የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ነህምያ መግቢያ

መግቢያ
በመጽሐፈ ነህምያ ውስጥ ጐላ ብሎ የሚታየው ነገር ነህምያ በእግዚአብሔር ላይ ስለ ነበረው ጽኑ መታመንና ወደ እግዚአብሔርም ስላቀረባቸው ጸሎቶች የሚያወሳው ታሪክ ነው።
መጽሐፈ ነህምያ ሦስት ዐበይት ነጥቦችን ይዟል፦
አንደኛው፥ ይሁዳን እንዲያስተዳድር በፋርስ ንጉሠ ነገሥት በተላከው በነህምያ መሪነት የኢየሩሳሌም ቅጽሮች መታደሳቸውን የሚያስረዳው ታሪክ ነው፤ ከዚህም በቀር ነህምያ ቁሳዊና ሃይማኖታዊ ተሐድሶ ማስረዳቱ፤
ሁለተኛው፥ የእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ በዕዝራ ስለ መነበቡና ሕዝቡ ኃጢአታቸውን ስለ መናዘዛቸው መተረከ፤
ሦስተኛው፥ ነህምያ የይሁዳ አገረ ገዢ ሆኖ ስላካሄዳቸው ሌሎች ተግባሮች መገለጡ ናቸው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ንጉሥ አርጤክስስ ነህምያን ወደ ኢየሩሳሌም መላኩ (1፥1—2፥10)
የኢየሩሳሌም ግንብ እንደገና መገንባቱ (2፥11—4፥17)
ነህምያ ስለ ድኾች ማሰቡ (5፥1-19)
የጠላት አድማም እያለ የግንቡ ሥራ ማለቁ (6፥1—7፥3)
የምርኮ ተመላሾች (7፥4-72)
ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ ለሕዝቡ ማንበቡ፥ የዳስ በዓልን ማክበራቸው (8፥1-18)
ሕዝቡ ኃጢአቱን መናዘዙ (9፥1-37)
ለእግዚአብሔር ሕግ ለመታዘዝ የስምምነት ውል መፈረማቸው (10፥1-39)
በይሁዳና በየሩሳሌም የሰፈሩ ሰዎች (11፥1-36)
ከምርኮ የተመለሱ ካህናትና ሌዋውያን (12፥1-26)
ነህምያ የከተማውን ግንብ ማስመረቁ (12፥27-47)
ነህምያ ያደረገው ለውጥ (13፥1-31)
ምዕራፍ

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ