የዘላለም ሕይወትናሙና
የዘላለም ሕይወት በሞት አይቋረጥም።
ከጥቂት ቀናት በፊት የዘላለም ሕይወት የሚጀምረው ዳግመኛ በተወለድንበት ቅጽበት እንደሆነ ተነጋግረን ነበር። አማኞችም ልክ እንደ ሌሎች ሰዎች ስለሚሞቱ እንዴት ለዘላለም ሊኖሩ ይችላሉ?
ጌታ ኢየሱስ ይህን ጥያቄ፤ የወዳጁን የመቃብር ስፍራ በጎበኘበት ወቅት አንስቶት ነበር። ጌታ ኢየሱስ ከፊት ለፊቱ የተዘጋጀውን የሞትን አስጨናቂነት እና እውነትን ያውቅ ነበር። ሆኖም፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ ለዘላለም እንደማይሞት ተናግሯል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
''እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም'' (ዮሐንስ 5፡24)። የሰው ልጅ ከወደቀበት ጊዜ አንሥቶ ሞት ያስከተለው የኃጢአት እርግማን ተወግዷል፤ በመሆኑም ሞት በእሱ ላይ ተጽዕኖ የለውም።
አማኝ ሲሞት ሰውነቱ ብቻ ይሞታል፣ መንፈሱ ግን ከጌታ ጋር በክብር ይኖራል! ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋር መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ ( 2 ቆሮንቶስ 5፡8)። የስጋ ሞት ዘላለማዊ ህይወታችንን አያቋርጠውም።
''ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ? … በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን'' (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡55-57)።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://globalrize.org