የዘላለም ሕይወትናሙና
የዘላለም ሕይወት ሊገኝ የሚችለው በኢየሱስ ብቻ ነው።
ጌታ ኢየሱስ ሰዎች የዘላለም ሕይወት እንዲኖራቸው ወደ ምድር መጣ። ጌታ ኢየሱስ ይህን ሕይወትን የሚሰጥ ብቸኛው መንገድ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ይህ የዘላለም ሕይወት በእግዚአብሔር ልጅ፣ በጌታ ኢየሱስ ውስጥ እንዳለ ይናገራል።
የዘላለም ሕይወት ምንጩ ከጌታ ኢየሱስ ጋር ያለን የግል ግንኙነት ላይ የተመስረት ሲሆን፤ ጌታ ኢየሱስ በቃሉ እንደተናገረው፡- ''መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም'' (ዮሐ. 14፡6)።
ሰዎች በራሳቸው ይህን ሕይወት ለማግኘት ሞክረዋል፣ ለምሳሌ በሥርዕት በመኖር ወይም በጥልቀት በማሰላሰል ሲሆን፤ ይህ እንደማይጠቅም በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በግልጽ ተቀምጧል። ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቀን እና የዘላለም ሕይወት የሚሰጠን ብቸኛው መንገድ ጌታ ኢየሱስ ነው። ያለዚህ እርቅ፣ ኃጢአታችን በእግዚአብሔር ፊት መቅረብን የማይቻል ያደርገዋል።
ለዚህም፣ ከጌታ ኢየሱስ ጋር የግል የሕይወት ግንኙንት አስፈላጊ እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ደጋግመው ያሳስባሉ፡- “እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20)።
የእግዚአብሔር ልጅ አለህ?
ስለ አገልግሎታችን መረጃ ለማግኘት GlobalRize.org እና እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ተጨማሪ ትምህርት ለማግኘት ይጎብኙን።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://globalrize.org