የዘላለም ሕይወትናሙና
የዘላለም ሕይወት ማብቂያ የለውም።
እግዚአብሔር አምላካችን ዘላለማዊ ነው። አምላካችን ከጊዜ በላይ ነው። እርሱ ያለ እና የሚኖር ነው። "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው" (ዕብ 13፡8)።
በዚህ የዘላለም ሕይወት ውስጥ አማኞች ከአምላካቸው ጋር ያለ ጊዜ ገደብ ለዘላለም ይኖራሉ። የአምላካችን የእግዚአብሔር መንግሥት መቼም አያልቅም። የጌታ መልአክ ለዮሐንስ እንዳሳየው፡- ''ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም በግንባራቸው ላይ ይሆናል። ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሓይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘላለም እስከ ዘላለምም ይነግሣሉ'' (ራዕይ 22፡4-5)።
ለእኛ ህይወታችን አላፊ ለሆነው፣ በጊዜም ለተገደብነው ሰዎች የዘላለም ሕይወትን ለመረዳት ከባድ ነው። ''ዕድሜያችንንም በመቃተት እንጨርሳለን'' (መዝሙረ ዳዊት 90:9)።
የዛሬው ጽሑፍ እንደሚያሳየው፤ የዓለም ታሪክ ጅማሬና ፍጻሜ አለው፤ በጊዜ ገደብ ውስጥ ሊጠፋ ያለው ዓለም እና ምድሩ በማለፍ ጉዞ ላይ ይገኛል።
የአምላካችን የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ አይደለችም። እግዚአብሔር ለልጆቹ ቃል የገባላቸው የዘላለም ሕይወት ማብቂያ የለውም።
የዘላለም ሕይወት የማያልቅ በመሆኑ፣ በዚህ በሚጠፋው ዓለም ላይ ያለዎትን አመለካከት እንዴት ይለውጠዋል?
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://globalrize.org