የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዕዝራ 10

10
ከባ​ዕ​ዳን ወገን የተ​ጋቡ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እን​ዲ​ፋቱ ስለ ማድ​ረግ
1ዕዝ​ራም እያ​ለ​ቀ​ሰና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​ወ​ደቀ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ የወ​ን​ድና የሴት፥ የሕ​ፃ​ና​ትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰበ፤ ሕዝ​ቡም እጅግ አለ​ቀሱ። 2ከኤ​ላም ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውም የኢ​ያ​ሔል ልጅ ሴኬ​ንያ ዕዝ​ራን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሰ​ናል” ይላል። የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ እን​ግ​ዶች ሴቶ​ችን አግ​ብ​ተ​ናል፤ አሁን ግን ስለ​ዚህ ነገር ገና ለእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ አለ። 3አሁ​ንም እንደ ጌታ​ዬና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ትእ​ዛዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ምክር፥ ሴቶ​ችን ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን እን​ሰ​ድድ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ጋር ቃል ኪዳን እና​ድ​ርግ። ተነሥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ትእ​ዛዝ ገሥ​ፃ​ቸው፤ እንደ ሕጉም ያድ​ርጉ፤ 4ይህም ነገር ለአ​ንተ ይገ​ባ​ልና፥ እኛም ከአ​ንተ ጋር ነንና ተነሣ፤ በርታ፤ አድ​ር​ገ​ውም።”
5ዕዝ​ራም ተነሣ፤ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ እን​ደ​ዚህ ቃል ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ማሉ። 6ዕዝ​ራም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ተነ​ሥቶ ወደ ኤሊ​ያ​ሴብ ልጅ ወደ ዮሐ​ናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም ኀጢ​አት ያለ​ቅስ ነበ​ርና ገብቶ እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። 7የም​ርኮ ልጆች ሁሉም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ዐዋጅ ነገረ 8“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማ​ይ​መጣ ሁሉ እንደ ሽማ​ግ​ሎ​ችና እን​ዳ​ለ​ቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበ​ዝ​በዝ፤ እር​ሱም ከም​ር​ኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስ​ነ​ገረ።
9ሦስት ቀንም ሳያ​ልፍ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ሰዎች ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ​ዚህ ነገ​ርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጡ። 10ካህ​ኑም ዕዝራ ተነ​ሥቶ፥ “ተላ​ል​ፋ​ች​ኋል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን በደል ታበዙ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን ሴቶች አግ​ብ​ታ​ች​ኋል። 11አሁ​ንም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤#ዕብ. “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ዘዙ” ይላል። ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አድ​ርጉ፤ ከም​ድ​ርም አሕ​ዛ​ብና ከእ​ን​ግ​ዶች ሴቶች ተለዩ” አላ​ቸው። 12ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “እንደ ተና​ገ​ር​ኸን እና​ደ​ርግ ዘንድ ይገ​ባ​ናል። 13ነገር ግን የሕ​ዝቡ ቍጥር ብዙ ነው፤ ጊዜ​ውም የት​ልቅ ዝናብ ጊዜ ነው፤ በሜ​ዳም ልን​ቆም አን​ች​ልም፤ በዚ​ህም ነገር እጅግ በድ​ለ​ና​ልና ይህ ሥራ የአ​ንድ ወይም የሁ​ለት ቀን ሥራ አይ​ደ​ለም። 14አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በጉ​ባ​ኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር የአ​ም​ላ​ካ​ችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡት በከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን ያሉት ሁሉ በተ​ቀ​ጠ​ረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የከ​ተ​ማው ሁሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ፈራ​ጆች ይምጡ።” 15ነገር ግን የአ​ሣ​ሄል ልጅ ዮና​ታ​ንና የቴ​ቁዋ ልጅ የሐ​ዝያ ስለ​ዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤#ዕብ. “ይህን ነገር ተቃ​ወሙ ሜሱ​ላ​ምና ሌዋ​ዊው ሰበ​ታ​ይም ረዱ​አ​ቸው” ይላል። ሜሱ​ላ​ምና ሌዋ​ዊው ሰባ​ታ​ይም ይረ​ዱ​አ​ቸው ነበር።
16የስ​ደ​ተ​ኞ​ቹም ልጆች እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ሁሉም በየ​ስ​ማ​ቸው ተለዩ፤ በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ነገ​ሩን ይመ​ረ​ምሩ ዘንድ ተቀ​መጡ። 17እስከ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር እስከ መጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ድረስ ሠር​ተው እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡ​ትን ሰዎች ሁሉ መር​ም​ረው ጨረሱ።
ከአ​ሕ​ዛብ ሴቶች ሚስ​ትን ያገቡ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች
18ከካ​ህ​ና​ቱም ወገን ልጆች እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ ከኢ​ያሱ ልጆ​ችና ከወ​ን​ድ​ሞቹ ማዓ​ሥያ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኦሬም፥ ገዳ​ልያ። 19ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይፈቱ ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡ፤ ስለ በደ​ላ​ቸ​ውም ከመ​ን​ጋው አንድ አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ። 20ከኢ​ሚር ልጆ​ችም አና​ኒና ዝብ​ድያ። 21ከኤ​ራም ልጆ​ችም መሳ​ሔል፥ ኤልያ፥ ሴሚያ፥ ያሔል፥ ዖዝያ። 22ከጳ​ሰ​ኮር ልጆ​ችም ኤል​ዮና፥ መሐ​ሰዓ፥ ይስ​ማ​ኤል፥ ናት​ና​ኤል፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ኤልሣ። 23ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሰሜኢ፥ ቆሊ​ጣስ የሚ​ባል ቆልያ፥ ፈዲሓ፥ ይሁዳ፥ አል​ዓ​ዛር። 24ከመ​ዘ​ም​ራ​ንም ኤል​ያ​ሴብ፤ ከበ​ረ​ኞ​ችም ሰሎም፥ ጤሎም፥ ኡሪ። 25ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ከፋ​ሮስ ልጆች ራምያ፥ ዖዝያ፥ መል​ክያ፥ ሚያ​ሚን፥ አል​ዓ​ዛር፥ መል​ክያ፥ ቤን​ያህ። 26ከኤ​ላም ልጆ​ችም መታ​ንያ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ኤል፥ አብዲ፥ ይሬ​ሞት፥ ኤልያ። 27ከዛቱ ልጆ​ችም ዔሊ​ዔ​ናይ፥ ኤል​ያ​ሴብ፥ መታ​ንያ፥ ኤር​ሞት፥ ዛባድ፥ ዓዚዛ። 28ከቤ​ባይ ልጆ​ችም ዮሐ​ናን፥ ሐና​ንያ፥ ዘባይ፥ አጥ​ላይ። 29ከባኒ ልጆ​ችም ሜሱ​ላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብ፥ ሳዓል፥ ራሞት። 30ከፈ​ሐት ሞዓብ ልጆ​ችም ዓድና፥ ክላል፥ በና​ያስ፥ ማዕ​ሴያ፥ መታ​ንያ፥ ባስ​ል​ኤል፥ በነዊ፥ ምናሴ። 31ከኤ​ራም ልጆ​ችም አል​ዓ​ዛር፥ ይሲያ፥ ሚል​ክያ፥ ሰማያ፥ ስም​ዖን፥ 32ብን​ያም፥ መሉክ፥ ሰማ​ርያ። 33ከሐ​ሱም ልጆ​ችም መታ​ንያ፥ መታታ፥ ዛባድ፥ ኤሊ​ፋ​ልጥ፥ ይሬ​ማይ፥ ምናሴ፥ ሰሜኢ። 34ከባኒ ልጆ​ችም ማዕ​ዳይ፥ ዓም​ራም፥ ኡኤል፥ 35በና​ያስ፥ በዳያ፥ ኬል​ቅያ፥ 36ውንያ፥ መሪ​ሙት፥ ኤል​ያ​ሴብ፤ 37መታ​ንያ፥ መት​ናይ፥ የዕሡ፤ 38የባ​ኔይ ልጆ​ችና የሰ​ሜይ ልጆች፤ 39ሰሌ​ምያ፥ ናታን፥ ሐዳያ፤ 40መክ​ነ​ድ​ባይ፥ ሴሴይ፥ ሰራይ፤ 41ኤዛ​ር​ኤል፥ ሰሌ​ምያ፥ ሰማ​ርያ፥ 42ሰሎም፥ አማ​ርያ፥ ዮሴፍ። 43ከናቡ ልጆ​ችም ይዒ​ኤል፥ መታ​ትያ፥ ዛባድ፥ ዛብ​ንያ፥ ያዳይ፥ ኢዮ​ኤል፥ በና​ያስ። 44እነ​ዚህ ሁሉ እን​ግ​ዶ​ቹን ሚስ​ቶች አግ​ብ​ተው ነበር፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም ሚስ​ቶች ዐያ​ሌ​ዎቹ ልጆ​ችን ወል​ደው ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ