2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 22
22
የዳዊት የምስጋና መዝሙር
1 #
መዝ. 18፥1። ጌታ ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፥ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለጌታ ዘመረ፤ 2#መዝ. 18፥3-51።እንዲህም አለ፤
ጌታ ዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤
3 #
1ሳሙ. 2፥1-2። አምላኬ የምደገፍበት፥ ዐለቴ፥
ጋሻዬና የመዳኔ ቀንድ ነው።
እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፥
መጠጊያና አዳኜ ነው፤
አንተ ከጨካኞች ታድነኛለህ።
4ምስጋና የሚገባውን ጌታን እጠራለሁ፤
ከጠላቶቼም እድናለሁ።
5የሞት ሞገድ ከበበኝ፤
የጥፋትም ጐርፍ አጥለቀለቀኝ።
6የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤
የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ።
7በጨነቀኝ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፤
ወደ አምላኬም ጮኽሁ።
እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤
ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።
8ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤
የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤
እርሱ ተቆጥቶአልና ራዱ።
9ከአፍንጫው የቁጣ ጢስ ወጣ፤
ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤
ከእርሱ የሚንበለበል ፍም ወጣ።
10 #
መዝ. 144፥5። ሰማያትን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤
ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።
11 #
ዘፀ. 25፥18-22። በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤
በነፋስም ክንፍ ሲከንፍ ታየ።
12ሁለንተናውን በጨለማ ሰወረ፥
በውሃ በተሞላ ጥቅጥቅ ደመና፥ ራሱን ከበበ።
13በፊቱ ካለው ብርሃን የእሳት ፍም ነደደ።
14ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፤ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።
15 #
መዝ. 144፥6። ፍላጻውን ሰደደ፤ በተናቸውም፤
በመብረቁም ብልጭታ አወካቸው።
16 #
ዘፀ. 15፥8። ከጌታ ተግሣጽ፥ ከአፍንጫው ከሚወጣው፥
ከእስትንፋሱ ቁጣ የተነሣ፥
የባሕር መተላለፊያዎች ታዩ፤
የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።
17 #
መዝ. 144፥7። ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤
ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ።
18በርትተውብኝ ነበርና፥
ከብርቱ ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም ታደገኝ።
19በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ ጌታ ግን ደገፈኝ።
20ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤
ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ።
21ጌታ እንደጽድቄ መለሰልኝ፤
እንደ እጄም ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ፤
22የጌታን መንገድ ጠብቄአለሁና፤
ከአምላኬ ክፋት በማድረግ አልተለየሁም።
23ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤
ከሥርዓቱም አልራቅሁም።
24በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤
ራሴንም ከኃጢአት ጠብቄአለሁ።
25ጌታም እንደጽድቄ፥ በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና
ብድራትን ከፈለኝ።
26 #
1ሳሙ. 2፥30። “ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ ሆነህ ትገኛለህ፥
ለቅን ሰው አንተም ቅን ሆነህ ትታያለህ።
27ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ ሆነህ ትታያለህ፥
ለጠማማ ሰው ግን ጠማማ ሆነህ ትታያለህ።
28አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤
ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፥ ትዕቢተኞችን ይመለከታል።
29ጌታ ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤
ጌታም ጨለማዬን ያበራል።
30በአንተ ርዳታ ሠራዊት አልፌ ወደ ፊት እሮጣለሁ፤
በአምላኬም ኃይል ቅጥሩን እዘላለሁ።
31 #
ምሳ. 30፥5። የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤
የጌታም ቃል የጠራ ነው፤
ለሚታመኑበትም ሁሉ ጋሻ ነው፤
32ከጌታ በቀር አምላክ ማን ነው፤
ከአምላካችንስ በቀር ዓለት ማን ነው?
33ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቀና እግዚአብሔር ነው።
34 #
መዝ. 62፥3፤ ዕን. 3፥19። እግሮቼን እንደ ብሆር እግር ያበረታል፤
በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል።
35ክንዶቼም የናስ ቀስት መሳብ እንዲችሉ፥
እጆቼን ለጦርነት ያሰለጥናል።
36የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤
ምላሽህም ታላቅ አድርጎኛል።
37እርምጃዬን አሰፋህ፤
እግሮቼም አልተሰነካከሉም።
38ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤
ሳላጠፋቸው ወደ ኋላ አልተመለስሁም።
39ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ አስጨነቅኻቸው
ተመልሰውም እንዳይቆሙ፥ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።
40ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥
በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛለህ።
41የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥
የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።
42ለርዳታ ጮኹ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም፤
ወደ ጌታ ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም።
43በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አደቀቅዃቸው፤
በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም።
44ከሕዝቤ ጥቃት አዳንከኝ፤
የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ፤
የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤
45ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤
እንደ ሰሙኝም በፍጥነት ይታዘዙኛል።
46ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።
47ጌታ ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤
የመዳኔ ዓለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።
48የሚበቀልልኝ አምላክ፥ ሕዝቦችን ከሥሬ የሚያስገዛልኝ፤
49ከጠላቶቼ እጅ ነጻ የሚያወጣኝ እርሱ ነው።
በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤
ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።
50 #
መዝ. 22፥23፤ ሮሜ 15፥9። ስለዚህ ጌታ ሆይ፥ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤
ለስምህም ምስጋና እዘምራለሁ።
51ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤
ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥
የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳያል፥
ይህንንም ለዘለዓለም ያደርጋል።”
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 22: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ