YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 141

141
በዋሻ በነ​በረ ጊዜ የዳ​ዊት ትም​ህ​ርት።
1በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤
በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ንሁ።
2ልመ​ና​ዬን በፊቱ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤
መከ​ራ​ዬ​ንም በፊቱ እና​ገ​ራ​ለሁ።
3ሰው​ነቴ በላዬ ላይ ባለ​ቀች ጊዜ
አቤቱ፥ መን​ገ​ዴን አንተ ታው​ቃ​ለህ፤
በም​ሄ​ድ​ባት በዚ​ያች መን​ገድ ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ።
4ወደ ቀኝም ተመ​ልሼ አየሁ፥
የሚ​ያ​ው​ቀ​ኝም አጣሁ፤
መሸ​ሸ​ጊ​ያም የለ​ኝም፥
ስለ ሰው​ነ​ቴም የሚ​መ​ራ​መር የለም።
5አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦
“አንተ ተስ​ፋዬ ነህ፥
በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር አንተ ዕድል ፋን​ታዬ ነህ” አልሁ።
6እጅግ ተዋ​ር​ጃ​ለ​ሁና ወደ ልመ​ናዬ ተመ​ል​ከት፤
በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና ከከ​በ​ቡኝ አድ​ነኝ።
7አቤቱ፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግን ዘንድ
ሰው​ነ​ቴን ከእ​ሥ​ራት አው​ጣት፤
ዋጋ​ዬን እስ​ክ​ት​ሰ​ጠኝ ድረስ
ጻድ​ቃን እኔን ይጠ​ብ​ቃሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in