መዝሙረ ዳዊት 139
139
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1“አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥
ከዐመፀኛ ሰውም ታደገኝ፥
2ሁልጊዜ በልባቸው ዐመፃን የሚመክሩ፥
ይገድሉኝ ዘንድ ይከብቡኛል።
3ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፤
ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ።
4አቤቱ፥ ከኃጥኣን እጅ ጠብቀኝ፥
እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ
ከዐመፀኞች ሰዎች አድነኝ።
5ትዕቢተኞች ወጥመድን ሰወሩብኝ፥
ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ፤
በመንገዴም ዕንቅፋትን አኖሩ።
6እግዚአብሔርንም፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤
የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ” አልሁት።
7አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የድኅነቴ ኀይል፥
በጦርነት ቀን በራሴ ላይ ሁነህ ሰወርኸኝ።
8አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለኀጢአተኞች አትስጠኝ፤
በላዬ ተማከሩ፥ እንዳይታበዩም አትተወኝ።
9የአሽክላቸው ራስ የከንፈራቸውም ክፋት ይድፈናቸው።
10የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፤
መቆም እንዳይችሉ በችግር ወደ ምድር ይውደቁ።
11ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፤
ዐመፀኛ ሰውን ክፋት ለጥፋት ታድነዋለች።
12እግዚአብሔር ለድሆች ዳኝነትን
ለችግረኞችም ፍርድን እንዲያደርግ ዐወቅሁ።
13ጻድቃን ግን በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ፤
ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 139: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in