የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ዕዝራ 10

10
የሕዝቡ መልስ
1ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት በግንባሩ ወድቆ እያለቀሰ በሚጸልይበትና በሚናዘዝበት ጊዜ፤ ወንዶች፥ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙበት እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፥ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ። 2ከዔላም ልጆች ወገን የነበረ፥ የይሒኤል ልጅ ሽካንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለአምላካችን ታማኞች አልሆንም፥ የምድሪቱን ሕዝቦች እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፥ አሁንም ግን በዚህ ነገር ለእስራኤል ተስፋ አለ። 3ስለዚህ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ፥ ሚስቶችን ሁሉ ከእነርሱ የተወለዱትንም እንላካቸው፤ እንደ ጌታዬና በአምላካችን ትእዛዝ እንደሚንቀጠቀጡ#10፥3 እንደሚንቀጠቀጡ፤ እንደሚፈሩ ሕዝቦች ምክር፥ እንደ ሕጉም ይደረግ። 4ተነሥ ይህም ነገር የአንተ ሥራ ነውና፥ እኛም ከአንተ ጋር እንሆናለን፤ በርታ፥ አድርገውም።”
5ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹን፥ ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልንም ሁሉ እንደዚህ ቃል እንዲያደርጉ አስማላቸው፥ እነርሱም ማሉ።
የእንግዶች ሴቶችና ልጆቻቸው ተቀባይነት ማጣት
6ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሣ፥ ወደ ኤልያሺብ ልጅ ወደ ይሆሐናን ክፍል ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹ አለመታመን አዝኖ ነበርና በዚያ ገብቶ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። 7ምርኮኞቹ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አዋጅ ነገሩ። 8በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ሁሉ እንደ አለቆቹና እንደ ሽማግሌዎቹ ምክር ንብረቱ ሁሉ ይወረስ፥ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ ይለይ፤
9በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ። 10ካህኑ ዕዝራም ተነሣ እንዲህም አላቸው፦ “አልታመናችሁም፥ የእስራኤልን በደል ልታበዙ እንግዶች ሴቶችን አግብታችኋል። 11ስለዚህ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለጌታ ተናዘዙ፥ ፈቃዱንም አድርጉ፤ እራሳችሁንም ከምድሪቱ ሕዝቦችና ከእንግዶች ሴቶች ለዩ።” 12ጉባኤውም ሁሉ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብለው መለሱ፦ “እንደ ተናገርኸን ማድረግ ይገባናል። 13ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ጊዜውም የዝናብ ጊዜ ነው፥ በውጭ ልንቆም አንችልም፥ በዚህ ነገር እጅግ ተላልፈናልና ይህ ሥራ የአንድ ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም። 14አለቆቻችንም ለጉባኤው ሁሉ ይቁሙ፥ ስለዚህም ነገር የአምላካችን የነደደው ቁጣ ከእኛ እንዲመለስ፥ እያንዳንዳቸው በከተሞቻችን ያሉ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።” 15የዐሣሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያሕዝያ ብቻ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ምሹላምና ሌዋዊውም ሻብታይ ደገፏቸው።
16ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፥ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችን መሪዎች መረጠ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፥ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፥ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ሊመረምሩ ተቀመጡ። 17እስከ መጀመሪያው ወር፥ መጀመሪያው ቀን ድረስ እንግዶች ሴቶች ያገቡትን ሰዎች ሁሉ መርምረው ጨረሱ።
18ከካህናቱ ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፥ ከዮፃዳቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ፥ ማዕሤያ፥ ኤሊዔዜር፥ ያሪብና ግዳልያ፤ 19ሚስቶቻቸውን ለማሰናበት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም ከመንጋው አንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ። 20ከኢሜርም ልጆች፥ ሐናኒና ዝባድያ፤ 21ከሐሪም ልጆችም፦ ማዕሤያ፥ ኤልያ፥ ሽማዕያ፥ ይሒኤል፥ ዑዚያ፤ 22ከፓሽሑር ልጆችም፦ ኤልዮዔናይ፥ ማዕሤያ፥ ዪሽማኤል፥ ናትናኤል፥ ዮዛባድ፥ ኤልዓሣ።
23ከሌዋውያንም፦ ዮዛባድ፥ ሺምዒ፥ ቅሊጣ የሚባል ቄላያ፥ ፕታሕያ፥ ይሁዳ፥ ኤሊዔዜር።
24ከመዘምራንም፦ ኤልያሺብ፥ ከበረኞችም፥ ሻሉም፥ ጤሌምና ኡሪ።
25ከእስራኤልም ከፓርዖሽ ልጆች፦ ራምያ፥ ዪዚያ፥ ማልኪያ፥ ሚያሚን፥ ኤልዓዛር፥ ማልኪያና ብናያስ። 26ከዔላም ልጆችም፦ ማታንያ፥ ዘካርያ፥ ይሒኤል፥ ዓብዲ፥ የሬሞትና ኤሊያ። 27ከዛቱ ልጆችም፦ ዔልዮዔያይ፥ ኤልያሺብ፥ ማታንያ፥ ይሬሞት፥ ዛባድ፥ ዓዚዛ። 28ከቤባይ ልጆችም፦ ይሆሐናን፥ ሐናንያ፥ ዘባይ፥ ዓትላይ። 29ከባኒ ልጆችም፦ ምሹላም፥ ማሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሹብ፥ ሽአል፥ ራሞት። 30ከፓሐት ሞዓብ ልጆች፦ ዓድና፥ ክላል፥ ብናያስ፥ ማዕሤያ፥ ማታንያ፥ ብጻልኤል፥ ቢኑይና ምናሴ። 31ከሓሪም ልጆችም፦ ኤሊዔዜር፥ ዪሺያ፥ ማልኪያ፥ ሽማዕያ፥ ስምዖን፥ 32ብንያም፥ ማሉክና ሽማርያ። 33ከሐሹም ልጆች፦ ማትናይ፥ ማታታ፥ ዛባድ፥ ኤሊፌሌጥ፥ ይሬማይ፥ ምናሴ፥ ሺምዒ። 34ከባኒ ልጆችም፦ ማዕዳይ፥ ዓምራምና ኡኤል፥ 35ብናያ፥ ቤድያ፥ ክሉሂ 36ዋንያ፥ ምሬሞት፥ ኤልያሺብ፥ 37ማታንያ፥ ማትናይና ያዐሦ፥ 38ባኒ፥ ቢኑይ፥ ሺምዒ፥ 39ሼሌምያ፥ ናታንና ዓዳያ 40ማክናድባይ፥ ሻሻይ፥ ሻራይ፥ 41ዓዛርኤል፥ ሼሌምያሁ፥ ሽማርያ፥ 42ሻሉም፥ አማርያና ዮሴፍ። 43ከንቦ ልጆችም፦ ይዒኤል፥ ማቲትያ፥ ዛባድ፥ ዝቢና፥ ያዳይ፥ ዮኤል፥ ብናያ። 44እነዚህ ሁሉ እንግዶች ሚስቶችን አግብተው ነበር፤ ከእነዚህም አንዳንዶቹ ሚስቶች ልጆችን ወልደው ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ