የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 11

11
ሰሎ​ሞን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ራቀ
1ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ሴቶ​ችን ይወድ ነበር፥ ከባ​ዕ​ዳን ሕዝ​ብም የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ና​ው​ያ​ትን፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ት​ንና ሲዶ​ና​ው​ያ​ትን፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፦ ሚስ​ቶ​ችን አገባ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ትከ​ተሉ ዘንድ ልባ​ች​ሁን እን​ዳ​ይ​መ​ልሱ ወደ እነ​ርሱ አት​ግቡ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ አይ​ግቡ” ካላ​ቸው ከአ​ሕ​ዝብ አገባ፤ ሰሎ​ሞን ግን እነ​ር​ሱን ተከ​ተለ፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም። 3ለእ​ር​ሱም ሰባት መቶ ሚስ​ቶ​ችና ሦስት መቶ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት። 4ከዚህ በኋላ ሰሎ​ሞን በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አል​ነ​በ​ረም። ከባ​ዕድ ያገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶ​ቹም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ይከ​ተል ዘንድ ልቡን መለ​ሱት። 5ሰሎ​ሞ​ንም የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንን አም​ላክ አስ​ጠ​ራ​ጢ​ስን የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ን​ንም ርኵ​ሰት ኮሞ​ስን ተከ​ተለ። 6ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ውም። 7ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን ለሞ​አብ ርኵ​ሰት ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞን ልጆች ርኵ​ሰት ለሞ​ሎክ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አን​ጻር በአ​ለው ተራራ ላይ መስ​ገ​ጃን ሠራ። 8ሰሎ​ሞ​ንም ልዩ ከሆኑ ከአ​ሕ​ዝብ ለአ​ገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶቹ ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረገ፤ ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ዕጣ​ንም አጠነ።
9ሁለት ጊዜም ከተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ውን መል​ሶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ሎ​ሞን ላይ ቍጣን ተቈጣ። 10ስለ​ዚ​ህም ነገር ወደ ባዕድ አም​ል​ኮት እን​ዳ​ይ​ሄድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ይጠ​ብ​ቅና ያደ​ርግ ዘንድ አዘ​ዘው፤ ልቡ​ናው ግን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ሆ​ነም። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን አለው፥ “ይህን ሠር​ተ​ሃ​ልና፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሕጌን አል​ጠ​ብ​ቅ​ህ​ምና መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከአ​ንተ ከፍዬ ለባ​ሪ​ያህ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ። 12ነገር ግን ከል​ጅህ እጅ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ እንጂ ስለ አባ​ትህ ስለ ዳዊት ይህን በዘ​መ​ንህ አላ​ደ​ር​ግም። 13ነገር ግን ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትና ስለ መረ​ጥ​ኋት ሀገሬ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለል​ጅህ አንድ ነገድ እሰ​ጣ​ለሁ እንጂ መን​ግ​ሥ​ቱን ሁሉ አል​ከ​ፍ​ልም።”
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርን ከረ​ም​ማ​ቴር ወገን የኤ​ል​ያ​ዳሔ ልጅ ኤስ​ሮ​ምን የሲባ ንጉሥ ጌታ​ውን አድ​ረ​ዓ​ዛ​ርን ጠላት አድ​ርጎ በሰ​ሎ​ሞን ላይ አስ​ነሣ። ሰዎ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ። የዓ​መ​ፁም አበ​ጋዝ እርሱ ነበር። ደማ​ስ​ቆ​ንም እጅ አደ​ረ​ጋት። በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርም ከኤ​ዶ​ም​ያስ ነገ​ሥ​ታት ዘር ነበር።
በሰ​ሎ​ሞን ላይ ጠላት እንደ ተነ​ሣ​በት
15ዳዊ​ትም ኤዶ​ም​ያ​ስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ ተወ​ግ​ተው የሞ​ቱ​ትን ሊቀ​ብር በወጣ ጊዜ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም ወንድ ሁሉ በገ​ደለ ጊዜ፥ 16ኢዮ​አ​ብና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ወንድ ሁሉ እስ​ኪ​ገ​ድሉ ድረስ ስድ​ስት ወር በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር። 17አዴር፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ከኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች የሆኑ የአ​ባቱ አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ኰበ​ለሉ፤ ወደ ግብ​ፅም ገቡ። አዴር ግን ገና ሕፃን ነበር። 18ከም​ድ​ያ​ምም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ከፋ​ራን ሰዎ​ችን ወሰዱ፤ ወደ ግብ​ፅም መጡ፤ ወደ ግብ​ፅም ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን ሄዱ፤ አዴ​ርም ወደ ፈር​ዖን ገባ። እር​ሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረ​ገው። 19አዴ​ርም በፈ​ር​ዖን ፊት እጅግ ባለ​ም​ዋል ሆነ። የሚ​ስ​ቱ​ንም የቴ​ቄ​ም​ና​ስን ታላቅ እኅት ሚስት አጋ​ባው። 20የቴ​ቄ​ም​ናስ እኅት ወንድ ልጅ ጌን​ባ​ትን ለአ​ዴር ወለ​ደ​ች​ለት፤ ቴቄ​ም​ና​ስም በፈ​ር​ዖን ልጆች መካ​ከል አሳ​ደ​ገ​ችው፤ ጌን​ባ​ትም በፈ​ር​ዖን ልጆች መካ​ከል ነበረ። 21አዴ​ርም በግ​ብፅ ሳለ ዳዊት እንደ አባ​ቶቹ እን​ዳ​ን​ቀ​ላፋ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ አዴር ፈር​ዖ​ንን፥ “ወደ ሀገሬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ” አለው። 22ፈር​ዖ​ንም፥ “እነሆ፥ ከእኔ ዘንድ ወደ ሀገ​ርህ መሄድ የፈ​ለ​ግህ ምን አጥ​ተህ ነው?” አለው። አዴ​ርም፥ “አን​ዳች አላ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ልሂድ” ብሎ መለሰ። አዴ​ርም ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ።
23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከጌ​ታው ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር የኰ​በ​ለ​ለ​ውን የኤ​ል​ያ​ዳን ልጅ ሬዞ​ንን ጠላት አድ​ርጎ አስ​ነ​ሣ​በት። 24ዳዊ​ትም የሲ​ባን ሰዎች በገ​ደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎ​ችን ሰብ​ስቦ የጭ​ፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማ​ስ​ቆም ሄዱ፥ በዚ​ያም ተቀ​መጡ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ላይ አነ​ገ​ሡት። 25በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ጠላት ነበረ። አዴ​ርም ያደ​ረ​ጋት ክፋት ይህች ናት፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አስ​ጨ​ነቀ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ነገሠ።
ኢዮ​ር​ብ​ዓም እን​ደ​ሚ​ነ​ግሥ ትን​ቢት እንደ ተነ​ገ​ረ​ለት
26ከሳ​ሪራ ሀገር የሆነ የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ዊው የና​ባ​ጥና ሳሩሃ የተ​ባ​ለች የመ​በ​ለት ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋይ ነበረ። 27እር​ሱም ያደ​ረ​ገው ይህ ነው በን​ጉሡ በሰ​ሎ​ሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዳ​ርቻ ያለ ቅጥ​ር​ንና የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ። 28ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ፤ ሰሎ​ሞ​ንም ጐል​ማ​ሳው ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሥራ የጸና መሆ​ኑን ባየ ጊዜ በዮ​ሴፍ ነገድ ሥራ ሁሉ ላይ ሾመው። 29ከዚህ በኋ​ላም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ሴሎ​ና​ዊው ነቢዩ አኪያ በመ​ን​ገድ ላይ ተገ​ና​ኘው፤ ከመ​ን​ገ​ድም ገለል አደ​ረ​ገው፤ አኪ​ያም አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር። ሁለ​ቱም በሜዳ ነበሩ። 30አኪ​ያም የለ​በ​ሰ​ውን አዲስ ልብስ ይዞ ከዐ​ሥራ ሁለት ቀደ​ደው። 31ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አለው፥ “ዐሥር ቅዳጅ ውሰድ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን እጅ መን​ግ​ሥ​ቱን እለ​ያ​ታ​ለሁ፤ ዐሥ​ሩ​ንም ነገ​ዶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። 32ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገ​ሮች ሁሉ ስለ መረ​ጥ​ኋት ከተማ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ግን ሁለት ነገድ ይቀ​ሩ​ለ​ታል፤ 33ትቶ​ኛ​ልና፥ ለሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርኵ​ሰት ለአ​ስ​ጠ​ራ​ጢስ፥ ለሞ​አ​ብም አም​ላክ ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች አም​ላክ ለሞ​ሎክ ሰግ​ዶ​አ​ልና፥ አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ በፊቴ ቅን ነገ​ርን ያደ​ርግ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዶቼ አል​ሄ​ደ​ምና። 34መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ሁሉ ከእጁ አል​ወ​ስ​ድም፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ስለ ጠበ​ቀው ስለ መረ​ጥ​ሁት ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊት ግን በዕ​ድ​ሜው ሁሉ አለቃ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። 35መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ከልጁ እጅ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተም ዐሥ​ሩን ነገድ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። 36ስሜ​ንም ባኖ​ር​ሁ​ባት በዚ​ያች በመ​ረ​ጥ​ኋት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለባ​ሪ​ያዬ ለዳ​ዊት በፊቴ ሁል​ጊዜ መብ​ራት ይሆ​ን​ለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገ​ድን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ። 37አን​ተ​ንም እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ፤ ነፍ​ስ​ህም በወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ላይ አነ​ግ​ሥ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ። 38ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ብት​ሰማ፥ በመ​ን​ገ​ዴም ብት​ሄድ፥ በፊ​ቴም የቀ​ና​ውን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ብት​ጠ​ብቅ፥ ከአ​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ፤ ለዳ​ዊ​ትም እንደ ሠራ​ሁ​ለት የታ​መነ ቤትን እሠ​ራ​ል​ሃ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። 39ስለ​ዚ​ህም የዳ​ዊ​ትን ዘር አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን በዘ​መን ሁሉ አይ​ደ​ለም።” 40ሰሎ​ሞ​ንም ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ሊገ​ድ​ለው ወደደ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ተነ​ሥቶ ወደ ግብፅ ሀገር፥ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሱስ​ቀም ኰብ​ልሎ ሄደ፥ ሰሎ​ሞ​ንም እስ​ኪ​ሞት ድረስ በግ​ብፅ ተቀ​መጠ።
የሰ​ሎ​ሞን ሞትና የሮ​ብ​ዐም መን​ገሥ
(2ዜ.መ. 9፥29-31)
41የቀ​ረ​ውም የሰ​ሎ​ሞን ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ ጥበ​ቡም ሁሉ፥ እነሆ፥ በሰ​ሎ​ሞን የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። 42ሰሎ​ሞ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን አርባ ዓመት ነበረ። 43ሰሎ​ሞ​ንም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ