YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 138

138
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ ፈተ​ን​ኸኝ፥ ዐወ​ቅ​ኸ​ኝም።
2አንተ መቀ​መ​ጤ​ንና መነ​ሣ​ቴን ታው​ቃ​ለህ።
የል​ቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስ​ተ​ው​ላ​ለህ።
3ፍለ​ጋ​ዬ​ንና መን​ገ​ዴን አንተ ትመ​ረ​ም​ራ​ለህ፤
መን​ገ​ዶ​ቼን ሁሉ አስ​ቀ​ድ​መህ ዐወ​ቅህ፥
4የዐ​መፃ ቃል በአ​ን​ደ​በቴ እን​ደ​ሌለ።
5አቤቱ፥ አንተ እነሆ፥ የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የኋ​ላ​ውን ሁሉ ዐወ​ቅህ፤
አንተ ፈጠ​ር​ኸኝ፥ እጅ​ህ​ንም በላዬ አደ​ረ​ግህ።
6ዕው​ቀ​ትህ በእኔ ላይ ተደ​ነ​ቀች፤
በረ​ታ​ች​ብኝ፥ ወደ እር​ሷም ለመ​ድ​ረስ አል​ች​ልም።
7ከመ​ን​ፈ​ስህ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ?
ከፊ​ት​ህስ ወዴት እሸ​ሻ​ለሁ?
8ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤
ወደ ጥል​ቁም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሲኦል” ይላል። ብወ​ርድ፥ አንተ በዚያ አለህ፤
9እንደ ንስ​ርም ክን​ፍን ብወ​ስድ፥
እስከ ባሕር መጨ​ረ​ሻም ብበ​ርር፥
10በዚያ እጅህ ትመ​ራ​ኛ​ለች፥
ቀኝ​ህም ታኖ​ረ​ኛ​ለች።
11በእ​ው​ነት ጨለማ ይሸ​ፍ​ነ​ኛል ብል፥
ሌሊት በደ​ስ​ታዬ ብር​ሃን ይሆ​ናል፤
12ጨለማ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ጨ​ል​ም​ምና፥
ሌሊ​ትም እንደ ቀን ታበ​ራ​ለ​ችና፤
እንደ ጨለ​ማዋ እን​ዲሁ ብር​ሃ​ንዋ ነው።
13አቤቱ፥ አንተ ኵላ​ሊ​ቴን ፈጥ​ረ​ሃ​ልና፥
ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀምሮ ተቀ​በ​ል​ኸኝ።#ግእዝ “ወተ​ወ​ከ​ፍ​ከኒ ከመ አእ​ምር” ይላል።
14በመ​ፈ​ራት የተ​ደ​ነ​ቅህ ነህና#ዕብ. “ግሩ​ምና ድንቅ ሆኜ ተፈ​ጥ​ሬ​አ​ለ​ሁና” ይላል። አቤቱ፥ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤
ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍ​ሴም እጅግ ትረ​ዳ​ዋ​ለች።
15በስ​ውር የሠ​ራ​ኸው አጥ​ንቴ ከአ​ንተ አል​ተ​ሰ​ወ​ረም፥
አካ​ሌም ከም​ድር በታች፥
16ያል​ተ​ሠራ አካ​ሌ​ንም#ግእዝ “ወዘሂ ገበ​ርኩ ርእያ አዕ​ይ​ን​ቲከ” ይላል። ዐይ​ኖ​ችህ አዩ፤
ሁሉም በመ​ጽ​ሐ​ፍህ ተጻፉ፥
በቀን ይፈ​ጠ​ራሉ፥
ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ አንድ ስንኳ አይ​ኖ​ርም።
17አቤቱ፥ ወዳ​ጆ​ችህ#ዕብ. “ዐሳ​ቦ​ችህ” ይላል። በእኔ ዘንድ እጅግ የከ​በሩ ናቸው፤
ከቀ​ደ​ም​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅግ ጸኑ።
18እቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ከአ​ሸ​ዋም ይልቅ ይበ​ዛሉ፤
ተነ​ሣሁ፥ ገናም ከአ​ንተ ጋር ነኝ።
19አቤቱ፥ አንተ ኃጥ​ኣ​ንን የም​ት​ገ​ድል ከሆ​ን​ህስ፥
የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
20በዐ​ሳ​ባ​ቸው ይኰ​ራ​ሉና፤
ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም በከ​ንቱ ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል።
21አቤቱ፥ የሚ​ጠ​ሉ​ህን እኔ የጠ​ላሁ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?
ስለ ጠላ​ቶ​ች​ህም አል​ጠ​ፋ​ሁ​ምን?
22ፍጹም ጥልን ጠላ​ኋ​ቸው፥ ጠላ​ቶ​ችም ሆኑኝ።
23አቤቱ፥ መር​ም​ረኝ፥ ልቤ​ንም ፈትን፤
ፈት​ነኝ፥ መን​ገ​ዶ​ች​ንም ዕወቅ፤
24በደ​ልም በእኔ ላይ ቢገኝ እይ፤
የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም መን​ገድ ምራኝ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in