የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕዝራ 10:7-17

ዕዝራ 10:7-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የም​ርኮ ልጆች ሁሉም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ዐዋጅ ነገረ “እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማ​ይ​መጣ ሁሉ እንደ ሽማ​ግ​ሎ​ችና እን​ዳ​ለ​ቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበ​ዝ​በዝ፤ እር​ሱም ከም​ር​ኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስ​ነ​ገረ። ሦስት ቀንም ሳያ​ልፍ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ሰዎች ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ​ዚህ ነገ​ርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጡ። ካህ​ኑም ዕዝራ ተነ​ሥቶ፥ “ተላ​ል​ፋ​ች​ኋል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን በደል ታበዙ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን ሴቶች አግ​ብ​ታ​ች​ኋል። አሁ​ንም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አድ​ርጉ፤ ከም​ድ​ርም አሕ​ዛ​ብና ከእ​ን​ግ​ዶች ሴቶች ተለዩ” አላ​ቸው። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “እንደ ተና​ገ​ር​ኸን እና​ደ​ርግ ዘንድ ይገ​ባ​ናል። ነገር ግን የሕ​ዝቡ ቍጥር ብዙ ነው፤ ጊዜ​ውም የት​ልቅ ዝናብ ጊዜ ነው፤ በሜ​ዳም ልን​ቆም አን​ች​ልም፤ በዚ​ህም ነገር እጅግ በድ​ለ​ና​ልና ይህ ሥራ የአ​ንድ ወይም የሁ​ለት ቀን ሥራ አይ​ደ​ለም። አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በጉ​ባ​ኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር የአ​ም​ላ​ካ​ችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡት በከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን ያሉት ሁሉ በተ​ቀ​ጠ​ረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የከ​ተ​ማው ሁሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ፈራ​ጆች ይምጡ።” ነገር ግን የአ​ሣ​ሄል ልጅ ዮና​ታ​ንና የቴ​ቁዋ ልጅ የሐ​ዝያ ስለ​ዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱ​ላ​ምና ሌዋ​ዊው ሰባ​ታ​ይም ይረ​ዱ​አ​ቸው ነበር። የስ​ደ​ተ​ኞ​ቹም ልጆች እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ሁሉም በየ​ስ​ማ​ቸው ተለዩ፤ በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ነገ​ሩን ይመ​ረ​ምሩ ዘንድ ተቀ​መጡ። እስከ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር እስከ መጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ድረስ ሠር​ተው እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡ​ትን ሰዎች ሁሉ መር​ም​ረው ጨረሱ።

ዕዝራ 10:7-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም ምርኮኞቹ ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ዐዋጅ ተነገረ፤ ዐዋጁም በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንም ሰው በሹማምቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፣ ራሱም ከምርኮኞቹ ጉባኤ እንዲወገድ የሚያዝ ነበር። ስለዚህ በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ በዘጠነኛው ወር በሃያኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ስለ ወቅቱ ጕዳይና ስለ ከባዱ ዝናብ በመጨነቅ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀምጠው ነበር። ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ታማኞች አልነበራችሁም፤ በእስራኤል በደል ላይ በደል በመጨመር ባዕዳን ሴቶችን አገባችሁ። አሁንም ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር ተናዘዙ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብና ከባዕዳን ሚስቶቻችሁ ተለዩ።” ጉባኤውም ሁሉ እንዲህ ሲሉ በታላቅ ድምፅ መለሱ፤ “እውነት ብለሃል፤ ያልኸውን መፈጸም ይገባናል። ይሁን እንጂ በዚህ የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው፤ ወቅቱም ክረምት ነው፤ ስለዚህ ውጭ መቆም አንችልም፤ ከዚህም በላይ በዚህ ነገር ብዙ ኀጢአት ስለ ሠራን፣ ይህ ጕዳይ በአንድና በሁለት ቀን የሚያልቅ አይደለም። ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም፣ በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቍጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋር በተወሰነው ቀን ይምጡ።” ይህንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው። ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤ በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡትን ወንዶች ሁሉ አጣርተው ጨረሱ።

ዕዝራ 10:7-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ምርኮኞቹም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ፥ እንደ አለቆቹና እንደ ሽማግሌዎችም ምክር በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ሁሉ ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፥ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ እንዲለይ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አዋጅ ነገሩ። ሦስት ቀንም ሳያልፍ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ። ካህኑም ዕዝራ ተነሥቶ፦ “ተላልፋችኋል፤ የእስራኤልን በደል ታበዙ ዘንድ እንግዶችን ሴቶች አግብታችኋል። አሁንም ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር ተናዘዙ፤ ደስ የሚያሰኘውንም አድርጉ፤ ከምድርም አሕዛብና ከእንግዶች ሴቶች ተለዩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ በታላቅ ድምፅ መልሰው እንዲህ አሉ፦ “እንደ ተናገርኸን እናደርግ ዘንድ ይገባናል። ነገር ግን የሕዝቡ ቍጥር ብዙ ነው፤ ጊዜውም የትልቅ ዝናብ ጊዜ ነው፤ በሜዳም ልንቆም አንችልም፤ በዚህም ነገር እጅግ በድለናልና ይህ ሥራ የአንድ ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም። አለቆቻችንም በጉባኤው ሁሉ ፋንታ ይቁሙ፤ ስለዚህም ነገር የአምላካችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት በከተሞቻችን ያሉት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሁሉ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።” ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ሜሱላምና ሌዋዊዉ ሳባታይ ረዱአቸው። ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፤ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፤ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ። እስከ መጀመሪያው ወር እስከ መጀመሪያው ቀን ድረስ ሠርተው፥ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡትን ሰዎች ሁሉ መርምረው ጨረሱ።

ዕዝራ 10:7-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከምርኮ የተመለሱትም ሁሉ በኢየሩሳሌም ይሰበሰቡ ዘንድ በመላው ኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ታወጀ። ይህም ሁሉ በሕዝቡ መሪዎች ምክርና ትእዛዝ የተወሰነ ነበር፤ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ወደዚህ ስብሰባ መምጣት ያልቻለ ማንም ሰው ቢኖር ንብረቱ ሁሉ እንደሚወረስና ከምርኮ ከተመቱት ሰዎች ጉባኤ እንደሚወገድ ተነገረው። ይህም ጥሪ እንደ ተላለፈ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ በይሁዳና በብንያም ግዛት የሚኖሩት ሁሉ ዘጠነኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው በቤተ መቅደሱ አደባባይ ተሰበሰቡ፤ ሰዎቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት በተሰበሰቡበት ጉዳይና በዝናቡ ምክንያት እየተንቀጠቀጡ ቆመው ነበር። ካህኑ ዕዝራም ቆሞ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “እነሆ እምነታችሁን አጓድላችሁ ተገኝታችኋል፤ ባዕዳን ሴቶችንም በማግባታችሁ ምክንያት በእስራኤል ላይ የበደልን ዕዳ አምጥታችኋል። ከአሁን በኋላ እንግዲህ በቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአታችሁን ሁሉ ተናዘዙ፤ እርሱም ደስ የሚሰኝበትን ነገር ሁሉ አድርጉ፤ በምድራችን ከሚኖሩት ባዕዳን ሁሉ ራቁ፤ ያገባችኋቸውንም ባዕዳን ሴቶች ወዲያ አስወግዱ።” የተሰበሰቡትም ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “አንተ የምትለውን ሁሉ እናደርጋለን!” አሉ። ንግግራቸውንም በመቀጠል እንዲህ አሉት፦ “እነሆ እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው፤ ከዚህም ጋር በከባድ ሁኔታ እየዘነበ ነው፤ መጠለያ በሌለበት በዚህ ስፍራ መቆም አልቻልንም፤ በዚህ ኃጢአት የተበከልነውም ብዙዎች በመሆናችን ይህን ሁሉ ነገር በአንድ ወይም በሁለት ቀኖች ውስጥ መፈጸም አይቻልም። ስለዚህ አለቆቻችን በዚሁ በኢየሩሳሌም ጉዳዩን ያጥኑት፤ ከዚህም በኋላ ባዕድ ሴት ያገባ ሁሉ እያንዳንዱ በሚሰጠው የቀጠሮ ቀን ከሚኖርባት ከተማ መሪዎችና ዳኞች ጋር እየመጣ ውሳኔውን ይቀበል፤ እግዚአብሔር የተቈጣበትም ሁኔታ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ይበርዳል።” ይህም በተነገረ ጊዜ መሹላምና ሻበታይ ተብሎ የሚጠራው አንድ ሌዋዊ ድጋፍ ከሰጡአቸው ከዐሣሔል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ከሆነው ከያሕዘያ በቀር ሌላ ተቃዋሚ አልነበረም። ከምርኮ የተመለሱት ሁሉ ይህንኑ ዕቅድ ለመቀበል ተስማሙ፤ ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ከጐሣ መሪዎች መካከል መርጦ አስፈጻሚዎችን በመሾም ስም ዝርዝራቸውን መዝግቦ አኖረ፤ እነርሱም ዐሥረኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመርመር ጀመሩ። በሚቀጥለው ዓመት በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ከባዕዳን ሴቶች ጋር የተጋቡትን ሰዎች ጉዳይ በሙሉ መርምረው ጨረሱ።

ዕዝራ 10:7-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ምርኮኞቹ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አዋጅ ነገሩ። በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ሁሉ እንደ አለቆቹና እንደ ሽማግሌዎቹ ምክር ንብረቱ ሁሉ ይወረስ፥ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ ይለይ፤ በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ። ካህኑ ዕዝራም ተነሣ እንዲህም አላቸው፦ “አልታመናችሁም፥ የእስራኤልን በደል ልታበዙ እንግዶች ሴቶችን አግብታችኋል። ስለዚህ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለጌታ ተናዘዙ፥ ፈቃዱንም አድርጉ፤ እራሳችሁንም ከምድሪቱ ሕዝቦችና ከእንግዶች ሴቶች ለዩ።” ጉባኤውም ሁሉ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብለው መለሱ፦ “እንደ ተናገርኸን ማድረግ ይገባናል። ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ጊዜውም የዝናብ ጊዜ ነው፥ በውጭ ልንቆም አንችልም፥ በዚህ ነገር እጅግ ተላልፈናልና ይህ ሥራ የአንድ ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም። አለቆቻችንም ለጉባኤው ሁሉ ይቁሙ፥ ስለዚህም ነገር የአምላካችን የነደደው ቁጣ ከእኛ እንዲመለስ፥ እያንዳንዳቸው በከተሞቻችን ያሉ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።” የዐሣሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያሕዝያ ብቻ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ምሹላምና ሌዋዊውም ሻብታይ ደገፏቸው። ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፥ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችን መሪዎች መረጠ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፥ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፥ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ሊመረምሩ ተቀመጡ። እስከ መጀመሪያው ወር፥ መጀመሪያው ቀን ድረስ እንግዶች ሴቶች ያገቡትን ሰዎች ሁሉ መርምረው ጨረሱ።