በጌታ ፊት በቀረቡ ጊዜ የሞቱት ሁለቱ የአሮን ልጆች ከሞቱ በኋላ ጌታ ሙሴን ተናገረው፤ ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። ነገር ግን አሮን ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀደሰ ስፍራ ይግባ። የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው። ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለት አውራ ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ። “አሮንም ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፥ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል። ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በጌታ ፊት ያቆማቸዋል። አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱ ዕጣ ለጌታ ሌላው ዕጣ ለዐዛዜል ይሆናል። አሮንም ለጌታ ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል ያቀርባል፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል። ለዐዛዜል ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል እንዲያስተሰርይበት፥ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ለመልቀቅ በሕይወቱ እንዳለ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።
ኦሪት ዘሌዋውያን 16 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘሌዋውያን 16:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች