የዮሐንስ ወንጌል 3:34-36

የዮሐንስ ወንጌል 3:34-36 አማ05

እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጠው መጥኖ ስላልሆነ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል። አብ ልጁን ይወዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ አስረክቦታል። በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በእርሱ ላይ ይኖርበታል እንጂ ሕይወትን አያገኝም።