በእግዚአብሔር ፊት ሌላ እሳትን ስላመጡ የሞቱ ሁለቱ የአሮን ልጆች ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተናገረው። እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። እንዲሁ አሮን ለኀጢአት መሥዋዕት ከላሞች ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ይግባ። የተቀደሰውንም የተልባ እግር ቀሚስ ይልበስ፤ የተልባ እግርም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፤ የተልባ እግር መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የተልባ እግር አክሊልም በራሱ ላይ ያድርግ፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው። ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለት የፍየል ጠቦቶች፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ። “አሮንም የኀጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም፥ ለቤተሰቡም ያስተሰርያል። ሁለቱንም የፍየል ጠቦቶች ወስዶ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያቆማቸዋል። አሮንም በሁለቱ የፍየል ጠቦቶች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፤ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር፥ ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ። አሮንም የእግዚአባሔር ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያቀርባል፤ ስለ ኀጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል። የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ዘንድ፥ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።
ኦሪት ዘሌዋውያን 16 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘሌዋውያን 16:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች