ዮሐንስ 3:34-36
ዮሐንስ 3:34-36 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና። አብ ልጁን ይወዳልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው። በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር የቍጣ መቅሠፍት በላዩ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
ያጋሩ
ዮሐንስ 3 ያንብቡዮሐንስ 3:34-36 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር መንፈሱን ሳይሰፍር ስለሚሰጥ፣ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል። አብ ወልድን ይወድዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል። በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
ያጋሩ
ዮሐንስ 3 ያንብቡዮሐንስ 3:34-36 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና። አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
ያጋሩ
ዮሐንስ 3 ያንብቡ