የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 64:1-11

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 64:1-11 አማ2000

ሰማ​ይን ብት​ከ​ፍት ከአ​ንተ የተ​ነሣ ተራ​ሮች ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ይቀ​ል​ጣ​ሉም። አደሮ ማር በእ​ሳት ፊት እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ እን​ዲሁ ጠላ​ቶ​ች​ህን እሳት ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ስም​ህም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይታ​ወ​ቃል፤ አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ። የክ​ብ​ር​ህ​ንም ሥራ ባደ​ረ​ግህ ጊዜ፥ ተራ​ሮች በፊ​ትህ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ። ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም። በቸ​ር​ነ​ትህ የሚ​ታ​ገሡ መን​ገ​ድ​ህ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ይገ​ና​ኙ​ሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈ​ጣህ፤ እኛም ኀጢ​አት ሠራን፤ ስለ​ዚ​ህም ተሳ​ሳ​ትን። ሁላ​ችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነ​ናል፤ ጽድ​ቃ​ች​ንም ሁሉ እንደ መር​ገም ጨርቅ ነው፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ምክ​ን​ያት እንደ ቅጠል ረግ​ፈ​ናል፤ እን​ዲ​ሁም ነፋስ ጠራ​ርጎ ወስ​ዶ​ናል። ስም​ህ​ንም የሚ​ጠራ፥ አን​ተ​ንም የሚ​ያ​ስብ የለም፤ ፊት​ህ​ንም ከእኛ መል​ሰ​ሃል፤ ለኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ንም አሳ​ል​ፈህ ሰጥ​ተ​ኸ​ናል። አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አን​ተም ሠሪ​ያ​ችን ነህ፤ እኛም ሁላ​ችን የእ​ጅህ ሥራ ነን። አቤቱ፥ እጅግ አት​ቈጣ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አታ​ስብ፤ አሁ​ንም እባ​ክህ፥ ወደ እኛ ተመ​ል​ከት፤ እኛ ሁላ​ችን ሕዝ​ብህ ነን። የተ​ቀ​ደሱ ከተ​ሞ​ችህ ምድረ በዳ ሆነ​ዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውድማ ሆና​ለች። አባ​ቶ​ቻ​ችን ያከ​በ​ሩት ክብ​ራ​ችን ቤተ መቅ​ደ​ስህ በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አል፤ ያማ​ረ​ውም ስፍ​ራ​ችን ፈር​ሶ​አል።