መዝሙረ ዳዊት 140
140
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ስማኝ፤
ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ቃል አድምጥ።
2ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥
እጆቼ የሠርክ መሥዋዕትን አነሡ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእጄንም ማንሣት እንደ ሠርክ መሥዋዕት” ይላል።
3አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ፥
ለከንፈሮቼም ጽኑዕ መዝጊያን አኑር።
4ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥
ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር
ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤
ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
5በጽድቅ ገሥጸኝ፥ በምሕረትም ዝለፈኝ፥
የኀጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤
ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።#ዕብ. “ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነው” ይላል።
6ኀያላኖቻቸው በዓለት አጠገብ ተጣሉ፥
ተችሎኛልና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቃሌ ጣፋጭ ናትና” ይላል። ቃሌን ስሙኝ።
7እንደ ጓል በምድር ላይ ተሰነጣጠቁ
እንዲሁ አጥንቶቻቸው በሲኦል ተበተኑ፥
8አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፤
በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አታውጣት።
9ከሰወሩብኝ ወጥመድ፥
ዐመፃንም ከሚያደርጉ ሰዎች እንቅፋት ጠብቀኝ።
10እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ
ኃጥኣን በወጥመዳቸው ይውደቁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 140: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in