የዘላለም ሕይወትናሙና
በአዲሱ ምድር ላይ ሀጢያት የለም።
የዘላለም ሕይወት ዋናው ነገር ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ተስማምቶ መኖር ሲሆን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በማመፅ ለሚኖሩ ሰዎች አይደለም። የኃጢአት ይቅርታ እና ጌትነቱን ያልተቀበሉ፤ በኃጢአተኛ አኗኗራቸው የጸኑ ሰዎች የዘላለም ሞት ይጠብቃቸዋል። ይህ በዚህ ምድር ላይ የምርጫቸው ውጤት ሲሆን፤ ማንም ሰው አሁን ከእግዚአብሔር ጋር መኖር የማይፈልግ፣ ለዘላለም ከእርሱ ጋር ሊኖር አይችልም።
የዘላለም ሕይወት ፍጹም የሆነ ሕይወትን ለኖሩ ሰዎች ብቻ አይደለም። ያ ቢሆን ኖሮ አንድም ሰው ብቁ አይሆንም ነበር። ሁላችንም እግዚአብሔርን በድለናል፣ ኃጢአተኛ ሆነን ተወልደናል። ዳዊት በመዝሙሩ “እነሆ በዓመፅ ተወልጃለሁ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” (መዝሙር 51፡5)።
ዋናው ነገር ኃጢአታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ታጥቦ መወገዱ ነው ( ራዕይ 7፡14)። ከኃጢዓታችን ንስሐ ከገባን እና ጌታ ኢየሱስን እንደ ጌታችን እና አዳኛችን ከተቀበልን እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ይላል። እርሱ "ተመልሰህ ትራራልናለህ፤ ኀጢአታችንን በእግርህ ትረግጣለህ፤ በደላችንንም ሁሉ ወደ ጥልቁ ባሕር ትጥላለህ"( ሚክያስ 7፡19)።
ከፈተናና ከኃጢአት ጋር ለሚታገሉ አማኞች ሁሉ ይህ ትልቅ ተስፋ ነው! በአዲሱ ምድር ላይ ኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ድል ይደረጋል።
ከኃጢአት ነጻ ለመሆን ትፈልጋለህ?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://globalrize.org