YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 70

70
አስ​ቀ​ድ​መው ስለ ተማ​ረኩ ስለ አሚ​ና​ዳብ ልጆች የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አላ​ፍ​ርም።
2በጽ​ድ​ቅህ አስ​ጥ​ለኝ፥ ታደ​ገ​ኝም፤
ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፥ ፈጥ​ነ​ህም አድ​ነኝ።
3በጠ​ን​ካራ ቦታ ታድ​ነኝ ዘንድ
አም​ላ​ኬና መድ​ኀ​ኒቴ ሁነኝ፤
ኀይ​ሌና መጠ​ጊ​ያዬ አንተ ነህና።
4አም​ላኬ ከኃ​ጥ​ኣን እጅ፥
ከዐ​መ​ፀ​ኛና ከግ​ፈ​ኛም እጅ አድ​ነኝ።
5አቤቱ፥ አንተ ተስ​ፋዬ ነህና፥
ጌታዬ ሆይ፥ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሬ ተስፋ አደ​ረ​ግ​ሁህ።
6በእ​ናቴ ማኅ​ፀን በአ​ንተ ጸናሁ፥
በማ​ኅ​ፀን ውስ​ጥም አንተ ሸሸ​ግ​ኸኝ፤
ሁል​ጊ​ዜም ስም አጠ​ራሬ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝማ​ሬዬ ለአ​ንተ ነው” ይላል። አንተ ነህ።
7ለብ​ዙ​ዎች እንደ ጥንግ ሆንሁ፤
አንተ ግን ረዳ​ቴና ኀይሌ ነህ።
8አፌን በም​ስ​ጋና ምላ
ሁል​ጊዜ ምስ​ጋ​ና​ህ​ንና የክ​ብ​ር​ህን ገና​ና​ነት አመ​ሰ​ግን ዘንድ።
9በእ​ር​ጅ​ናዬ ዘመን አት​ጣ​ለኝ፥
ጉል​በ​ቴም ባለቀ ጊዜ አም​ላኬ አት​ተ​ወኝ።
10ጠላ​ቶቼ በእኔ ላይ ተና​ግ​ረ​ዋ​ልና፥
ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በአ​ን​ድ​ነት ተማ​ክ​ረ​ዋ​ልና፥ እን​ዲ​ህም አሉ፦
11“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ታል፤
የሚ​ያ​ድ​ነው የለ​ምና ተከ​ት​ላ​ችሁ ያዙት።”
12አም​ላኬ ሆይ፥ ከእኔ አት​ራቅ፤
አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።
13ነፍ​ሴን የሚ​ያ​ጣ​ሏት ይፈሩ፥ ይዋ​ረ​ዱም፥
ጉዳ​ቴ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ዕፍ​ረ​ት​ንና ኃሣ​ርን ይል​በሱ።
14እኔ ግን አቤቱ ሁል​ጊዜ ተስፋ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፥
በም​ስ​ጋ​ና​ህም ሁሉ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ።
15አፌ ጽድ​ቅ​ህን፥ ሁል​ጊ​ዜም ማዳ​ን​ህን ይና​ገ​ራል።
ሥራን አላ​ው​ቅ​ምና
16በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል እገ​ባ​ለሁ፤
አቤቱ፥ ጽድ​ቅ​ህን ብቻ አስ​ባ​ለሁ።
17አም​ላኬ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀም​ረህ አስ​ተ​ማ​ር​ኸኝ፤
እስከ ዛሬም ክብ​ር​ህን#ዕብ. “ታላቅ ተአ​ም​ራ​ት​ህን” ይላል። እና​ገ​ራ​ለሁ።
18አም​ላኬ ሆይ እስ​ክ​ሸ​መ​ግ​ልም ድረስ፥
ለሚ​መጣ ትው​ል​ድም ሁሉ ክን​ድ​ህን
ኀይ​ል​ህ​ንም ጽድ​ቅ​ህ​ንም እስ​ክ​ነ​ግር ድረስ፥ አት​ተ​ወኝ።
19አቤቱ፥ እስከ አር​ያም ታላ​ላቅ ነገ​ሮ​ችን አደ​ረ​ግህ፤
አም​ላክ ሆይ፥ እን​ዳ​ንተ ያለ ማን ነው?
20ብዙ ጭን​ቀ​ት​ንና መከ​ራን አሳ​ይ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥
ተመ​ል​ሰ​ህም ሕያው አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤
ከም​ድር ጥል​ቅም እን​ደ​ገና አወ​ጣ​ኸኝ።
21ጽድ​ቅ​ህ​ንም አበ​ዛ​ኸው።
ደስ ታሰ​ኘ​ኝም ዘንድ ተመ​ለ​ስህ።
ከም​ድር ጥል​ቅም እንደ ገና አወ​ጣ​ኸኝ።
22እኔም በመ​ዝ​ሙር መሣ​ሪያ ስለ እው​ነ​ትህ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤
የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላክ ሆይ፥ በመ​ሰ​ንቆ እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።
23ዝማ​ሬን ባቀ​ረ​ብ​ሁ​ልህ ጊዜ ከን​ፈ​ሮ​ቼን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥
ነፍ​ሴ​ንም አንተ አዳ​ን​ሃት።
24ክፉን ለእኔ የሚሹ ባፈ​ሩና በተ​ነ​ወሩ ጊዜ፥
አን​ደ​በቴ ደግሞ ሁል​ጊዜ ጽድ​ቅ​ህን ይና​ገ​ራል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 70