1 ነገሥት 11:1-10

1 ነገሥት 11:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ሴቶ​ችን ይወድ ነበር፥ ከባ​ዕ​ዳን ሕዝ​ብም የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ና​ው​ያ​ትን፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ት​ንና ሲዶ​ና​ው​ያ​ትን፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፦ ሚስ​ቶ​ችን አገባ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ትከ​ተሉ ዘንድ ልባ​ች​ሁን እን​ዳ​ይ​መ​ልሱ ወደ እነ​ርሱ አት​ግቡ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ አይ​ግቡ” ካላ​ቸው ከአ​ሕ​ዝብ አገባ፤ ሰሎ​ሞን ግን እነ​ር​ሱን ተከ​ተለ፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም። ለእ​ር​ሱም ሰባት መቶ ሚስ​ቶ​ችና ሦስት መቶ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት። ከዚህ በኋላ ሰሎ​ሞን በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አል​ነ​በ​ረም። ከባ​ዕድ ያገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶ​ቹም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ይከ​ተል ዘንድ ልቡን መለ​ሱት። ሰሎ​ሞ​ንም የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንን አም​ላክ አስ​ጠ​ራ​ጢ​ስን የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ን​ንም ርኵ​ሰት ኮሞ​ስን ተከ​ተለ። ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ውም። ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን ለሞ​አብ ርኵ​ሰት ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞን ልጆች ርኵ​ሰት ለሞ​ሎክ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አን​ጻር በአ​ለው ተራራ ላይ መስ​ገ​ጃን ሠራ። ሰሎ​ሞ​ንም ልዩ ከሆኑ ከአ​ሕ​ዝብ ለአ​ገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶቹ ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረገ፤ ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ዕጣ​ንም አጠነ። ሁለት ጊዜም ከተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ውን መል​ሶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ሎ​ሞን ላይ ቍጣን ተቈጣ። ስለ​ዚ​ህም ነገር ወደ ባዕድ አም​ል​ኮት እን​ዳ​ይ​ሄድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ይጠ​ብ​ቅና ያደ​ርግ ዘንድ አዘ​ዘው፤ ልቡ​ናው ግን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ሆ​ነም።

1 ነገሥት 11:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ንጉሥ ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን ማለትም ሞዓባውያትን፣ አሞናውያትን፣ ኤዶማውያትን፣ ሲዶናውያትን፣ ኬጢያውያትን አፈቀረ። እነዚህም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን፣ “ልባችሁን ወደ አማልክታቸው በርግጥ ይመልሱታልና ከእነርሱ ጋራ መጋባት የለባችሁም” ካላቸው አሕዛብ ወገን ነበሩ፤ ሆኖም ሰሎሞን ከእነዚሁ ጋራ ፍቅሩ ጠና። እርሱም ከነገሥታት የተወለዱ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡ ወደ ሌላ እንዲያዘነብል አደረጉት። ሰሎሞን በሸመገለ ጊዜ ሚስቶቹ ልቡን ወደ ሌሎች አማልክት መለሱት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ እንደ ተገዛ ሁሉ፣ በፍጹም ልቡ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር አልተገዛም። ሰሎሞንም የሲዶናውያንን ሴት አምላክ አስታሮትን፣ አስጸያፊውን የአሞናውያንን አምላክ ሚልኮምን ተከተለ። ስለዚህ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ፤ እንደ አባቱ እንደ ዳዊትም እግዚአብሔርን እስከ መጨረሻው አልተከተለም። ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ባለው ተራራ ላይ ለአስጸያፊው የሞዓብ አምላክ ለካሞሽ እንዲሁም አስጸያፊ ለሆነው ለአሞናውያን አምላክ ለሞሎክ ማምለኪያ ኰረብታ ሠራ። ለአማልክታቸው ዕጣን ለሚያጥኑና መሥዋዕት ለሚያቀርቡ ለሌሎቹ ሚስቶቹም ሁሉ በዚሁ ዐይነት ሠራላቸው። ሰሎሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡ ስለ ሸፈተ፣ እግዚአብሔር ተቈጣው። ምንም እንኳ ሌሎች አማልክትን እንዳይከተል ሰሎሞንን ቢከለክለውም፣ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልጠበቀም፤

1 ነገሥት 11:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ንጉሡም ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ፥ በሞዓባውያንና በአሞናውያን በኤዶማውያንም በሲዶናውያንና በሒታውያን ሴቶች፥ በብዙ እንግዶች ሴቶች ፍቅር ተነደፈ። እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች “አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፤ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ፤” ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ። ለእርሱም ወይዛዝርት የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት። ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም። ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን ተከተለ። ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም። በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ። ለአማልክቶቻቸው ዕጣን ለሚያጥኑ መሥዋዕትም ለሚሠው ለእንግዶች ሚስቶቹ ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ሁለት ጊዜም ከተገለጠለት፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳይከተል ካዘዘው ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡን አርቆአልና፥ እግዚአብሔርም ያዘዘውን ነገር አልጠበቀምና እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቈጣ።

1 ነገሥት 11:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ በዚህም መሠረት ከግብጽ ንጉሥ ልጅ ሌላ የሒታውያን፥ የሞአባውያን፥ የዐሞናውያን፥ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን፥ “አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደ ሆነ በእርግጥ ወደ አማልእክታቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ” ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፤ እነዚህን ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች እግዚአብሔር እንዳይጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፤ ሰሎሞን ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተሰባበረ። ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቊባቶች ነበሩት፤ እነርሱም ሰሎሞንን ከእግዚአብሔር እንዲርቅ አደረጉት፤ በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም። የሲዶናውያን ሴት አምላክ ለነበረችው ለዐስታሮትና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአጸያፊው ለዐሞናውያን አምላክ ሰገደ። በደል በመሥራትም እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በቅንነት በመከተል ረገድ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም። ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው። እንዲሁም የባዕዳን አገሮች ሚስቶቹ ለየአማልክታቸው ዕጣን የሚያጥኑባቸውንና መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸውን ስፍራዎች ሠራ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ ተገልጦለት ባዕዳን አማልክትን እንዳያመልክ ያዘዘው ቢሆንም እንኳ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፤ ይልቁንም ከእግዚአብሔር እየራቀ ሄደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ተቈጣ፤

1 ነገሥት 11:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ በዚህም መሠረት ከግብጽ ንጉሥ ልጅ ሌላ የሒታውያን፥ የሞዓባውያን፥ የዐሞናውያን፥ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ። ጌታ ለእስራኤላውያን፥ “አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደሆነ በእርግጥ ወደ አማልእክታቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ” ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፤ እነዚህን ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች ጌታ እንዳይጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፤ ሰሎሞን ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተሰባበረ። ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቁባቶች ነበሩት፤ እነርሱም ሰሎሞንን ከጌታ እንዲርቅ አደረጉት። በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም። የሲዶናውያን ሴት አምላክ ለነበረችው ለዐስታሮትና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአጸያፊው ለዐሞናውያን አምላክ ሰገደ። በደል በመሥራትም ጌታን አሳዘነ፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በቅንነት በመከተል ረገድ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም። ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ኬሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው። እንዲሁም የባዕዳን አገሮች ሚስቶቹ ለየአማልክታቸው ዕጣን የሚያጥኑባቸውንና መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸውን ስፍራዎች ሠራ። ሰሎሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ጌታ ልቡ ስለሸፈተ፥ እግዚአብሔር ተቈጣው። ምንም እንኳ ሌሎች አማልክትን እንዳይከተል ሰሎሞንን ቢከለክለውም፥ ሰሎሞን የጌታን ትእዛዝ አልጠበቀም፤