መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 22

22
የዳ​ዊት መዝ​ሙር ከጠ​ላ​ቶቹ በዳነ ጊዜ
(መዝ. 17)
1ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሳ​ኦል እጅና ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ እጅ ባዳ​ነው ቀን የዚ​ህን መዝ​ሙር ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ።
2እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለቴ፥ አም​ባ​ዬም፥ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነው፤
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠባ​ቂዬ ነው፤ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ፤
ጋሻ​ዬና የመ​ድ​ኀ​ኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥
መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ከግ​ፈኛ ታድ​ነ​ኛ​ለህ።
4ምስ​ጋና የሚ​ገ​ባ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ራ​ለሁ፤
ከጠ​ላ​ቶቼም እድ​ና​ለሁ።
5የሞት ጭንቅ ያዘኝ፤
የዐ​መፅ ጎር​ፍም አስ​ፈ​ራኝ፤
6የሞት ጣር ከበ​በኝ፤
የሞት ወጥ​መ​ድም ደረ​ሰ​ብኝ።
7በጨ​ነ​ቀኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራ​ሁት፤
እን​ዲ​ረ​ዳ​ኝም ወደ አም​ላኬ ጮኽሁ፤
ከመ​ቅ​ደ​ሱም ቃሌን ሰማኝ፤
ጩኸ​ቴም በፊቱ ወደ ጆሮ​ዎቹ ገባ።
8ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ ተና​ወ​ጠ​ችም፤
የሰ​ማይ መሠ​ረ​ቶ​ችም ተነ​ቃ​ነቁ፤ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡም፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና።
9ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፤
ከአ​ፉም የሚ​በላ እሳት ነደደ፤
ፍምም ከእ​ርሱ ተቃ​ጠለ።
10ሰማ​ዮ​ችን አዘ​ነ​በለ፤ ወረ​ደም፤
ጭጋ​ግም ከእ​ግሩ በታች ነበረ።
11በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ ተቀ​ምጦ በረረ፤
በነ​ፋ​ስም ክን​ፎች ሆኖ ታየ፤
12መሰ​ወ​ር​ያ​ውን ጨለማ አደ​ረገ፤
በዙ​ሪ​ያ​ውም የነ​በ​ረ​ውን ድን​ኳን የውኃ ጨለማ አደ​ረገ፤
በደ​መ​ናም አገ​ዘ​ፈው።
13በፊ​ቱም ካለው ብር​ሃን የተ​ነሣ ፍም ተቃ​ጠለ።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ አን​ጐ​ደ​ጐደ፤
ልዑ​ልም ቃሉን ሰጠ።
15ፍላ​ጻ​ውን ላከ፤ በተ​ና​ቸ​ውም፤
መብ​ረ​ቅ​ንም አሰ​ምቶ አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው።
16ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣፅ የተ​ነሣ፥
ከመ​ዓ​ቱም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥
የባ​ሕር ፈሳ​ሾች ታዩ፤
የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ።
17ከላይ ላከ፤ ወሰ​ደ​ኝም፤
ከብዙ ውኆ​ችም አወ​ጣኝ።
18ከብ​ር​ቱ​ዎች ጠላ​ቶቼ፥
ከሚ​ጠ​ሉ​ኝም አዳ​ነኝ፤ በር​ት​ተ​ው​ብኝ ነበ​ርና።
19በመ​ከ​ራዬ ቀን ደረ​ሱ​ብኝ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ደጋ​ፊዬ ሆነ።
20ወደ ሰፊ ስፍ​ራም አወ​ጣኝ፤
ወድ​ዶ​ኛ​ልና አዳ​ነኝ።
21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድቄ ይከ​ፍ​ለ​ኛል፤
እንደ እጄ ንጽ​ሕ​ናም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል፤
22የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጠብ​ቄ​አ​ለ​ሁና፥
በአ​ም​ላ​ኬም አላ​መ​ፅ​ሁ​ምና።
23ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበ​ርና፤
ጽድ​ቁም ከእኔ አል​ራ​ቀ​ምና።
24በእ​ርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆ​ና​ለሁ፤
ከዐ​መ​ፃ​ዬም ራሴን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።
25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ጽድቄ፥
እንደ እጄም ንጽ​ሕና በዐ​ይ​ኖቹ ፊት መለ​ሰ​ልኝ።
26ከጻ​ድቅ ጋር ጻድቅ ትሆ​ና​ለህ፤
ከን​ጹሕ ሰውም ጋር ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ፤
27ከተ​መ​ረ​ጠም ጋር የተ​መ​ረጠ ትሆ​ና​ለህ፤
ከጠ​ማማ ጋርም ጠማማ ትሆ​ና​ለህ።
28አንተ የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሕዝብ ታድ​ና​ለ​ህና፤
የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ዐይ​ኖች ግን ታዋ​ር​ዳ​ለህ።
29አቤቱ! አንተ መብ​ራቴ ነህና፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጨለ​ማ​ዬን ያበ​ራ​ል​ኛ​ልና።
30በአ​ንተ ብቻ​ዬን እሮ​ጣ​ለ​ሁና፤
በአ​ም​ላ​ኬም ቅጥ​ሩን እዘ​ል​ላ​ለ​ሁና።
31የኀ​ያል አም​ላክ መን​ገድ ንጹሕ ነው፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤
በእ​ሳ​ትም የጋለ ነው፤
በእ​ር​ሱም ለሚ​ታ​መ​ኑት ጠባ​ቂ​ያ​ቸው ነው።
32ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ጽኑዕ ማን ነው?
ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በቀር ፈጣሪ ማን ነው?
33በኀ​ይል የሚ​ያ​ጸ​ናኝ ኀያል እርሱ ነው፤
መን​ገ​ዴ​ንም ንጹሕ አድ​ርጎ አዘ​ጋጀ፤
34እግ​ሮቼን እንደ ዋልያ እግ​ሮች አጸና፤
በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም አቆ​መኝ።
35ለእ​ጆቼ ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ራል፤
ለክ​ን​ዴም የናስ ቀስት አዘዘ።
36የመ​ድ​ኀ​ኒ​ቴ​ንም ጋሻ ሰጠ​ኸኝ፤
መል​ስ​ህም አበ​ዛ​ችኝ፤
37በሜ​ዳም አረ​ማ​መ​ዴን በበ​ታቼ አሰ​ፋህ፤
እግ​ሮቼም አል​ተ​ን​ሸ​ራ​ተ​ቱም።
38ጠላ​ቶ​ቼን አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤
እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ አል​መ​ለ​ስም።
39እቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቆ​ምም አይ​ች​ሉም፤
ከእ​ግ​ሬም በታች ይወ​ድ​ቃሉ።
40በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ በኀ​ይል ታጸ​ና​ኛ​ለህ፤
በላዬ የቆ​ሙ​ት​ንም በበ​ታቼ ታስ​ገ​ዛ​ቸ​ዋ​ለህ።
41የጠ​ላ​ቶ​ቼን ጀርባ ሰጠ​ኸኝ፤
የሚ​ጠ​ሉ​ኝ​ንም አጠ​ፋ​ሃ​ቸው።
42ጮኹ፤ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤
ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምም።
43በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨ​ኋ​ቸው፤
እንደ ጎዳ​ናም ጭቃ ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ ደቀ​ደ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም።
44ከአ​ሕ​ዛብ ጠብ አድ​ነኝ፤
የአ​ሕ​ዛ​ብም ራስ አድ​ር​ገህ ትሾ​መ​ኛ​ለህ፤
የማ​ላ​ው​ቀው ሕዝብ ተገ​ዛ​ልኝ።
45የባ​ዕድ ልጆች ዋሹኝ፤
በጆሮ ሰም​ተው መለ​ሱ​ልኝ።
46የባ​ዕድ ልጆች አረጁ፤
ከማ​ን​ከ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ተሰ​ና​ከሉ።
47እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ነው፤ ጠባ​ቂ​ዬም ቡሩክ ነው፤
የሕ​ይ​ወቴ ጠባቂ አም​ላኬ ከፍ ከፍ ይበል፤
48በቀ​ሌን የሚ​መ​ል​ስ​ልኝ አም​ላክ ጽኑዕ ነው።
አሕ​ዛ​ብን በበ​ታቼ ያስ​ገ​ዛ​ል​ኛል፤
49ከጠ​ላ​ቶቼ የሚ​ያ​ወ​ጣኝ እርሱ ነው፤
በእ​ኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገ​ኛ​ለህ፤
ከግ​ፈ​ኛም ሰው ታድ​ነ​ኛ​ለህ።
50አቤቱ፥ ስለ​ዚህ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥
ለስ​ም​ህም እዘ​ም​ራ​ለሁ።
51የን​ጉ​ሡን መድ​ኀ​ኒት ታላቅ ያደ​ር​ጋል፤
ቸር​ነ​ቱ​ንም ለቀ​ባው ለዳ​ዊ​ትና ለዘሩ፥
ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያደ​ር​ጋል።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ