መዝሙረ ዳዊት 70
70
አስቀድመው ስለ ተማረኩ ስለ አሚናዳብ ልጆች የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አላፍርም።
2በጽድቅህ አስጥለኝ፥ ታደገኝም፤
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ፈጥነህም አድነኝ።
3በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ
አምላኬና መድኀኒቴ ሁነኝ፤
ኀይሌና መጠጊያዬ አንተ ነህና።
4አምላኬ ከኃጥኣን እጅ፥
ከዐመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
5አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥
ጌታዬ ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምሬ ተስፋ አደረግሁህ።
6በእናቴ ማኅፀን በአንተ ጸናሁ፥
በማኅፀን ውስጥም አንተ ሸሸግኸኝ፤
ሁልጊዜም ስም አጠራሬ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝማሬዬ ለአንተ ነው” ይላል። አንተ ነህ።
7ለብዙዎች እንደ ጥንግ ሆንሁ፤
አንተ ግን ረዳቴና ኀይሌ ነህ።
8አፌን በምስጋና ምላ
ሁልጊዜ ምስጋናህንና የክብርህን ገናናነት አመሰግን ዘንድ።
9በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥
ጉልበቴም ባለቀ ጊዜ አምላኬ አትተወኝ።
10ጠላቶቼ በእኔ ላይ ተናግረዋልና፥
ነፍሴንም የሚሹአት በአንድነት ተማክረዋልና፥ እንዲህም አሉ፦
11“እግዚአብሔር ትቶታል፤
የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።”
12አምላኬ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፤
አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ተመልከት።
13ነፍሴን የሚያጣሏት ይፈሩ፥ ይዋረዱም፥
ጉዳቴንም የሚፈልጉ ዕፍረትንና ኃሣርን ይልበሱ።
14እኔ ግን አቤቱ ሁልጊዜ ተስፋ አደርግሃለሁ፥
በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ።
15አፌ ጽድቅህን፥ ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል።
ሥራን አላውቅምና
16በእግዚአብሔር ኀይል እገባለሁ፤
አቤቱ፥ ጽድቅህን ብቻ አስባለሁ።
17አምላኬ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤
እስከ ዛሬም ክብርህን#ዕብ. “ታላቅ ተአምራትህን” ይላል። እናገራለሁ።
18አምላኬ ሆይ እስክሸመግልም ድረስ፥
ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን
ኀይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥ አትተወኝ።
19አቤቱ፥ እስከ አርያም ታላላቅ ነገሮችን አደረግህ፤
አምላክ ሆይ፥ እንዳንተ ያለ ማን ነው?
20ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና፥
ተመልሰህም ሕያው አደረግኸኝ፤
ከምድር ጥልቅም እንደገና አወጣኸኝ።
21ጽድቅህንም አበዛኸው።
ደስ ታሰኘኝም ዘንድ ተመለስህ።
ከምድር ጥልቅም እንደ ገና አወጣኸኝ።
22እኔም በመዝሙር መሣሪያ ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ፤
የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።
23ዝማሬን ባቀረብሁልህ ጊዜ ከንፈሮቼን ደስ ይላቸዋል፥
ነፍሴንም አንተ አዳንሃት።
24ክፉን ለእኔ የሚሹ ባፈሩና በተነወሩ ጊዜ፥
አንደበቴ ደግሞ ሁልጊዜ ጽድቅህን ይናገራል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 70: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in