ዮሐንስ 3:34-36

ዮሐንስ 3:34-36 NASV

እግዚአብሔር መንፈሱን ሳይሰፍር ስለሚሰጥ፣ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል። አብ ወልድን ይወድዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል። በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።”