YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 139

139
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1“አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድ​ነኝ፥
ከዐ​መ​ፀኛ ሰውም ታደ​ገኝ፥
2ሁል​ጊዜ በል​ባ​ቸው ዐመ​ፃን የሚ​መ​ክሩ፥
ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ ይከ​ብ​ቡ​ኛል።
3ምላ​ሳ​ቸ​ውን እንደ እባብ ሳሉ፤
ከከ​ን​ፈ​ራ​ቸው በታች የእ​ባብ መርዝ አለ።
4አቤቱ፥ ከኃ​ጥ​ኣን እጅ ጠብ​ቀኝ፥
እር​ም​ጃ​ዬ​ንም ሊያ​ሰ​ና​ክሉ ከመ​ከሩ
ከዐ​መ​ፀ​ኞች ሰዎች አድ​ነኝ።
5ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ፥
ለእ​ግ​ሮ​ቼም የወ​ጥ​መድ ገመ​ድን ዘረጉ፤
በመ​ን​ገ​ዴም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖሩ።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤
የል​መ​ና​ዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድ​ምጥ” አል​ሁት።
7አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የድ​ኅ​ነቴ ኀይል፥
በጦ​ር​ነት ቀን በራሴ ላይ ሁነህ ሰወ​ር​ኸኝ።
8አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ከም​ኞቴ የተ​ነሣ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች አት​ስ​ጠኝ፤
በላዬ ተማ​ከሩ፥ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ዩም አት​ተ​ወኝ።
9የአ​ሽ​ክ​ላ​ቸው ራስ የከ​ን​ፈ​ራ​ቸ​ውም ክፋት ይድ​ፈ​ና​ቸው።
10የእ​ሳት ፍም በላ​ያ​ቸው ይው​ደቅ፤
መቆም እን​ዳ​ይ​ችሉ በች​ግር ወደ ምድር ይው​ደቁ።
11ተና​ጋሪ ሰው በም​ድር ውስጥ አይ​ጸ​ናም፤
ዐመ​ፀኛ ሰውን ክፋት ለጥ​ፋት ታድ​ነ​ዋ​ለች።
12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለድ​ሆች ዳኝ​ነ​ትን
ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ፍር​ድን እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ ዐወ​ቅሁ።
13ጻድ​ቃን ግን በእ​ው​ነት ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፤
ቅኖ​ችም በፊ​ትህ ይኖ​ራሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in