ዘሌዋውያን 16:1-10

ዘሌዋውያን 16:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሁለቱ የአሮን ልጆች ያልተፈቀደ እሳት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ፊት በመቅረባቸው ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ “እኔ በታቦቱ ስርየት መክደኛ በደመና የምገለጥበት ስለ ሆነ፥ መጋረጃውን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ያለበት ሁልጊዜ ሳይሆን፥ በአንድ በተወሰነ ቀን ብቻ መሆኑን፥ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው፤ ይህን ትእዛዝ የማይፈጽም ከሆነ ይሞታል፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችለውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አንድ አውራ በግ ካቀረበ በኋላ መሆን አለበት።” “አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን ታጥቦ የክህነት ልብሱን ይልበስ፤ ይኸውም ከበፍታ የተሠራውን ቀሚስና ሱሪ ይልበስ፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራውን ቀበቶ ይታጠቅ፤ ከበፍታ የተሠራውንም መጠምጠሚያ ራሱ ላይ ያድርግ። “የእስራኤልም ማኅበር ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ለአሮን ያምጡለት። የራሱንና የቤተሰቡንም ኃጢአት ለማስተስረይ አንድ ኰርማ መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ። ከዚህም በኋላ ሁለቱን ፍየሎች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ይውሰድ፤ በዚያም አንዱ ‘ለእግዚአብሔር’ ሁለተኛው ‘ለዐዛዜል’ የሚል ምልክት ያለባቸው ሁለት ድንጋዮች ወስዶ ዕጣ ያውጣ፤ አሮንም በዕጣ ለእግዚአብሔር የተመረጠውን ፍየል ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል። ለዐዛዜል የተመረጠውም ፍየል የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ በረሓ እንዲላክ ከነሕይወቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቀርባል።”

ዘሌዋውያን 16:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሌላ እሳ​ትን ስላ​መጡ የሞቱ ሁለቱ የአ​ሮን ልጆች ከሞቱ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ተና​ገ​ረው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ በደ​መ​ናው ውስጥ እታ​ያ​ለ​ሁና እን​ዳ​ይ​ሞት በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ወዳ​ለው ወደ ስር​የቱ መክ​ደኛ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁል​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ገባ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ንገ​ረው። እን​ዲሁ አሮን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች ወይ​ፈን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይግባ። የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ቀሚስ ይል​በስ፤ የተ​ልባ እግ​ርም ሱሪ በገ​ላው ላይ ይሁን፤ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂያ ይታ​ጠቅ፤ የተ​ልባ እግር አክ​ሊ​ልም በራሱ ላይ ያድ​ርግ፤ እነ​ዚህ የተ​ቀ​ደሱ ልብ​ሶች ናቸው፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ታጥቦ ይል​በ​ሳ​ቸው። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለት የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ በግ ይው​ሰድ። “አሮ​ንም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባል፤ ለራ​ሱም፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል። ሁለ​ቱ​ንም የፍ​የል ጠቦ​ቶች ወስዶ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ቸ​ዋል። አሮ​ንም በሁ​ለቱ የፍ​የል ጠቦ​ቶች ላይ ዕጣ ይጥ​ል​ባ​ቸ​ዋል፤ አን​ዱን ዕጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሌላ​ው​ንም ዕጣ ለሚ​ለ​ቀቅ። አሮ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ባ​ሔር ዕጣ የሆ​ነ​በ​ትን ፍየል ያቀ​ር​ባል፤ ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ያደ​ር​ገ​ዋል። የመ​ለ​ቀ​ቅም ዕጣ የሆ​ነ​በ​ትን ፍየል ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​በት ዘንድ፥ ለመ​ለ​ቀ​ቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰ​ድ​ደው ዘንድ በሕ​ይ​ወቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​መ​ዋል።

ዘሌዋውያን 16:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በእግዚአብሔር ፊት በቀረቡ ጊዜ ከሞቱት፣ ከሁለቱ የአሮን ልጆች ሞት በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተናገረው። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው። “ወደ ተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ፣ አሮን እንዲህ ያድርግ፤ ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይዞ ይምጣ፤ የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፤ በሰውነቱ ላይ የሚያርፈውን ከበፍታ የተሠራውን የውስጥ ሱሪ ያጥልቅ፤ የበፍታውን መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የበፍታውን መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ ልብሶቹ የተቀደሱ በመሆናቸው እነዚህን ከመልበሱ በፊት ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ። ከእስራኤል ማኅበረ ሰብ ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ። “አሮን ለራሱና ለቤተ ሰቡ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ፣ ወይፈኑን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ስለ ራሱ ያቅርብ፤ ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያቁማቸው። አሮንም አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር፣ ሌላውን ለሚለቀቀው ፍየል ለማድረግ በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል። በዕጣ ለእግዚአብሔር የደረሰውንም ፍየል አምጥቶ ለኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ ይሠዋ። ወደ ምድረ በዳ ተለቅቆ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ፣ እንዲለቀቅ ዕጣ የወጣበትን ፍየል ከነሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።

ዘሌዋውያን 16:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በእግዚአብሔር ፊት የቀረቡና የሞቱ ሁለቱ የአሮን ልጆች ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተናገረው፤ እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። እንዲሁ አሮን ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀደሰ ስፍራ ይግባ። የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ የበፍታውንም መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው። ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለት አውራ ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ። አሮንም ለእርሱ ያለውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፥ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል። ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያቆማቸዋል። አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ። አሮንም የእግዚአብሔር ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያቀርባል፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል። የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ዘንድ፥ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።

ዘሌዋውያን 16:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሁለቱ የአሮን ልጆች ያልተፈቀደ እሳት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ፊት በመቅረባቸው ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ “እኔ በታቦቱ ስርየት መክደኛ በደመና የምገለጥበት ስለ ሆነ፥ መጋረጃውን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ያለበት ሁልጊዜ ሳይሆን፥ በአንድ በተወሰነ ቀን ብቻ መሆኑን፥ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው፤ ይህን ትእዛዝ የማይፈጽም ከሆነ ይሞታል፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችለውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አንድ አውራ በግ ካቀረበ በኋላ መሆን አለበት።” “አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን ታጥቦ የክህነት ልብሱን ይልበስ፤ ይኸውም ከበፍታ የተሠራውን ቀሚስና ሱሪ ይልበስ፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራውን ቀበቶ ይታጠቅ፤ ከበፍታ የተሠራውንም መጠምጠሚያ ራሱ ላይ ያድርግ። “የእስራኤልም ማኅበር ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ለአሮን ያምጡለት። የራሱንና የቤተሰቡንም ኃጢአት ለማስተስረይ አንድ ኰርማ መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ። ከዚህም በኋላ ሁለቱን ፍየሎች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ይውሰድ፤ በዚያም አንዱ ‘ለእግዚአብሔር’ ሁለተኛው ‘ለዐዛዜል’ የሚል ምልክት ያለባቸው ሁለት ድንጋዮች ወስዶ ዕጣ ያውጣ፤ አሮንም በዕጣ ለእግዚአብሔር የተመረጠውን ፍየል ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል። ለዐዛዜል የተመረጠውም ፍየል የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ በረሓ እንዲላክ ከነሕይወቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቀርባል።”

ዘሌዋውያን 16:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በጌታ ፊት በቀረቡ ጊዜ የሞቱት ሁለቱ የአሮን ልጆች ከሞቱ በኋላ ጌታ ሙሴን ተናገረው፤ ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። ነገር ግን አሮን ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀደሰ ስፍራ ይግባ። የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው። ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለት አውራ ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ። “አሮንም ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፥ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል። ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በጌታ ፊት ያቆማቸዋል። አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱ ዕጣ ለጌታ ሌላው ዕጣ ለዐዛዜል ይሆናል። አሮንም ለጌታ ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል ያቀርባል፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል። ለዐዛዜል ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል እንዲያስተሰርይበት፥ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ለመልቀቅ በሕይወቱ እንዳለ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።