ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 26:27-46

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 26:27-46 አማ2000

እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ አግ​ድ​ማ​ች​ሁም ብት​ሄ​ዱ​ብኝ፥ እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ። የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ። የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በእጅ የተ​ሠሩ የዕ​ን​ጨት ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሬሳ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ሬሳ​ዎች ላይ እጥ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም ትጸ​የ​ፋ​ች​ኋ​ለች። ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም መዓዛ አላ​ሸ​ት​ትም። ምድ​ሪ​ቱ​ንም የተ​ፈ​ታች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ር​ስዋ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ቃሉ። እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ። “በዚ​ያም በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ሁሉ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ምድር ሳላ​ችሁ፥ ምድ​ሪቱ ሰን​በት በማ​ድ​ረ​ግዋ ደስ ይላ​ታል፤ በዚ​ያም ጊዜ ምድ​ሪቱ ታር​ፋ​ለች፤ ስን​በ​ት​ንም በማ​ድ​ረ​ግዋ ደስ ይላ​ታል። እና​ንተ ተቀ​ም​ጣ​ች​ሁ​ባት በነ​በረ ጊዜ በሰ​ን​በ​ቶ​ቻ​ችሁ አላ​ረ​ፈ​ችም ነበ​ርና በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ሁሉ ታር​ፋ​ለች። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤ ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው ከሰ​ይፍ እን​ዲ​ሸሹ እርስ በር​ሳ​ቸው ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላሉ፤ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም። በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ምድር ትው​ጣ​ች​ኋ​ለች። ከእ​ና​ን​ተም ተለ​ይ​ተው የቀ​ሩት ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይጠ​ፋሉ፤ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀጢ​አት ደግሞ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ይቀ​ል​ጣሉ። “እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እን​ዳ​ሉኝ፥ በፊ​ቴም አግ​ድ​መው እንደ ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛሉ። እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤ ያን ጊዜ እኔ ከያ​ዕ​ቆብ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ደግ​ሞም ከይ​ስ​ሐቅ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን፥ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አስ​ባ​ለሁ። ምድ​ርም ከእ​ነ​ርሱ መጥ​ፋት የተ​ነሣ ባዶ ትቀ​ራ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ሳይ​ኖሩ በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ዕረ​ፍት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ፍር​ዴ​ንም ስለ ናቁ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም ሥር​ዐ​ቴን ስለ ተጸ​የ​ፈች የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ቅጣት ይሸ​ከ​ማሉ። ነገር ግን እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ነኝና እነ​ርሱ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ሳሉ፥ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያለ​ኝን ቃል ኪዳን እስ​ካ​ፈ​ርስ ድረስ አል​ጥ​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ጸ​የ​ፋ​ቸ​ው​ምም። እኔ አም​ላ​ካ​ቸው እሆን ዘንድ አሕ​ዛብ እያዩ ከግ​ብፅ ምድር ከግ​ዞት ቤት እን​ዳ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው የቀ​ድሞ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውን ስለ እነ​ርሱ አስ​ባ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ር​ሱና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰ​ጣ​ቸው ሥር​ዐ​ቶ​ችና ፍር​ዶች፥ ሕግ​ጋ​ትም እነ​ዚህ ናቸው።