ሁለቱ የአሮን ልጆች ያልተፈቀደ እሳት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ፊት በመቅረባቸው ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ “እኔ በታቦቱ ስርየት መክደኛ በደመና የምገለጥበት ስለ ሆነ፥ መጋረጃውን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ያለበት ሁልጊዜ ሳይሆን፥ በአንድ በተወሰነ ቀን ብቻ መሆኑን፥ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው፤ ይህን ትእዛዝ የማይፈጽም ከሆነ ይሞታል፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችለውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አንድ አውራ በግ ካቀረበ በኋላ መሆን አለበት።” “አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን ታጥቦ የክህነት ልብሱን ይልበስ፤ ይኸውም ከበፍታ የተሠራውን ቀሚስና ሱሪ ይልበስ፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራውን ቀበቶ ይታጠቅ፤ ከበፍታ የተሠራውንም መጠምጠሚያ ራሱ ላይ ያድርግ። “የእስራኤልም ማኅበር ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ለአሮን ያምጡለት። የራሱንና የቤተሰቡንም ኃጢአት ለማስተስረይ አንድ ኰርማ መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ። ከዚህም በኋላ ሁለቱን ፍየሎች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ይውሰድ፤ በዚያም አንዱ ‘ለእግዚአብሔር’ ሁለተኛው ‘ለዐዛዜል’ የሚል ምልክት ያለባቸው ሁለት ድንጋዮች ወስዶ ዕጣ ያውጣ፤ አሮንም በዕጣ ለእግዚአብሔር የተመረጠውን ፍየል ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል። ለዐዛዜል የተመረጠውም ፍየል የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ በረሓ እንዲላክ ከነሕይወቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቀርባል።”
ኦሪት ዘሌዋውያን 16 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘሌዋውያን 16:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች