የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 64:1-11

ኢሳይያስ 64:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሰማ​ይን ብት​ከ​ፍት ከአ​ንተ የተ​ነሣ ተራ​ሮች ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ይቀ​ል​ጣ​ሉም። አደሮ ማር በእ​ሳት ፊት እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ እን​ዲሁ ጠላ​ቶ​ች​ህን እሳት ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ስም​ህም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይታ​ወ​ቃል፤ አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ። የክ​ብ​ር​ህ​ንም ሥራ ባደ​ረ​ግህ ጊዜ፥ ተራ​ሮች በፊ​ትህ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ። ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም። በቸ​ር​ነ​ትህ የሚ​ታ​ገሡ መን​ገ​ድ​ህ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ይገ​ና​ኙ​ሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈ​ጣህ፤ እኛም ኀጢ​አት ሠራን፤ ስለ​ዚ​ህም ተሳ​ሳ​ትን። ሁላ​ችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነ​ናል፤ ጽድ​ቃ​ች​ንም ሁሉ እንደ መር​ገም ጨርቅ ነው፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ምክ​ን​ያት እንደ ቅጠል ረግ​ፈ​ናል፤ እን​ዲ​ሁም ነፋስ ጠራ​ርጎ ወስ​ዶ​ናል። ስም​ህ​ንም የሚ​ጠራ፥ አን​ተ​ንም የሚ​ያ​ስብ የለም፤ ፊት​ህ​ንም ከእኛ መል​ሰ​ሃል፤ ለኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ንም አሳ​ል​ፈህ ሰጥ​ተ​ኸ​ናል። አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አን​ተም ሠሪ​ያ​ችን ነህ፤ እኛም ሁላ​ችን የእ​ጅህ ሥራ ነን። አቤቱ፥ እጅግ አት​ቈጣ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አታ​ስብ፤ አሁ​ንም እባ​ክህ፥ ወደ እኛ ተመ​ል​ከት፤ እኛ ሁላ​ችን ሕዝ​ብህ ነን። የተ​ቀ​ደሱ ከተ​ሞ​ችህ ምድረ በዳ ሆነ​ዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውድማ ሆና​ለች። አባ​ቶ​ቻ​ችን ያከ​በ​ሩት ክብ​ራ​ችን ቤተ መቅ​ደ​ስህ በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አል፤ ያማ​ረ​ውም ስፍ​ራ​ችን ፈር​ሶ​አል።

ኢሳይያስ 64:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አቤቱ፤ ሰማያትን ቀድደህ ምነው በወረድህ! ምነዋ ተራሮች በፊትህ በተናወጡ! እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ ውሃንም እንደሚያፈላ፣ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤ መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ። እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣ አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ። ከጥንት ጀምሮ፣ በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣ እንደ አንተ ያለውን አምላክ ያየ ዐይን፣ ያደመጠ ጆሮ ፈጽሞ አልነበረም። በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣ መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤ እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣ እነሆ፤ ተቈጣህ፤ ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን? ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል። ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤ አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤ ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤ ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል። ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤ ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤ እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤ ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና። የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆኑ፤ ጽዮን ራሷ እንኳ ምድረ በዳ፣ ኢየሩሳሌምም የተፈታች ሆናለች። አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣ በእሳት ተቃጥሏል፤ ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል።

ኢሳይያስ 64:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ! እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አህዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ። ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ ወረድህ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ። ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም። ጽድቅን የሚያደርገውን በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እነሆ፥ አንተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን፥ ስለዚህም ተሳሳትን። ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፥ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፥ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፥ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል። አሁን ግን፥ አቤቱ፥ እንተ አባታችን ነህ፥ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን። አቤቱ፥ እጅግ አትቈጣ፥ ለዘላለምም ኃጢአትን አታስብ፥ እነሆ፥ እባክህ፥ ተመልከት፥ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን። የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል፥ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየሩሳሌምም ውድማ ሆናለች። አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፥ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል።

ኢሳይያስ 64:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ምነው ሰማያትን ከፍተህ ብትወርድ፤ ተራራዎችም አንተን አይተው ምነው በተንቀጠቀጡ፤ እሳት ደረቁን እንጨት በሚያጋይ ጊዜ ፍሙ የተጣደውን ውሃ እንደሚያፍለቀልቀው፥ ሕዝቦችም በአንተ መገለጥ እንዲንቀጠቀጡ ወርደህ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ አድርግ! ከዚህ በፊትም መጥተህ እኛ ያልጠበቅናቸውን እጅግ አስፈሪ የሆኑ ነገሮችን በፈጸምክበት ጊዜ ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ። ከጥንት ጀምሮ ተስፋቸውን በእርሱ አድርገው ለሚተማመኑበት ወገኖች እነዚያን ሁሉ ድንቅ ነገሮች ያደረገ አምላክ ከአንተ በቀር አልተሰማም፤ አልታየም፤ የተረዳም የለም። የአንተን መንገድ አስታውሰው ፈቃድህን በደስታ የሚፈጽሙትን ትረዳቸዋለህ፤ ፈቃድህን መተላለፍን በቀጠልን ጊዜ ግን አንተ ተቈጣኸን፤ ታዲያ እንዴት ልንድን እንችላለን? እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል። በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም። ሆኖም አምላክ ሆይ! አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች ስንሆን አንተ ሠሪአችን ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን። አምላክ ሆይ! አምርረህ አትቈጣ፤ ኃጢአታችንንም ለዘለዓለም አታስብብን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ መሆናችንን አስታውስ። የተቀደሱ ከተሞችህ በረሓ ሆነዋል፤ ጽዮን በረሓ ኢየሩሳሌምም ባድማ ሆነዋል። የቀድሞ አባቶቻችን አንተን ሲያመሰግኑበት የነበረ፥ ቅዱስና ውብ የሆነው ቤተ መቅደስህ በእሳት ጋይቶአል፤ የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ፈራርሰዋል።

ኢሳይያስ 64:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድ! ምነው ተራሮችም ቢናወጡ! እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ እንዲገለጥ፥ አሕዛብም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ፤ ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ አንተ ወረድህ፥ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ። ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ማንም አልሰሙም፥ የትኛውም ጆሮ አልተቀበለውም፥ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ አምላካችን በቀር ሌላ ማንም አላየውም። ጽድቅን የሚያደርገውን፥ በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እኛ ኃጢአት ሠራን፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጥተህ ነበር፤ ፊትህን ስለሰወርክብን እኛ ተሳሳትን። ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፥ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል። አሁን ግን፥ አቤቱ ጌታ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን። አቤቱ ጌታ፥ እጅግ አትቈጣ፥ ለዘለዓለምም ኃጢአትን አታስብ፤ እነሆ፥ እባክህ፥ ተመልከት፥ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን። የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ፥ ኢየሩሳሌምም የተተወች ሆናለች። አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፤ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈራርሷል።