድማ ሆና እስከተቀመጠችበት ጊዜ ድረስ ሁሉ ሰንበታትን በማድረግዋ ትደሰታለች፤ በዚያም ጊዜ ምድሪቱ ታርፋለች፥ ሰንበታትንም በማድረግዋ ትደሰታለች። እናንተ ተቀምጣችሁባት በነበረ ጊዜ በሰንበቶቻችሁ ያልነበራትን እረፈት ባድማ ሆና እስከተቀመጠችበት ጊዜ ድረስ ሁሉ ይኖራታል። በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ። ማንም ሳያሳድዳቸው ከሰይፍ እንደሚሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ እናንተም በጠላቶቻችሁ ፊት የምትቆሙበት ኃይል አይኖራችሁም። በአሕዛብም መካከል ታልቃላችሁ፥ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች። ከእናንተም መካከል የተረፉት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይመነምናሉ፤ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ እንደ እነርሱ ይመነምናሉ። “ነገር ግን እኔን በመቃወም ሄደዋልና፥ በእኔ ላይ ፈጽሞ በከዳተኝነት ያደረጉትን በደላቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ይናዘዛሉ። እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ እኔም ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ እንዲሁም ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትንም ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስታውሳለሁ። ምድርሪቱም በእነርሱ ትተዋለች፤ ያለ እነርሱም ባድማ ሆና እስከተቀመጠችበት ጊዜ ድረስ ሰንበታትን በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስላልተቀበሉ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የበደላቸውን ቅጣት ይቀበላሉ። በዚህ ነገር ሁሉ ግን እኔ ጌታ አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ ፈጽሞ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም። እኔ አምላክ እንድሆናቸው አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።” ጌታም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰጣቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።