YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 69

69
ለመ​ዘ​ም​ራን አለ​ቃ​ለ​መ​ታ​ሰ​ቢያ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ እኔን ለማ​ዳን ተመ​ል​ከት፤
አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ፍጠን።
2ነፍ​ሴን የሚ​ሹ​አት ይፈሩ፥ ይጐ​ስ​ቍ​ሉም፥
ክፉ​ንም የሚ​መ​ክ​ሩ​ብኝ ወደ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ ይፈ​ሩም።
3እሰይ! እሰይ! የሚ​ሉኝ አፍ​ረው ወዲ​ያው ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ።
4አቤቱ፥ የሚ​ሹህ ሁሉ በአ​ንተ ሐሤት ያድ​ርጉ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤
ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወ​ድዱ፥ “ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።
5እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይረ​ዳ​ኛል፤
ረዳቴ መጠ​ጊ​ያ​ዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አም​ላኬ አት​ዘ​ግይ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in