ዘሌዋውያን 16:15-34

ዘሌዋውያን 16:15-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ፍየሉንም ለሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረደው፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ወስዶ በወይፈኑ ደም እንዳደረገው በዚህኛው ያድርግ፤ ደሙን በስርየቱ መክደኛ ላይ፣ እንዲሁም በመክደኛው ትይዩ ይርጭ። ከእስራኤላውያን ርኩሰትና ዐመፅ፣ ከየትኛውም ኀጢአታቸው ይነጻ ዘንድ በዚህ ሁኔታ ለቅድስተ ቅዱሳኑ ያስተሰርይለታል፤ በርኩሰታቸው መካከል በእነርሱ ዘንድ ላለችውም የመገናኛዋ ድንኳን እንደዚሁ ያደርጋል። አሮን ለማስተስረይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለራሱ፣ ለቤተ ሰቡና ለእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ አስተስርዮ እስኪወጣ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝ። “ከዚያም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ይምጣ፤ ለመሠዊያውም ያስተስርይለት፤ ከወይፈኑና ከፍየሉ ደም ወስዶ የመሠዊያውን ቀንዶች ሁሉ ያስነካ፤ ከእስራኤላውያንም ርኩሰት መሠዊያውን ለማንጻትና ለመቀደስ ከደሙ ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭበት። “አሮን ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው የሚያደርገውን ስርየት ከፈጸመ በኋላ፣ በሕይወት ያለውን ፍየል ወደ ፊት ያቅርበው። ሁለት እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ በላዩም የእስራኤላውያንን ክፋትና ዐመፅ፣ ኀጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዝበት፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ይጫን፤ ፍየሉንም ለዚሁ ተግባር በተመደበ ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይስደደው። ፍየሉም ኀጢአታቸውን ሁሉ ተሸክሞ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፤ ሰውየውም ፍየሉን ሰው ሊኖርበት በማይችል ስፍራ ይልቀቀው። “ከዚህ በኋላ አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ሄዶ፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ሊገባ ሲል የለበሳቸውን የበፍታ ልብሶች አውልቆ በዚያው ይተዋቸው። በተቀደሰውም ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ የዘወትር ልብሱንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ ለራሱ ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ለሕዝቡም ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ። የኀጢአት መሥዋዕቱንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥል። “የሚለቀቀውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል። ደማቸው ለማስተስረያነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባው፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡት ወይፈንና ፍየል ከሰፈር ውጭ ተወስደው ቈዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸው ይቃጠል። እነዚህንም የሚያቃጥል ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል። “ለእናንተ የተሰጣችሁ የዘላለም ሥርዐት ይህ ነው፦ ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ሰውነታችሁን አድክሙ፤ የአገሩ ተወላጅም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ምንም ሥራ አይሥራ፤ የምትነጹበት ስርየት በዚህች ዕለት ይደረግላችኋልና፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኀጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። ይህች የፍጹም ዕረፍት ሰንበት ናት፤ ሰውነታችሁን አድክሙባት፤ የዘላለም ሥርዐት ናት። ሊቀ ካህናት ለመሆን አባቱን በመተካት የተቀባና የተሾመ ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው፣ ለካህናቱና ለማኅበረ ሰቡ ሁሉ ያስተስርይ። “ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሁናችሁ፤ በዚህም ሥርዐት መሠረት ለእስራኤላውያን ኀጢአት ሁሉ በዓመት አንድ ጊዜ ስርየት ይደረግ።” እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ተደረገ።

ዘሌዋውያን 16:15-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ስለ ሕዝቡም ኃጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፥ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፤ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ በፍየሉ ደም ያደርጋል፤ በመክደኛውም ላይና በመክደኛውም ፊት ይረጨዋል። ከእስራኤል ልጆች ርኩስነት ከመተላለፋቸውም ከኃጢአታቸውም የተነሣ ለመቅደሱ ያስተሰርይለታል፤ እንዲሁም በርኩስነታቸው መካከል ከእነርሱ ጋር ለኖረች ለመገናኛው ድንኳን ያደርጋል። እርሱም ለማስተስረይ ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤተ ሰቡም፥ ለእስራኤል ጉባዔ ሁሉ አስተስርዮ እስኪወጣ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ማንም አይኖርም። በእግዚአብሔርም ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያ ወጥቶ ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል። ከደሙም በእርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል፥ ከእስራኤልም ልጆች ርኩስነት ያነጻዋል፥ ይቀድሰውማል። መቅደሱንም፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ መሠዊያውንም ማስተስረይ ከፈጸመ በኋላ ሕያውን ፍየል ያቀርባል፤ አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል። ፍየሉም ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሀ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል። አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባል፥ ወደ መቅደሱም በገባ ጊዜ የለበሰውን የበፍታ ልብስ ያወልቃል፥ በዚያም ይተወዋል፤ በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የሕዝቡንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል። የኃጢአቱንም መሥዋዕት ስብ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል። ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደ መቅደስ የገባውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ወደ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቁርበታቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ። ያቃጠላቸውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል። ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተስረያ ይሆንላችኋልና በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቍት፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል፥ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ፤ የዘላለም ሥርዓት ነው። የሚቀባውም፥ በአባቱም ፈንታ ካህን ሊሆን የሚካነው ካህን ያስተስርይ፥ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ ለቅድስተ ቅዱሳንም ያስተስርይ፤ ለመገናኛውም ድንኳን ለመሠዊያውም ያስተስርይ፤ ለካህናቱም ለጉባኤውም ሕዝብ ሁሉ ያስተስርይ። ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ያስተሰርይ ዘንድ የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።

ዘሌዋውያን 16:15-34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ስለ ሕዝ​ቡም ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ያር​ዳል፤ ደሙ​ንም ወደ መጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም ደም እን​ዳ​ደ​ረገ በፍ​የሉ ደም ያደ​ር​ጋል፤ በመ​ክ​ደ​ኛው ላይና በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት ይረ​ጨ​ዋል። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርኩ​ስ​ነት፥ ከመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም፥ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለመ​ቅ​ደሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እን​ዲ​ሁም በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው መካ​ከል ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለኖ​ረች ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ያደ​ር​ጋል። እርሱ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ወደ መቅ​ደሱ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ አስ​ተ​ስ​ርዮ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ማንም አይ​ኖ​ርም። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወዳ​ለው ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጥቶ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም፥ ከፍ​የ​ሉም ደም ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ያሉ​ትን ቀን​ዶች ያስ​ነ​ካል። ከደ​ሙም በእ​ርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረ​ጫል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርኩ​ስ​ነት ያነ​ጻ​ዋል፤ ይቀ​ድ​ሰ​ው​ማል። “ስለ​መ​ቅ​ደሱ፥ስለ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን፥ ስለ መሠ​ዊ​ያ​ውም ማስ​ተ​ስ​ረ​ያና ስለ ካህ​ና​ትም ማን​ጻት ከፈ​ጸመ በኋላ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ፍየል ያቀ​ር​ባል። አሮ​ንም ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በደ​ኅ​ነ​ኛው ፍየል ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ በላ​ዩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ በፍ​የ​ሉም ራስ ላይ ያሸ​ክ​መ​ዋል፤ በተ​ዘ​ጋ​ጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰ​ድ​ደ​ዋል። ፍየ​ሉም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ወደ በረሃ ይሸ​ከ​ማል፤ ፍየ​ሉ​ንም ዛፍ በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ ውስጥ ይለ​ቅ​ቀ​ዋል። “አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይገ​ባል፤ ወደ መቅ​ደ​ሱም በገባ ጊዜ የለ​በ​ሰ​ውን የተ​ልባ እግር ልብስ ያወ​ል​ቃል፤ በዚ​ያም ይተ​ወ​ዋል። በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍራ ገላ​ውን በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ሌላ​ው​ንም ልብስ ለብሶ ይወ​ጣል፤ የእ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ለካ​ህ​ናቱ እን​ዳ​ስ​ተ​ሰ​ረየ ለራ​ሱም፥ ለሕ​ዝ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል። የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል። ለመ​ለ​ቀቅ የሚ​ሆ​ነ​ውን ፍየል የወ​ሰደ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል። ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ። ያቃ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል። “ይህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ። በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋ​ልና በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ራሳ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ የሀ​ገር ልጅም፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል የተ​ቀ​መጠ እን​ግዳ ሥራን ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ። ታላቅ ሰን​በት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም ታዋ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው። የሚ​ቀ​ባ​ውም፥ በአ​ባ​ቱም ፋንታ ካህን ሊሆን የሚ​ካ​ነው ካህን ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ልብስ ይል​በስ። ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለካ​ህ​ና​ቱም፥ ለጉ​ባ​ኤ​ውም ሕዝብ ሁሉ ያስ​ተ​ስ​ርይ። ይህም አንድ ጊዜ በዓ​መት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አደ​ረገ።

ዘሌዋውያን 16:15-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ፍየሉንም ለሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረደው፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ወስዶ በወይፈኑ ደም እንዳደረገው በዚህኛው ያድርግ፤ ደሙን በስርየቱ መክደኛ ላይ፣ እንዲሁም በመክደኛው ትይዩ ይርጭ። ከእስራኤላውያን ርኩሰትና ዐመፅ፣ ከየትኛውም ኀጢአታቸው ይነጻ ዘንድ በዚህ ሁኔታ ለቅድስተ ቅዱሳኑ ያስተሰርይለታል፤ በርኩሰታቸው መካከል በእነርሱ ዘንድ ላለችውም የመገናኛዋ ድንኳን እንደዚሁ ያደርጋል። አሮን ለማስተስረይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለራሱ፣ ለቤተ ሰቡና ለእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ አስተስርዮ እስኪወጣ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝ። “ከዚያም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ይምጣ፤ ለመሠዊያውም ያስተስርይለት፤ ከወይፈኑና ከፍየሉ ደም ወስዶ የመሠዊያውን ቀንዶች ሁሉ ያስነካ፤ ከእስራኤላውያንም ርኩሰት መሠዊያውን ለማንጻትና ለመቀደስ ከደሙ ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭበት። “አሮን ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው የሚያደርገውን ስርየት ከፈጸመ በኋላ፣ በሕይወት ያለውን ፍየል ወደ ፊት ያቅርበው። ሁለት እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ በላዩም የእስራኤላውያንን ክፋትና ዐመፅ፣ ኀጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዝበት፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ይጫን፤ ፍየሉንም ለዚሁ ተግባር በተመደበ ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይስደደው። ፍየሉም ኀጢአታቸውን ሁሉ ተሸክሞ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፤ ሰውየውም ፍየሉን ሰው ሊኖርበት በማይችል ስፍራ ይልቀቀው። “ከዚህ በኋላ አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ሄዶ፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ሊገባ ሲል የለበሳቸውን የበፍታ ልብሶች አውልቆ በዚያው ይተዋቸው። በተቀደሰውም ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ የዘወትር ልብሱንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ ለራሱ ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ለሕዝቡም ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ። የኀጢአት መሥዋዕቱንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥል። “የሚለቀቀውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል። ደማቸው ለማስተስረያነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባው፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡት ወይፈንና ፍየል ከሰፈር ውጭ ተወስደው ቈዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸው ይቃጠል። እነዚህንም የሚያቃጥል ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል። “ለእናንተ የተሰጣችሁ የዘላለም ሥርዐት ይህ ነው፦ ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ሰውነታችሁን አድክሙ፤ የአገሩ ተወላጅም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ምንም ሥራ አይሥራ፤ የምትነጹበት ስርየት በዚህች ዕለት ይደረግላችኋልና፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኀጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። ይህች የፍጹም ዕረፍት ሰንበት ናት፤ ሰውነታችሁን አድክሙባት፤ የዘላለም ሥርዐት ናት። ሊቀ ካህናት ለመሆን አባቱን በመተካት የተቀባና የተሾመ ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው፣ ለካህናቱና ለማኅበረ ሰቡ ሁሉ ያስተስርይ። “ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሁናችሁ፤ በዚህም ሥርዐት መሠረት ለእስራኤላውያን ኀጢአት ሁሉ በዓመት አንድ ጊዜ ስርየት ይደረግ።” እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ተደረገ።

ዘሌዋውያን 16:15-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ስለ ሕዝቡም ኃጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፥ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፤ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ በፍየሉ ደም ያደርጋል፤ በመክደኛውም ላይና በመክደኛውም ፊት ይረጨዋል። ከእስራኤል ልጆች ርኩስነት ከመተላለፋቸውም ከኃጢአታቸውም የተነሣ ለመቅደሱ ያስተሰርይለታል፤ እንዲሁም በርኩስነታቸው መካከል ከእነርሱ ጋር ለኖረች ለመገናኛው ድንኳን ያደርጋል። እርሱም ለማስተስረይ ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤተ ሰቡም፥ ለእስራኤል ጉባዔ ሁሉ አስተስርዮ እስኪወጣ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ማንም አይኖርም። በእግዚአብሔርም ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያ ወጥቶ ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል። ከደሙም በእርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል፥ ከእስራኤልም ልጆች ርኩስነት ያነጻዋል፥ ይቀድሰውማል። መቅደሱንም፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ መሠዊያውንም ማስተስረይ ከፈጸመ በኋላ ሕያውን ፍየል ያቀርባል፤ አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል። ፍየሉም ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሀ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል። አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባል፥ ወደ መቅደሱም በገባ ጊዜ የለበሰውን የበፍታ ልብስ ያወልቃል፥ በዚያም ይተወዋል፤ በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የሕዝቡንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል። የኃጢአቱንም መሥዋዕት ስብ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል። ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደ መቅደስ የገባውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ወደ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቁርበታቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ። ያቃጠላቸውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል። ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተስረያ ይሆንላችኋልና በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቍት፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል፥ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ፤ የዘላለም ሥርዓት ነው። የሚቀባውም፥ በአባቱም ፈንታ ካህን ሊሆን የሚካነው ካህን ያስተስርይ፥ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ ለቅድስተ ቅዱሳንም ያስተስርይ፤ ለመገናኛውም ድንኳን ለመሠዊያውም ያስተስርይ፤ ለካህናቱም ለጉባኤውም ሕዝብ ሁሉ ያስተስርይ። ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ያስተሰርይ ዘንድ የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።

ዘሌዋውያን 16:15-34 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህም በኋላ ለሕዝቡ የኃጢአት ማስተስረያ የሆነውን ፍየል ይረድ፤ ደሙንም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አስገብቶ በኰርማው ደም ባደረገው ዐይነት፥ በስርየት መክደኛው ላይ፥ እንዲሁም በኪዳኑ ታቦት ፊት ይርጨው። በዚህም ዐይነት ቅድስተ ቅዱሳኑን ከእስራኤል ሕዝብ ርኲሰትና ከኃጢአታቸውም ሁሉ ለማጥራት የማንጻትን ሥርዓት ይፈጽማል፤ ንጹሕ ባልሆነ ሰፈር መካከል ስለሚገኝ ድንኳኑንም ለማንጻት እንዲሁ ያደርጋል። አሮን ለማስተሰረይ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ ለራሱ፥ ለቤተሰቡ፥ ለእስራኤል ጉባኤ ሁሉ አስተስርዮ እስኪወጣ ድረስ ድንኳን ውስጥ ማንም አይኑር፤ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ወጥቶ መሠዊያውን ያንጻው፤ ከኰርማውና ከፍየሉ ጥቂት ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ጒጦች ይቀባ፤ ከደሙም ጥቂቱን ወስዶ በጣቱ እየነከረ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ይርጭ፤ በዚህም ዐይነት ከእስራኤል ሕዝብ ርኲሰትን በማንጻት መሠዊያውን የተቀደሰ ያደርገዋል። አሮን ቅድስተ ቅዱሳኑን፥ የመገናኛውን ድንኳን የቀረውን ክፍልና መሠዊያውንም የማንጻት ሥርዓት ከፈጸመ በኋላ ለዐዛዜል የተመረጠውን ፍየል ወስዶ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ሁለት እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭናል፤ የሕዝቡን ክፋት፥ ኃጢአትና ዐመፅ ሁሉ በመናዘዝ አዛውሮ በፍየሉ ራስ ላይ ያሸክመዋል፤ ከዚህ በኋላ ለዚህ ሥራ የተመደበ ሰው ፍየሉን ነድቶ ወደ በረሓ ይወስደዋል። ፍየሉንም ኃጢአታቸውን ሁሉ ተሸክሞ ምንም ሰው ወደማይኖርበት ምድረ በዳ ወስዶ ይለቀዋል። “አሮንም ወደ ድንኳኑ ይግባ፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከመግባቱ በፊት ለብሶት የነበረውን የክህነት ልብስ አውልቆ፥ በዚያ ይተወው፤ በተቀደሰውም ቦታ ሰውነቱን ታጥቦ የዘወትር ልብሱን ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ የራሱንና የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቅርብ። ኃጢአትን ለማስተስረይ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውንም የእንስሳ ስብ፥ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ የተመረጠውን ፍየል እየነዳ ወደ በረሓ ይዞት ሄዶ የነበረውም ሰው ወደ ሰፈር ከመግባቱ በፊት ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም ይታጠብ። ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆነው የቀረቡትና ኃጢአትን ለማስተስረይ ደማቸው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የነበረው ኰርማና ፍየልም ከሰፈር ወደ ውጪ ተወስደው በእሳት ይቃጠሉ፤ እንዲሁም ቆዳቸው፥ ሥጋቸውና የሆድ ዕቃቸው በሙሉ ይቃጠል። እነርሱንም የሚያቃጥለው ሰው ወደ ሰፈር ከመመለሱ በፊት ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም ይታጠብ። “ከዚህ የሚከተሉትን መመሪያዎች በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁአቸዋላችሁ፦ ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እስራኤላውያንና በእነርሱ መካከል የሚኖሩ መጻተኞች ራሳቸውን ማዋረድ አለባቸው፤ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩበት። በዚያን ዕለት ንጹሖች እንድትሆኑ የኃጢአት ማስተስረይ ይደረግላችኋል፤ ከዚያም ከኃጢአታችሁ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የነጻችሁ ትሆናላችሁ፤ ያም ዕለት እንደ ሰንበት የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ፤ በዚያን ቀን ራሳችሁን አዋርዱ ይህም የዘለዓለም ሥርዓት ነው። በአባቱ ምትክ ሊቀ ካህናት እንዲሆን ተለይቶ የሚሾመው ካህን የተቀደሰ የክህነት በፍታ ልብሱን ለብሶ ያስተሰርያል። እርሱም ለቅድስተ ቅዱሳኑ፥ ለመገናኛው ድንኳን፥ ለመሠዊያው፥ ለካህናቱና ለጉባኤው ያስተሰርያል። በዓመት አንድ ጊዜ የእስራኤላውያንን ኃጢአት ሁሉ ማስተስረይ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።” በዚህም ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ።

ዘሌዋውያን 16:15-34 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ለሕዝቡም የሆነውን የኃጢአት መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፥ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፤ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ እንዲሁ በፍየሉ ደም ላይ ያደርጋል፤ በስርየቱ መክደኛም ላይና በስርየቱ መክደኛም ፊት ለፈት ይረጨዋል። ከእስራኤል ልጆች ርኩስነት፥ ከመተላለፋቸውም፥ ከኃጢአታቸውም ሁሉ የተነሣ ለተቀደሰው ስፍራ ያስተሰርይለታል፤ በርኩስነታቸውም መካከል ከእነርሱ ጋር ላለው ለመገናኛው ድንኳን እንዲሁ ያደርጋል። አሮንም ለማስተስረይ ወደተቀደሰው ስፍራ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤተሰቡም፥ ለእስራኤል ጉባዔ ሁሉ አስተስርዮ እስኪ ወጣ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ማንም ሰው አይገኝ። ከዚያም በኋላ በጌታ ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያው ይወጣል፤ ለእርሱም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል። ከደሙም በእርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል፥ ከእስራኤልም ልጆች ርኩስነት ያነጻዋል፥ ይቀድሰዋልም። “የተቀደሰውንም ስፍራ፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ መሠዊያውንም ማስተስረይ ከፈጸመ በኋላ በሕይወት ያለውን ፍየል ያቀርባል፤ አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውንም ሁሉ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ያደርገዋል። ፍየሉም በደላቸውን ሁሉ በረሀ ወደ ሆነ ስፍራ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ እንዲሄድ ይለቅቀዋል። “አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባል፥ ወደ ተቀደሰውም ስፍራ በገባ ጊዜ የለበሰውን የበፍታ ልብስ ያወልቃል፥ በዚያም ይተወዋል፤ በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ይለብሳል፤ ወጥቶም ለእርሱ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት እና ለሕዝቡ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል። የኃጢአቱንም መሥዋዕት ስብ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ወደ ዐዛዜል የሄደውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል። ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደተቀደሰው ስፍራ የገባውን፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቆዳቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ። ያቃጠላቸውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል። “ይህም የዘለዓለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አዋርዱ፥ የአገሩም ተወላጅ ሆነ በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤ ለእናንተ በዚህ ቀን እንድትነጹ ማስተስረያ ይደረግላችኋልና፤ በጌታም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። ለእናንተም ፈጽሞ የምታርፉበት ታላቅ ሰንበት ይሆናል፥ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ፤ የዘለዓለም ሥርዓት ነው። በአባቱም ፈንታ ካህን ሆኖ ለማገልገል ተለይቶ የሚቀባው ካህን የተቀደሰውን የበፍታ ልብስ ለብሶ ያስተስርያል። ለቅድስተ ቅዱሳንም ያስተስርይ፤ ለመገናኛውም ድንኳን ለመሠዊያውም ያስተስርይ፤ ለካህናቱም ለጉባኤውም ሕዝብ ሁሉ ያስተስርይ። ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ለማስተሰረይ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆንላችኋል።” ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።