መዝሙር 2
2
መዝሙር 2
መሲሓዊ ትዕይንት
1ሕዝቦች ለምን ያሤራሉ?#2፥1 ዕብራይስጡ እንዲሁ ሲሆን፣ ሰብዓ ሊቃናት ግን ይቈጣሉ ይላል።
ሰዎችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ?
2የምድር ነገሥታት ተነሡ፤
ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ#2፥2 ወይም የተቀባው ላይ
ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤
3“ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፣
የእግር ብረታቸውንም አውልቀን እንጣል” አሉ።
4በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤
ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
5ከዚያም በቍጣው ይናገራቸዋል፤
በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል፤
6ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣
በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።
7 የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤
እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤#2፥7 ወይም …አባትህ ሆንሁ
8ለምነኝ፤
መንግሥታትን ርስት አድርጌ፣
የምድርንም ዳርቻ ግዛት እንዲሆንህ እሰጥሃለሁ።
9አንተም በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፤#2፥9 ወይም በብረት ዘንግ ትሰባብራቸዋለህ
እንደ ሸክላ ዕቃ ታደቅቃቸዋለህ።”
10ስለዚህ እናንት ነገሥታት ልብ በሉ፤
እናንት የምድር ገዦችም፣ ተጠንቀቁ።
11 እግዚአብሔርን በፍርሀት አገልግሉት፤
ለእርሱ መራድም ደስ ያሰኛችሁ።
12እንዳይቈጣና በመንገድ እንዳትጠፉ፣
ዝቅ ብላችሁ ልጁን ሳሙት፤
ቍጣው ፈጥኖ ይነድዳልና።
እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።
Currently Selected:
መዝሙር 2: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.