2 ሳሙኤል 22:1-18

2 ሳሙኤል 22:1-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ፣ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፤ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ ከዐመፀኛ ሰዎችም ታድነኛለህ። “ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ። የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ። “በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ። ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ። ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ። ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ። በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ። ጨለማው በዙሪያው እንዲከብበው፣ ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ። በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣ የመብረቅ ብልጭታ ወጣ። እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ። ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው። ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫው ከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታየ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ። “ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ። ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።

2 ሳሙኤል 22:1-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሳ​ኦል እጅና ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ እጅ ባዳ​ነው ቀን የዚ​ህን መዝ​ሙር ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ። እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለቴ፥ አም​ባ​ዬም፥ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠባ​ቂዬ ነው፤ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ፤ ጋሻ​ዬና የመ​ድ​ኀ​ኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ከግ​ፈኛ ታድ​ነ​ኛ​ለህ። ምስ​ጋና የሚ​ገ​ባ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ራ​ለሁ፤ ከጠ​ላ​ቶቼም እድ​ና​ለሁ። የሞት ጭንቅ ያዘኝ፤ የዐ​መፅ ጎር​ፍም አስ​ፈ​ራኝ፤ የሞት ጣር ከበ​በኝ፤ የሞት ወጥ​መ​ድም ደረ​ሰ​ብኝ። በጨ​ነ​ቀኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራ​ሁት፤ እን​ዲ​ረ​ዳ​ኝም ወደ አም​ላኬ ጮኽሁ፤ ከመ​ቅ​ደ​ሱም ቃሌን ሰማኝ፤ ጩኸ​ቴም በፊቱ ወደ ጆሮ​ዎቹ ገባ። ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ ተና​ወ​ጠ​ችም፤ የሰ​ማይ መሠ​ረ​ቶ​ችም ተነ​ቃ​ነቁ፤ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና። ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፤ ከአ​ፉም የሚ​በላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ ተቃ​ጠለ። ሰማ​ዮ​ችን አዘ​ነ​በለ፤ ወረ​ደም፤ ጭጋ​ግም ከእ​ግሩ በታች ነበረ። በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ ተቀ​ምጦ በረረ፤ በነ​ፋ​ስም ክን​ፎች ሆኖ ታየ፤ መሰ​ወ​ር​ያ​ውን ጨለማ አደ​ረገ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የነ​በ​ረ​ውን ድን​ኳን የውኃ ጨለማ አደ​ረገ፤ በደ​መ​ናም አገ​ዘ​ፈው። በፊ​ቱም ካለው ብር​ሃን የተ​ነሣ ፍም ተቃ​ጠለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ አን​ጐ​ደ​ጐደ፤ ልዑ​ልም ቃሉን ሰጠ። ፍላ​ጻ​ውን ላከ፤ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቅ​ንም አሰ​ምቶ አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣፅ የተ​ነሣ፥ ከመ​ዓ​ቱም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥ የባ​ሕር ፈሳ​ሾች ታዩ፤ የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ። ከላይ ላከ፤ ወሰ​ደ​ኝም፤ ከብዙ ውኆ​ችም አወ​ጣኝ። ከብ​ር​ቱ​ዎች ጠላ​ቶቼ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ኝም አዳ​ነኝ፤ በር​ት​ተ​ው​ብኝ ነበ​ርና።

2 ሳሙኤል 22:1-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ፣ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፤ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ ከዐመፀኛ ሰዎችም ታድነኛለህ። “ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ። የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ። “በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ። ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ። ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ። ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ። በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ። ጨለማው በዙሪያው እንዲከብበው፣ ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ። በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣ የመብረቅ ብልጭታ ወጣ። እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ። ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው። ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫው ከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታየ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ። “ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ። ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።

2 ሳሙኤል 22:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ እጅ ሁሉ ባዳነው ቀን የዚህን ቅኔ ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ። እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፥ እግዚአብሔር ጠባቂያ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፥ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኃኒቴ ሆይ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ። የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፥ የሲኦል ጣር ከበበኝ፥ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ። በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፥ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኽቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ። ምድርም ተንቀጠቀጠች፥ ተናወጠችም፥ የሰማዮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቆጥቶአልና ተንቀጠቀጡ። ከቁጣው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፥ ፍምም ከእርሱ በራ። ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ፥ ወረደም፥ ጨለማም ከእግሩ በታች ነበረ። በኪሩብም ላይ ተቀምቶ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ ሆኖ ታየ፥ መሰወርያውን ጨለማ፥ በዙሪያውም የነበረውን ድንኳን፥ በደመና ውስጥ የነበረ የጨለማ ውኃ አደረገ። በፊቱም ካለው ብርሃን የተነሣ ፍም ተቃጠለ። እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጎደጎደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ፥ ፍላጻውን ላከ፥ በተናቸውም፥ መብረቆችን ላከ፥ አወካቸውም። ከእግዚአብሔር ዘለፋ፥ ከመዓቱም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የባሕር ፈሳሾች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ። ከላይ ሰደደ፥ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ። ከብርቱዎች ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።

2 ሳሙኤል 22:1-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ዳዊትን ከሳኦልና ከሌሎቹም ጠላቶቹ እጅ በመታደግ ባዳነው ጊዜ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ክብር ዘመረ፦ እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬ የደኅንነቴ ኀይል፥ ጠንካራ ምሽጌ ነው። አንተ የመዳን አለቴ ነህ፤ እንዲሁም ጋሻዬ፥ የጦር መሣሪያዬና ከለላዬ ነህ፤ ከኀያላን እጅ ታድነኛለህ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ እርሱም ከጠላቶቼ ያድነኛል። የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፤ የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ፤ መከራ በደረሰብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም አምላኬን ለመንኩት። በመቅደሱም ሆኖ ድምፄን ሰማ ጩኸቴንም አደመጠ። እግዚአብሔር ስለ ተቈጣ ምድር ተናወጠች፤ ተንቀጠቀጠችም፤ የአድማስ መሠረቶች ተናጉ፤ ተነቃነቁም። ከአፍንጫው የቊጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉም የሚባላ የእሳት ነበልባልና የሚያቃጥል ፍም ወጣ። ሰማይን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቊር ደመና ነበረ፤ በኪሩቤል ላይ ሆኖ በረረ፤ በነፋስም ክንፎች ላይ ሆኖ መጠቀ። ሁለንተናውን በጨለማ ሸፈነ። በውሃ የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ከቦታል። በፊቱ ካለው ነጸብራቅ የተነሣ ጥቅጥቅ ያለ ደመና፥ በረዶና የሚነድ እሳት መጣ። እግዚአብሔር ከሰማይ አንጐዳጐደ፤ ልዑል እግዚአብሔር ድምፁን አሰማ። ፍላጻውን ከቀስቱ አስፈነጠረ፤ ጠላቶቹንም በተናቸው፤ በመብረቁም ብልጭታ አሳደዳቸው። እግዚአብሔርም ከአፍንጫው ከሚወጣው የእስትንፋስ ወላፈንና በግሣጼው የባሕሩ ውስጥ ወለል ታየ፥ የምድሩም መሠረት ተገለጠ። እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ እጁን በመዘርጋት ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ። በጣም በርትተውብኝ ከነበሩት ከኀይለኞች ጠላቶቼና ከሚጠሉኝ ሰዎች ሁሉ እጅ እግዚአብሔር አዳነኝ።

2 ሳሙኤል 22:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታ ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፥ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለጌታ ዘመረ፤ እንዲህም አለ፤ ጌታ ዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምደገፍበት፥ ዐለቴ፥ ጋሻዬና የመዳኔ ቀንድ ነው። እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፥ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ አንተ ከጨካኞች ታድነኛለህ። ምስጋና የሚገባውን ጌታን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። የሞት ሞገድ ከበበኝ፤ የጥፋትም ጐርፍ አጥለቀለቀኝ። የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ። በጨነቀኝ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ። ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቆጥቶአልና ራዱ። ከአፍንጫው የቁጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከእርሱ የሚንበለበል ፍም ወጣ። ሰማያትን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ። በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ ሲከንፍ ታየ። ሁለንተናውን በጨለማ ሰወረ፥ በውሃ በተሞላ ጥቅጥቅ ደመና፥ ራሱን ከበበ። በፊቱ ካለው ብርሃን የእሳት ፍም ነደደ። ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፤ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ። ፍላጻውን ሰደደ፤ በተናቸውም፤ በመብረቁም ብልጭታ አወካቸው። ከጌታ ተግሣጽ፥ ከአፍንጫው ከሚወጣው፥ ከእስትንፋሱ ቁጣ የተነሣ፥ የባሕር መተላለፊያዎች ታዩ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ። ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ። በርትተውብኝ ነበርና፥ ከብርቱ ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም ታደገኝ።