መዝሙረ ዳዊት 69
69
ለመዘምራን አለቃለመታሰቢያ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ተመልከት፤
አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
2ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ፥ ይጐስቍሉም፥
ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደኋላቸው ይመለሱ፥ ይፈሩም።
3እሰይ! እሰይ! የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
4አቤቱ፥ የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ፥ ደስም ይበላቸው፤
ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ፥ “ዘወትር እግዚአብሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።
5እኔ ድሃና ምስኪን ነኝ፤ እግዚአብሔርም ይረዳኛል፤
ረዳቴ መጠጊያዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አምላኬ አትዘግይ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 69: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in