መዝሙር 3
3
መዝሙር 3
የመከራ ተቀባዩ የጧት ጸሎት
ዳዊት ከልጁ ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ የዘመረው መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ!
ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!
2ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር
አይታደግሽም” አሏት። ሴላ#3፥2 በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚገኝ ሲሆን፣ የቃሉ ትርጕም በትክክል አይታወቅም፤ የሙዚቃ ምልክት ሳይሆን አይቀርም
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን
የምትከልል ጋሻ ነህ፤
ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና
የምታደርግ አንተ ነህ።#3፥3 ወይም እግዚአብሔር… ወደ ላይ የምታነሣ ክብሬ ሆይ
4ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ፤
እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ
5እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤
እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።
6በየአቅጣጫው የከበበኝን፣
አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
7 እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ!
አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤
የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤
የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።
8ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤
በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ
Currently Selected:
መዝሙር 3: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.