የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 1

1
1የኬ​ል​ቅያ ልጅ የነ​ህ​ምያ ቃል።
በሃ​ያ​ኛው ዓመት በካ​ሴሎ ወር እን​ዲህ ሆነ፤ እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ 2ከወ​ን​ድ​ሞች አንዱ ሐናኒ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይ​ሁዳ መጡ፤ እኔም የዳ​ኑ​ትን፥ ከም​ር​ኮም የተ​ረ​ፉ​ትን የአ​ይ​ሁ​ድን ነገር፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ነገር ጠየ​ቅ​ኋ​ቸው። 3እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።
4ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦ 5“አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥ 6እኔ ባሪ​ያህ ዛሬ በፊ​ትህ ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሌሊ​ትና ቀን የም​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችህ ያድ​ምጡ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ይከ​ፈቱ፤ በአ​ንተ ላይም ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ኀጢ​አት ለአ​ንተ እን​ና​ዘ​ዛ​ለን፤ እኔም፥ የአ​ባ​ቴም ቤት በድ​ለ​ናል። 7እኛም በአ​ንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠር​ተ​ናል፤ ለባ​ሪ​ያ​ህም ለሙሴ ያዘ​ዝ​ኸ​ውን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ሕጉ​ንም አል​ጠ​በ​ቅ​ንም።
8“አሁ​ንም ለሙሴ ለባ​ሪ​ያህ እን​ዲህ ስትል ያዘ​ዝ​ሃ​ትን ነገር አስብ። ብት​በ​ድ​ሉም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ። 9ወደ እኔ ብት​መ​ለሱ ግን፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም ምንም ከእ​ና​ንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበ​ተኑ፥ ከዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስሜም ይኖ​ር​በት ዘንድ ወደ መረ​ጥ​ሁት ስፍራ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።
10“እነ​ዚ​ህም በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በብ​ርቱ እጅህ የተ​ቤ​ዥ​ሃ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህና ሕዝ​ብህ ናቸው። 11ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባ​ሪ​ያ​ህን ጸሎት፥ ስም​ህ​ንም ይፈሩ ዘንድ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ጸሎት ያድ​ምጥ፤ ዛሬም ለባ​ሪ​ያህ አከ​ና​ው​ን​ለት፤ በዚ​ህም ሰው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጠው።” እኔም ለን​ጉሡ ጠጅ አሳ​ላፊ ነበ​ርሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ